-
የሰላም መስፍን እንደሚነሳ የተሰጠ ተስፋየኢሳይያስ ትንቢት—ለመላው የሰው ዘር የፈነጠቀ ብርሃን ጥራዝ 1
-
-
የአምላክ ‘ሕግና ምስክር’
8. ዛሬ ልንመራበት የሚገባው ‘ሕግ’ እና ‘ምስክር’ ምንድን ነው?
8 ሌሎቹን ትእዛዛት ጨምሮ መናፍስታዊ ሥራዎችን የሚከለክለው የይሖዋ ሕግ ለይሁዳ ሰዎች የተሰወረ አልነበረም። በጽሑፍ የሰፈረ ነገር ነበር። ዛሬም የተሟላው ቃሉ በጽሑፍ ይገኛል። ይህም መለኮታዊ ሕጎችንና መመሪያዎችን ብቻ ሳይሆን አምላክ ከሕዝቡ ጋር ስላደረገው ግንኙነት የሚገልጹ ዘገባዎችን የያዘው መጽሐፍ ቅዱስ ነው። ይሖዋ ከሰዎች ጋር ስላደረገው ግንኙነት የሚገልጸው በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የሚገኘው ይህ ዘገባ እንደ ምሥክር ወይም ማረጋገጫ ሆኖ ስለ ይሖዋ ማንነትና ባሕርያት ያስተምረናል። እስራኤላውያን መመሪያ ለማግኘት ሙታንን ከማማከር ይልቅ መሄድ የነበረባቸው ወደ ማን ነው? ኢሳይያስ “ወደ ሕግና ወደ ምስክር” በማለት መልሱን ይሰጠናል። (ኢሳይያስ 8:20ሀ) አዎን፣ እውነተኛ የእውቀት ብርሃን ማግኘት የሚፈልጉ ሁሉ መሄድ ያለባቸው በጽሑፍ ወደ ሰፈረው የአምላክ ቃል ነው።
9. ንስሐ የማይገቡ ኃጢአተኞች መጽሐፍ ቅዱስን የሚጠቅሱ መሆናቸው የሚፈይደው ነገር አለ?
9 ከመናፍስታዊ ድርጊቶች ጋር ንክኪ የነበራቸው አንዳንድ እስራኤላውያን በጽሑፍ ለሰፈረው የአምላክ ቃል አክብሮት አለን ብለው ይናገሩ ይሆናል። ይሁን እንጂ ይህ ከእውነታው የራቀ የግብዝነት አነጋገር ነው። ኢሳይያስ “እንዲህም ያለውን ቃል ደጋግመው ይናገሩታል ንጋትም አይበራላቸውም” ብሏል። (ኢሳይያስ 8:20ለ NW ) ኢሳይያስ እዚህ ላይ እየተናገረ ያለው ስለ የትኛው ቃል ነው? ‘ወደ ሕጉና ወደ ምስክሩ’ የሚለውን ቃል መጥቀሱ ሊሆን ይችላል። ምናልባት ዛሬ ያሉት ከሃዲዎች እንደሚያደርጉት አንዳንድ ከሃዲ እስራኤላውያን የአምላክን ቃል እየጠቀሱ ይናገሩ ይሆናል። ይሁን እንጂ ይህ እንዲሁ ቃል ብቻ ነው። የይሖዋን ፈቃድ ማድረግና ንጹሕ ካልሆኑ ልማዶች መራቅ ካልታከለበት በስተቀር ጥቅሶችን መጥቀሱ ብቻውን ወደ ‘ንጋት ብርሃን’ ወይም ከይሖዋ ወደሚገኘው የእውቀት ብርሃን አይመራም።b
-
-
የሰላም መስፍን እንደሚነሳ የተሰጠ ተስፋየኢሳይያስ ትንቢት—ለመላው የሰው ዘር የፈነጠቀ ብርሃን ጥራዝ 1
-
-
b በኢሳይያስ 8:20 ላይ የሚገኘው “እንዲህም ያለውን ቃል” የሚለው ሐረግ በኢሳይያስ 8:19 ላይ የተጠቀሰውን መናፍስታዊ ሥራ የሚያመለክት ሊሆን ይችላል። ይህ ከሆነ ደግሞ ኢሳይያስ በይሁዳ መናፍስታዊ ሥራን የሚያስፋፉት ሰዎች ሌሎችም መናፍስት ጠሪዎችን እንዲጠይቁ መወትወታቸውን ይቀጥላሉ ማለቱ ስለሚሆን ከይሖዋ ምንም ዓይነት የእውቀት ብርሃን አያገኙም።
-