-
ይሖዋ ለራሱ የከበረ ስም ያደርጋልየኢሳይያስ ትንቢት—ለመላው የሰው ዘር የፈነጠቀ ብርሃን ጥራዝ 2
-
-
12, 13. (ሀ) ይሖዋን የሚረዳው የማይኖረው በምን መንገድ ነው? (ለ) የይሖዋ ክንድ መዳን የሚያስገኘው እንዴት ነው? ቁጣውስ የሚያግዘው እንዴት ነው?
12 ይሖዋ በመቀጠል እንዲህ አለ:- “ተመለከትሁ፣ የሚረዳም አልተገኘም፤ የሚያግዝም አልነበረምና ተደነቅሁ፤ ስለዚህ የገዛ ክንዴ መድኃኒት አመጣልኝ፣ ቁጣዬም እርሱ አገዘኝ። በቁጣዬም አሕዛብን ረገጥሁ በመዓቴም ቀጠቀጥኋቸው፣ ደማቸውንም ወደ ምድር አፈሰስሁት።”—ኢሳይያስ 63:5, 6
13 በይሖዋ ታላቅ የበቀል ቀን ይሖዋን እንደረዳ አድርጎ ሊናገር የሚችል ሰው አይኖርም። ይሖዋም ቢሆን ፈቃዱን ለማስፈጸም የማንንም ሰው እርዳታ አይሻም።c እጅግ ኃያልና ብርቱ የሆነው ክንዱ ዓላማውን በሚገባ መፈጸም ይችላል። (መዝሙር 44:3፤ 98:1፤ ኤርምያስ 27:5) ከዚህም በተጨማሪ ቁጣው ያግዘዋል። እንዴት? የአምላክ ቁጣ ከቁጥጥር ውጪ የሆነ ስሜት ሳይሆን የጽድቅ ቁጣ በመሆኑ ነው። ይሖዋ ምንጊዜም ትክክለኛ በሆኑ መሠረታዊ ሥርዓቶች ላይ የተመረኮዘ እርምጃ የሚወስድ በመሆኑ ቁጣው የጠላቶቹን ‘ደም ወደ ምድር በማፍሰስ’ የኀፍረት ማቅና ሽንፈት እንዲያከናንባቸው ያነሳሳዋል እንዲሁም ያግዘዋል።—መዝሙር 75:8፤ ኢሳይያስ 25:10፤ 26:5
-
-
ይሖዋ ለራሱ የከበረ ስም ያደርጋልየኢሳይያስ ትንቢት—ለመላው የሰው ዘር የፈነጠቀ ብርሃን ጥራዝ 2
-
-
c ይሖዋ የሚረዳው ባለመገኘቱ እንደተደነቀ ገልጿል። ኢየሱስ ከሞተ ወደ 2, 000 ከሚጠጉ ዓመታት በኋላም ኃያላን ሰዎች የአምላክን ፈቃድ የሚቃወሙ መሆናቸው እጅግ የሚያስገርም ሊሆን ይችላል።—መዝሙር 2:2-12፤ ኢሳይያስ 59:16
-