-
በመሲሑ ግዛት የሚገኝ መዳንና ደስታየኢሳይያስ ትንቢት—ለመላው የሰው ዘር የፈነጠቀ ብርሃን ጥራዝ 1
-
-
6. በትንቢት የተነገረው መሲሑ ምን ዓይነት ገዥ እንደሚሆን ነው?
6 መሲሑ ምን ዓይነት ገዥ ይወጣው ይሆን? አሥሩን ነገድ ሰሜናዊ የእስራኤል መንግሥት እንዳጠፉት አሦራውያን ጨካኝና ያሻውን የሚያደርግ ንጉሥ ይሆናልን? በፍጹም አይሆንም። መሲሑን በተመለከተ ኢሳይያስ እንዲህ ይላል:- “የእግዚአብሔር መንፈስ፣ የጥበብና የማስተዋል መንፈስ፣ የምክርና የኃይል መንፈስ፣ የእውቀትና እግዚአብሔርን የመፍራት መንፈስ ያርፍበታል። እግዚአብሔርን በመፍራት ደስታውን ያያል። ” (ኢሳይያስ 11:2, 3ሀ) መሲሑ የተቀባው በዘይት ሳይሆን በአምላክ ቅዱስ መንፈስ ነው። ይህ የሆነው ኢየሱስ ሲጠመቅ ዮሐንስ እያየ የአምላክ ቅዱስ መንፈስ በእርግብ አምሳል በወረደበት ጊዜ ነበር። (ሉቃስ 3:22) ኢየሱስ የይሖዋ መንፈስ ‘አርፎበታል።’ በጥበብ፣ በማስተዋል፣ በምክር፣ በኃይልና በእውቀት ያከናወናቸው ነገሮች ይህንኑ የሚያንጸባርቁ ናቸው። እነዚህ አንድ ገዥ ሊኖረው የሚገቡ እንዴት ያሉ ግሩም ባሕርያት ናቸው!
-
-
በመሲሑ ግዛት የሚገኝ መዳንና ደስታየኢሳይያስ ትንቢት—ለመላው የሰው ዘር የፈነጠቀ ብርሃን ጥራዝ 1
-
-
8. ኢየሱስ ይሖዋን በመፍራት ደስ የሚለው እንዴት ነው?
8 በመሲሑ ላይ የሚንጸባረቀው የይሖዋ ፍርሃት ምንድን ነው? ኢየሱስ የአምላክን ኩነኔ በመፍራት ይሸበራል ማለት እንዳልሆነ ግልጽ ነው። ከዚህ ይልቅ መሲሑ ለአምላክ ያለው ፍርሃት በፍቅርና በአክብሮት ላይ የተመሠረተ ነው። አምላክን የሚፈራ አንድ ሰው እንደ ኢየሱስ ሁልጊዜ አምላክን “ደስ የሚያሰኘውን” ለማድረግ ይጥራል። (ዮሐንስ 8:29) ኢየሱስ በየዕለቱ ጤናማ በሆነ መንገድ ይሖዋን በመፍራት ከመመላለስ የበለጠ ደስታ እንደሌለ በቃልም ሆነ በድርጊት አስተምሯል።
ጻድቅና መሐሪ የሆነ ፈራጅ
9. በክርስቲያን ጉባኤ ውስጥ የመፍረድ ሥልጣን ላላቸው ወንዶች ኢየሱስ ምሳሌ የሚሆነው እንዴት ነው?
9 ኢሳይያስ ስለ መሲሑ ባሕርይ ተጨማሪ ነገርም ተንብዮአል:- “ዓይኑም እንደምታይ አይፈርድም፣ ጆሮውም እንደምትሰማ አይበይንም።” (ኢሳይያስ 11:3ለ) ችሎት ፊት መቅረብ ቢኖርብህና እንዲህ ዓይነት ዳኛ ብታገኝ ደስ አይልህም? መሲሑ የሰው ዘር ሁሉ ፈራጅ ሆኖ ሲሠራ በሐሰት የመከራከሪያ ነጥቦች፣ ችሎትን ለማደናገር በሚሰነዘሩ መሠሪ ሐሳቦች፣ በወሬ ወይም እንደ ሀብት ባሉ ውጫዊ ነገሮች አይታለልም። ማታለያዎችን ለይቶ ያውቃል እንዲሁም እምብዛም ከማይማርኩ ውጫዊ ሁኔታዎች በስተጀርባ ያለውን ይመለከታል። ‘የተሰወረውን የልብ ሰው’ ማለትም ‘ስውር የሆነውን ማንነት’ ያስተውላል። (1 ጴጥሮስ 3:4፣ የአዲሲቱ ዓለም ትርጉም የግርጌ ማስታወሻ) ይህ ወደር የማይገኝለት የኢየሱስ ምሳሌ በክርስቲያን ጉባኤ ውስጥ የመፍረድ ሥልጣን ላላቸው ሁሉ ግሩም አርዓያ ነው።—1 ቆሮንቶስ 6:1-4
-