-
ይሖዋ ለራሱ የከበረ ስም ያደርጋልየኢሳይያስ ትንቢት—ለመላው የሰው ዘር የፈነጠቀ ብርሃን ጥራዝ 2
-
-
14. ኢሳይያስ ምን ተገቢ የሆኑ ማሳሰቢያዎችን ሰጥቷል?
14 በቀድሞ ዘመን አይሁዳውያን ይሖዋ ለእነሱ ሲል ላደረጋቸው ነገሮች የነበራቸው አድናቆት የጠፋው ወዲያውኑ ነበር። በመሆኑም ኢሳይያስ ይሖዋ እነዚህን ነገሮች ያደረገላቸው ለምን እንደሆነ መለስ ብለው እንዲያስቡ ማድረጉ የተገባ ነው። ኢሳይያስ እንዲህ አለ:- “እግዚአብሔር እንደ ሰጠን ሁሉ፣ የእግዚአብሔርን ቸርነትና [“ፍቅራዊ ደግነት፣” NW ] የእግዚአብሔርን ምስጋና፣ እንደ ምሕረቱና እንደ ቸርነቱም [“ፍቅራዊ ደግነቱ፣” NW ] ብዛት ለእስራኤል ቤት የሰጠውን ትልቅ በጎነት አሳስባለሁ። እርሱም:- በእውነት ሕዝቤ፣ ሐሰትን የማያደርጉ ልጆች፣ ናቸው አለ፤ መድኃኒትም ሆነላቸው። በጭንቃቸው ሁሉ እርሱ ተጨነቀ፣ የፊቱም መልአክ አዳናቸው፤ በፍቅሩና በርኅራኄውም ተቤዣቸው፣ በቀደመውም ዘመን ሁሉ አንሥቶ ተሸከማቸው።”—ኢሳይያስ 63:7-9
-
-
ይሖዋ ለራሱ የከበረ ስም ያደርጋልየኢሳይያስ ትንቢት—ለመላው የሰው ዘር የፈነጠቀ ብርሃን ጥራዝ 2
-
-
16. (ሀ) ይሖዋ ከእስራኤል ጋር ቃል ኪዳን ሲገባ ምን አመለካከት ነበረው? (ለ) አምላክ ሕዝቡን የሚይዘው በምን መንገድ ነው?
16 ይሖዋ እስራኤላውያንን ከግብጽ ነፃ ካወጣቸው በኋላ ወደ ሲና ተራራ በመውሰድ እንዲህ ሲል ቃል ገባላቸው:- “ቃሌን በእውነት ብትሰሙ ኪዳኔንም ብትጠብቁ፣ . . . የተመረጠ ርስት ትሆኑልኛላችሁ፤ እናንተም የካህናት መንግሥት የተቀደሰም ሕዝብ ትሆኑልኛላችሁ።” (ዘጸአት 19:5, 6) ይሖዋ ይህን ግብዣ ሲያቀርብላቸው እያታለላቸው ነበር? በፍጹም፤ ምክንያቱም ይሖዋ “በእውነት ሕዝቤ፣ ሐሰትን የማያደርጉ ልጆች፣ ናቸው” በማለት እንደተናገረ ኢሳይያስ ገልጿል። አንድ ምሁር የሚከተለውን አስተያየት ሰጥተዋል:- “እዚህ ቦታ ላይ ‘በእውነት’ የሚለው ቃል የገባው ሉዓላዊው ጌታ የደነገገው በመሆኑ ወይም ይሖዋ አስቀድሞ የማወቅ ችሎታ ስላለው አይደለም። ይሖዋ በሕዝቡ ተስፋ ሊያደርግና እምነት ሊጥልባቸው የቻለው በፍቅሩ ተገፋፍቶ ነው።” አዎን፣ ይሖዋ ቃል ኪዳን የገባው ሕዝቡ እንዲሳካላቸው ካለው ቅን ምኞት በመነሳት ነው። በግልጽ የሚታይ ድክመት የነበረባቸው ቢሆንም እንኳ እምነት ጥሎባቸዋል። በአምላኪዎቹ ላይ እንዲህ ያለ እምነት የሚጥልን አምላክ ማምለክ ምንኛ የሚያስደስት ነው! በዛሬው ጊዜ ያሉ ሽማግሌዎችም የአምላክ ሕዝቦች ባላቸው መልካም ጎን ላይ በማተኮርና ልክ እንደ ይሖዋ በእነሱ ላይ እምነት በመጣል በአደራ የተሰጧቸውን የጉባኤው አባላት በእጅጉ ማጠንከር ይችላሉ።—2 ተሰሎንቄ 3:4፤ ዕብራውያን 6:9, 10
-