-
‘በፈጠርሁት ለዘላለም ደስ ይበላችሁ’የኢሳይያስ ትንቢት—ለመላው የሰው ዘር የፈነጠቀ ብርሃን ጥራዝ 2
-
-
አስተማማኝ የሆነ ተስፋ
27. ኢሳይያስ ወደ ትውልድ አገራቸው የሚመለሱት አይሁዶች የሚያገኙትን ደህንነት የገለጸው እንዴት ነው?
27 በትንቢቱ የመጀመሪያ ፍጻሜ መሠረት በአዲሱ ሰማይ አገዛዝ ሥር የሚኖሩት ከግዞት የተመለሱ አይሁዶች ሕይወት ምን መልክ ይኖረዋል? ይሖዋ እንዲህ ሲል ገለጸ:- “ከዚያም ወዲያ ጥቂት ዘመን ብቻ የሚኖር ሕፃን፣ ወይም ዕድሜውን ያልፈጸመ ሽማግሌ አይገኝም፤ ጎልማሳው የመቶ ዓመት ሆኖት ይሞታልና፣ ኃጢአተኛውም የመቶ ዓመት ሆኖት የተረገመ ይሆናልና።” (ኢሳይያስ 65:20) ከግዞት የሚመለሱት አይሁዳውያን ቀድሞ ወደነበረችበት ሁኔታ በምትመለሰው የትውልድ አገራቸው የሚያገኙትን ደህንነት ቁልጭ አድርጎ የሚያሳይ ግሩም መግለጫ ነው! አራስ ልጅ በጥቂት ቀናት ውስጥ ሕይወቱ አይቀጭም። በዕድሜ የገፋውም ሰው ቢሆን ሙሉ የሕይወት ዘመኑን ሳያገባድድ በአጭር አይቀጭም።d ኢሳይያስ የተናገራቸው ቃላት ወደ ይሁዳ የሚመለሱትን አይሁዳውያን ምንኛ የሚያጽናኑ ናቸው! ወደ አገራቸው ከተመለሱ በኋላ ምንም ዓይነት አስጊ ሁኔታ ስለማይገጥማቸው ጠላቶቻችን ልጆቻችንን ይነጥቁናል ወይም ጎልማሶቹን ይፈጁብናል ብለው የሚጨነቁበት ምክንያት አይኖርም።
28. ይሖዋ የተናገራቸው ቃላት በአዲሱ ዓለም በመንግሥቱ አገዛዝ ሥር ምን ዓይነት ሕይወት እንደሚኖር ያስገነዝቡናል?
28 ይሖዋ የተናገራቸው ቃላት በቅርቡ በሚመጣው አዲስ ዓለም ውስጥ ስለሚኖረው ሕይወት ምን ያስገነዝቡናል? በአምላክ መንግሥት አገዛዝ ሥር እያንዳንዱ ልጅ አስተማማኝ ተስፋ ይጠብቀዋል። በተጨማሪም ፈሪሃ አምላክ ያለው ሰው በጉልምስና ዕድሜው በሞት አይቀጭም። ከዚህ ይልቅ ታዛዥ የሰው ልጆች ከስጋት ነፃ የሆነ፣ የተረጋጋና አስደሳች ሕይወት ይኖራሉ። በአምላክ ላይ የሚያምፁ ሰዎችስ ምን ይገጥማቸዋል? እንዲህ ያሉ ሰዎች የመኖር መብት ይነፈጋሉ። በአምላክ ላይ የሚያምፅ ኃጢአተኛ “የመቶ ዓመት ሆኖት ይሞታል።” ይህ ሰው ማብቂያ የሌለው ሕይወት ማግኘት ይችል የነበረ ከመሆኑ አንጻር ሲታይ “ገና ሕፃን” [NW ] ሳለ በሞት እንደተቀጨ ተደርጎ ይቆጠራል።
-
-
‘በፈጠርሁት ለዘላለም ደስ ይበላችሁ’የኢሳይያስ ትንቢት—ለመላው የሰው ዘር የፈነጠቀ ብርሃን ጥራዝ 2
-
-
d አዲሱ መደበኛ ትርጉም ኢሳይያስ 65:20ን እንዲህ ሲል ተርጉሞታል:- “ከእንግዲህም በዚያ፣ ለጥቂት ጊዜ ብቻ በሕይወት የሚኖር ሕፃን፣ ወይም ዕድሜ ያልጠገበ አረጋዊ አይኖርም፤ አንድ መቶ ዓመት የሞላው ሰው ቢሞት፣ በአጭር እንደ ተቀጨ ይቈጠራል።”
-