-
አዲሱ ዓለም—አንተም በዚያ ትገኝ ይሆን?መጠበቂያ ግንብ—2000 | ሚያዝያ 15
-
-
6. ስለ “አዲስ ሰማይና አዲስ ምድር” የሚጠቅሰው አራተኛው ትንቢት የሚተነብየው ምንድን ነው?
6 አሁን በኢሳይያስ 66:22-24 ላይ የሚገኘውን “አዲስ ሰማይና አዲስ ምድር” የሚለው ሐረግ የተጠቀሰበትን አራተኛውን ቦታ እንመርምር። “እኔ የምሠራቸው አዲስ ሰማይና አዲስ ምድር ከፊቴ ጸንተው እንደሚኖሩ፣ እንዲሁ ዘራችሁና ስማችሁ ጸንተው ይኖራሉ፣ ይላል እግዚአብሔር። እንዲህ ይሆናል፤ በየመባቻውና በየሰንበቱ ሥጋ ለባሽ ሁሉ በፊቴ ይሰግድ ዘንድ ዘወትር ይመጣል፣ ይላል እግዚአብሔር። ወጥተውም በእኔ ያመፁብኝን ሰዎች ሬሳቸውን ያያሉ፤ ትላቸው አይሞትምና፣ እሳታቸውም አይጠፋምና፤ ለሥጋ ለባሽም ሁሉ አስጸያፊ ነገር ይሆናሉ።”
7. ኢሳይያስ 66:22-24 በመጪዎቹ ጊዜያት ፍጻሜውን ያገኛል ብለን የምንደመድመው ለምንድን ነው?
7 ይህ ትንቢት ወደ ትውልድ አገራቸው በተመለሱት አይሁዳውያን ላይ ይሠራ የነበረ ቢሆንም ሌላም ፍጻሜ ያለው ነው። የጴጥሮስ ሁለተኛ መልእክትና የራእይ መጽሐፍ ወደ ፊት ስለሚመጣ ‘አዲስ ሰማይና አዲስ ምድር’ የሚናገሩ በመሆናቸው ይህ የሚከናወነው እነዚህ መጻሕፍት ከተጻፉበት ዘመን ብዙ ቆይቶ መሆን ይኖርበታል። በአዲሱ ሥርዓት ታላቅና የተሟላ ፍጻሜውን ያገኛል ብለን ልንጠብቅ እንችላለን። ወደፊት ይፈጸማሉ ብለን ልንጠብቃቸው ከምንችላቸው ሁኔታዎች መካከል አንዳንዶቹን እንመርምር።
-
-
አዲሱ ዓለም—አንተም በዚያ ትገኝ ይሆን?መጠበቂያ ግንብ—2000 | ሚያዝያ 15
-
-
9 በተመሳሳይም የአዲሱ ምድር አባሎች የሆኑት የአምላክ ታማኝ አገልጋዮች ማለትም በአዲሱ ዓለም ውስጥ የሚኖሩት የእውነተኛ አምላኪዎች ማኅበር አባላት፣ ሁሉን ነገር ለፈጠረው አምላክ ንጹሕ አምልኮ ስለሚያቀርቡ በግለሰብ ደረጃ ጸንተው ይቆማሉ። ይህ አምልኮ አልፎ አልፎ ወይም ሲመች ብቻ የሚከናወን አይሆንም። በሙሴ በኩል ለእስራኤል ሕዝብ የተሰጠው የአምላክ ሕግ በየወሩ አዲስ ጨረቃ በታየ ቁጥር፣ እንዲሁም በየሳምንቱ በሰንበት ቀን መፈጸም የሚገባው የአምልኮ ሥርዓት እንዳለ ይደነግግ ነበር። (ዘሌዋውያን 24:5-9፤ ዘኁልቁ 10:10፤ 28:9, 10፤ 2 ዜና መዋዕል 2:4) ስለዚህ ኢሳይያስ 66:23 የእውነተኛው አምላክ አምልኮ ከሳምንት እስከ ሳምንት፣ ከወር እስከ ወር ዘወትር በቋሚነት እንደሚከናወን ያሳያል። አምላክ የለሽነትና ሃይማኖታዊ ግብዝነት በዚያ ጊዜ አይኖርም። ‘ሥጋ ለባሽ ሁሉ በይሖዋ ፊት ይሰግድ ዘንድ ይመጣል።’
-