-
ይሖዋ የጢሮስን ትዕቢት ይሽራልየኢሳይያስ ትንቢት—ለመላው የሰው ዘር የፈነጠቀ ብርሃን ጥራዝ 1
-
-
“የተርሴስ መርከቦች ሆይ፣ አልቅሱ”
3, 4. (ሀ) ተርሴስ የምትገኘው የት ነበር? በጢሮስና በተርሴስ መካከል የነበረው ዝምድና ምንድን ነው? (ለ) ከተርሴስ ጋር የሚነግዱት መርከበኞች ‘የሚያለቅሱበት’ ምክንያት አላቸው የምንለው ለምንድን ነው?
3 ኢሳይያስ “ስለ ጢሮስ የተነገረ ሸክም” የሚል ርዕስ ሰጥቶ ከጀመረ በኋላ እንዲህ ይላል:- “የተርሴስ መርከቦች ሆይ፣ አልቅሱ፤ ፈርሶአልና ቤት [“ወደብ፣” NW] የለም፣ መግባትም የለም።” (ኢሳይያስ 23:1ሀ) ተርሴስ በሜዲትራኒያን ምሥራቃዊ ክፍል ካለችው ጢሮስ ርቃ የምትገኝ የስፔይን አካል እንደነበረች ይታመናል።a ያም ሆኖ ግን የፊንቄ ሰዎች የተዋጣላቸው ባሕረተኞች የነበሩ ሲሆን መርከቦቻቸውም ትላልቅና አስተማማኝ ነበሩ። አንዳንድ ታሪክ ጸሐፊዎች በጨረቃና በማዕበል መካከል ያለውን ትስስር በማስተዋልና የሰማይን ምልክት ለባሕር ላይ ጉዞ እንደ መረጃ አድርገው በመጠቀም ረገድ የመጀመሪያ የሆኑት የፊንቄ ሰዎች እንደሆኑ ያምናሉ። በመሆኑም ከጢሮስ እስከ ተርሴስ ያለው ረጅም ርቀት እንቅፋት አልሆነባቸውም።
4 በኢሳይያስ ዘመን ተርሴስ ለጢሮስ ጥሩ የሸቀጥ ማራገፊያ የነበረች ሲሆን ምናልባትም ለብዙ ዘመናት ዋነኛ የብልጽግናዋ ምንጭ ሳትሆንላት አልቀረችም። ስፔይን የብር፣ የብረት፣ የቆርቆሮ እና የሌሎች የብረት ማዕድናት ከፍተኛ ክምችት ነበራት። (ከኤርምያስ 10:9፤ ሕዝቅኤል 27:12 ጋር አወዳድር።) “የተርሴስ መርከቦች” ማለትም ለንግድ ወደ ተርሴስ የሚመጡ የጢሮስ መርከቦች ሳይሆኑ አይቀሩም ማረፊያ ወደብ ሆናላቸው የነበረችው ጢሮስ በመጥፋቷ ‘ማልቀሳቸው’ ምንም አያስገርምም።
5. ከተርሴስ የሚመጡት መርከበኞች የጢሮስን መውደቅ የሚሰሙት የት ነው?
5 በባሕር ላይ ያሉት መርከበኞች የጢሮስን መውደቅ የሚያውቁት እንዴት ነው? ኢሳይያስ “ከኪቲም አገር ጀምሮ ተገልጦላቸዋል” በማለት መልሱን ይሰጣል። (ኢሳይያስ 23:1ለ) ‘የኪቲም አገር’ የተባለችው ከፊንቄ የባሕር ዳርቻ በስተ ምዕራብ 100 ኪሎ ሜትር ገደማ ርቃ የምትገኘው የቆጵሮስ ደሴት ሳትሆን አትቀርም። ከተርሴስ ተነስተው ወደ ምሥራቅ ለሚያቀኑት መርከቦች ይህ ጢሮስ ከመድረሳቸው በፊት የሚቆሙበት የመጨረሻ ማረፊያቸው ነው። በመሆኑም መርከበኞቹ በቆጵሮስ በሚያደርጉት ቆይታ ወቅት ማረፊያ ወደባቸው መውደቋን የሚገልጽ ወሬ ይሰማሉ። ይህ ለእነርሱ እንዴት አስደንጋጭ ነው! የሚያደርጉት ጠፍቷቸው ‘ያለቅሳሉ።’
-
-
ይሖዋ የጢሮስን ትዕቢት ይሽራልየኢሳይያስ ትንቢት—ለመላው የሰው ዘር የፈነጠቀ ብርሃን ጥራዝ 1
-
-
a አንዳንድ ምሁራን ተርሴስ በሜዲትራኒያን በስተ ምዕራብ የምትገኘው ሰርዲኒያ ነች ይላሉ። ሰርዲኒያም ቢሆን የምትገኘው ከጢሮስ በጣም ርቃ ነበር።
-