-
ይሖዋ ኩሩዋን ከተማ ያዋርዳልየኢሳይያስ ትንቢት—ለመላው የሰው ዘር የፈነጠቀ ብርሃን ጥራዝ 1
-
-
አምላክ ለማጥፋት የሚጠቀምበት መሣሪያ
10. ባቢሎንን ድል ለማድረግ ይሖዋ የሚጠቀመው በማን ነው?
10 ይሖዋ ባቢሎንን ለመጣል የሚጠቀምበት ኃይል የትኛው ይሆን? ከ200 ዓመታት ቀደም ብሎ ይሖዋ መልሱን ሰጥቷል:- “እነሆ፣ ብር የማይሹትን፣ ወርቅም የማያምራቸውን ሜዶናውያንን በላያቸው አስነሣለሁ። ፍላጾቻቸውም ጎበዞችን ይጨፈጭፋሉ፣ የማኅፀንንም ፍሬ አይምሩም፣ ዓይኖቻቸውም ለሕፃናት አይራሩም። እግዚአብሔርም ሰዶምንና ገሞራን ባፈረሰ ጊዜ እንደ ነበረው፣ የመንግሥታት ክብር የከለዳውያንም ትዕቢት ጌጥ ባቢሎን እንዲሁ ትሆናለች።” (ኢሳይያስ 13:17-19) የተቀማጠለችው ባቢሎን ትወድቃለች። ለይሖዋ እንደ መሣሪያ ሆኖ ይህን የሚያስፈጽመው ደግሞ በሩቅ ካለው የሜዶን ተራራማ አካባቢ የሚመጣ ሠራዊት ይሆናል።a በመጨረሻም ባቢሎን በሥነ ምግባር ብልግና የለየላቸው እንደነበሩት እንደ ሰዶምና ገሞራ ከተሞች ባድማ ትሆናለች።—ዘፍጥረት 13:13፤ 19:13, 24
-
-
ይሖዋ ኩሩዋን ከተማ ያዋርዳልየኢሳይያስ ትንቢት—ለመላው የሰው ዘር የፈነጠቀ ብርሃን ጥራዝ 1
-
-
11, 12. (ሀ) ሜዶን የዓለም ኃይል ለመሆን የበቃችው እንዴት ነው? (ለ) ትንቢቱ ስለ ሜዶን ሠራዊት የሚጠቅሰው እንግዳ የሆነ ባሕርይ ምንድን ነው?
11 በኢሳይያስ ዘመን ሜዶንና ባቢሎን በአሦር የግዛት ቀንበር ሥር ነበሩ። ከአንድ መቶ ዓመት ገደማ በኋላ በ632 ከዘአበ ሜዶንና ባቢሎን ሠራዊታቸውን አስተባብረው የአሦር ዋና ከተማ የነበረችውን ነነዌን ገለበጡ። ይህም ባቢሎን የዓለም ልዕለ ኃያል መንግሥት እንድትሆን በር ከፍቶላታል። ከአንድ መቶ ዓመት ገደማ በኋላ ግን ሜዶን እርሷን ለማጥፋት የምትነሣ ጠላትዋ እንደምትሆን አልተገነዘበችም! ይሁን እንጂ ከይሖዋ አምላክ ሌላ ይህንን ነገር አስቀድሞ ሊያውቅ የሚችል ማን ይኖራል?
12 ይሖዋ ለጥፋቱ እንደ መሣሪያ አድርጎ የሚጠቀምበትን ኃይል ማንነት ሲገልጽ የሜዶን ሠራዊት ‘ብር እንደማይሻና ወርቅም እንደማያምረው’ ተናግሯል። የጦርነት አባዜ ከተጠናወታቸው ወታደሮች የማይጠበቅ የሚያስገርም ባሕርይ ነው! የመጽሐፍ ቅዱስ ምሁር የሆኑት አልበርት ባርነስ እንዲህ ብለዋል:- “ምርኮን ተስፋ አድርጎ የማይነሳ ወራሪ ሠራዊት የለም ለማለት ይቻላል።” የሜዶን ሠራዊት በዚህ ረገድ ይሖዋ እንዳለው ሆኖ ተገኝቷልን? አዎን። በጄ ግሌንትዎርዝ በትለር በተዘጋጀው ዘ ባይብል ዎርክ በተባለው መጽሐፍ ላይ የቀረበውን ይህን አስተያየት ተመልከት:- “እስከ ዛሬ ድረስ ውጊያ ከገጠሙት ብሔራት ሁሉ በተለየ መልኩ ሜዶናውያን በተለይ ደግሞ ፋርሳውያን ከወርቅ ይልቅ የሚያጓጓቸው የሚያገኙት ድልና ክብር ነበር።”b ከዚህ አንፃር ሲታይ የፋርሱ ገዢ ቂሮስ እስራኤላውያንን ከባቢሎን ግዞት ነፃ አውጥቶ በሰደዳቸው ጊዜ ናቡከደነፆር ከኢየሩሳሌም ቤተ መቅደስ የዘረፋቸውን በሺህ የሚቆጠሩ የወርቅና የብር ዕቃዎች ለእስራኤላውያኑ መመለሱ ምንም አያስገርምም።—ዕዝራ 1:7-11
13, 14. (ሀ) የሜዶንና የፋርስ ተዋጊዎች ለምርኮ እምብዛም ባይጎመጁም ከፍተኛ ግምት የሚሰጡት ለምን ነገር ነበር? (ለ) ቂሮስ ባቢሎን ትኩራራበት የነበረውን መከላከያ ያለፈው እንዴት ነው?
13 የሜዶንም ሆኑ የፋርስ ተዋጊዎች ለምርኮ ያላቸው ፍቅር እምብዛም ይሁን እንጂ የሥልጣን ጥም ግን ነበራቸው። በዓለም መድረክ ከየትኛውም መንግሥት አንሰው መገኘት አይፈልጉም። ከዚህም በላይ ይሖዋ በልባቸው ‘ጥፋትን’ አስገብቷል። (ኢሳይያስ 13:6) በመሆኑም የባቢሎናውያን እናቶች የማኅፀን ፍሬ የሆኑትን የጠላት ወታደሮች ‘የሚጨፈጭፉበትን’ ፍላጻ ለማስወንጨፍ በሚጠቀሙበት ጠንካራ ደጋን አማካኝነት ባቢሎንን ለማንበርከክ ቆርጠዋል።
14 የባቢሎን ቅጥሮች የሜዶ ፋርስ ሠራዊት አለቃ የሆነውን ቂሮስን አልገቱትም። በ539 ከዘአበ ጥቅምት 5/6 ምሽት ላይ የኤፍራጥስን ወንዝ አቅጣጫ እንዲያስቀይሩ ትእዛዝ ሰጠ። የውኃው መጠን እየጎደለ ሲመጣ ወራሪዎቹ እስከ ጭናቸው የሚደርሰውን ውኃ አቋርጠው በቀስታ ወደ ከተማዋ ገቡ። የባቢሎን ነዋሪዎች ተዘናግተው እያሉ ተያዙና ባቢሎን ወደቀች። (ዳንኤል 5:30) ይሖዋ አምላክ ኢሳይያስ እነዚህን ነገሮች እንዲተነብይ በመንፈሱ አነሳስቶታል። ጉዳዩ በይሖዋ እጅ እንደነበር ምንም አያጠራጥርም።
-
-
ይሖዋ ኩሩዋን ከተማ ያዋርዳልየኢሳይያስ ትንቢት—ለመላው የሰው ዘር የፈነጠቀ ብርሃን ጥራዝ 1
-
-
a ኢሳይያስ በስም የጠቀሰው ሜዶንን ብቻ ነው። ይሁን እንጂ በባቢሎን ላይ አብረው የሚነሱት ነገሥታት በርከት ያሉ ሲሆኑ እነርሱም ሜዶን፣ ፋርስ፣ ኤላም እና ሌሎችም ትናንሽ ብሔራት ናቸው። (ኤርምያስ 50:9፤ 51:24, 27, 28) በአካባቢው የነበሩት አገሮች ሜዶንንና ፋርስን የሚጠሯቸው “ሜዶን” ብለው ነበር። ደግሞም በኢሳይያስ ዘመን ገናና ኃይል የነበረችው ሜዶን ናት። ፋርስ ኃያል ሆና ብቅ ያለችው በቂሮስ የግዛት ዘመን ነው።
-
-
ይሖዋ ኩሩዋን ከተማ ያዋርዳልየኢሳይያስ ትንቢት—ለመላው የሰው ዘር የፈነጠቀ ብርሃን ጥራዝ 1
-
-
b ይሁን እንጂ ከጊዜ በኋላ ሜዶናውያንና ፋርሳውያን ከፍተኛ የቅንጦት ፍቅር ያደረባቸው ይመስላል።—አስቴር 1:1-7
-