-
ይሖዋ ንጉሥ ነውየኢሳይያስ ትንቢት—ለመላው የሰው ዘር የፈነጠቀ ብርሃን ጥራዝ 1
-
-
6. ይሖዋ በረከቱን ከምድሪቱ የሚያነሳው ለምንድን ነው?
6 ኢሳይያስ የሚያሻማ ነገር እንዳይኖር ሲል መጪው ጥፋት ምን ያህል ስፋት እንዳለውና የሚመጣበት ምክንያት ጭምር ምን እንደሆነ ግልጽ አድርጓል:- “ምድርም አለቀሰች ረገፈችም፤ ዓለም ደከመች ረገፈችም፤ የምድርም ሕዝብ ታላላቆች ደከሙ። ምድርም ከሚቀመጡባት በታች ረክሳለች፣ ሕጉን ተላልፈዋልና፣ ሥርዓቱንም ለውጠዋልና፣ የዘላለሙንም [“ላልተወሰነ ጊዜ የሚዘልቀውን፣” NW] ቃል ኪዳን አፍርሰዋልና። ስለዚህ መርገም ምድርን ትበላለች በእርስዋም የተቀመጡ ይቀጣሉ፤ ስለዚህ የምድር ሰዎች ይቃጠላሉ ጥቂት ሰዎችም ይቀራሉ።” (ኢሳይያስ 24:4-6) እስራኤላውያን የከነዓንን ምድር ሲወርሱ ምድሪቱ ‘ወተትና ማር የምታፈስስ’ ሆና አግኝተዋታል። (ዘዳግም 27:3) ያም ሆኖ ሕልውናቸው በይሖዋ በረከት የተመካ ነበር። በሥርዓቱ ቢሄዱና ትእዛዙን ቢጠብቁ ምድሪቱ “እህልዋን ትሰጣለች።” ሕጉንና ትእዛዙን ቢተላለፉ ግን ምድሪቱን ለማልማት የሚያደርጉት ጥረት ሁሉ ‘ከንቱ ይሆናል’ ምድሪቱም “እህልዋን አትሰጥም።” (ዘሌዋውያን 26:3-5, 14, 15, 20) የይሖዋም መርገም ‘ምድርን ትበላለች።’ (ዘዳግም 28:15-20, 38-42, 62, 63) አሁን ይሁዳ የሚጠብቃት ይህ እርግማን ነው።
-
-
ይሖዋ ንጉሥ ነውየኢሳይያስ ትንቢት—ለመላው የሰው ዘር የፈነጠቀ ብርሃን ጥራዝ 1
-
-
8. (ሀ) ሕዝቡ ‘ሕጉን የተላለፉትና’ ‘ሥርዓቱን የለወጡት’ እንዴት ነው? (ለ) ‘ከሚረግፉት’ መካከል ‘ታላላቆቹ’ የመጀመሪያ የሆኑት እንዴት ነው?
8 ይሁን እንጂ ሕዝቡ “ላልተወሰነ ጊዜ የሚዘልቀውን ቃል ኪዳን” አፍርሷል። ከመለኮታዊ ምንጭ ያገኙትን ሕግ ወደ ጎን ገሸሽ በማድረግ ተላልፈዋል። በሕግ ነክ ጉዳዮች ረገድ ይሖዋ ከሰጣቸው የተለየ አሠራር በመከተል “ሥርዓቱን ለውጠዋል።” (ዘጸአት 22:25፤ ሕዝቅኤል 22:12) ከዚህ የተነሣ ሕዝቡ ከምድሪቱ ይወገዳል። ምሕረት የሌለው ፍርድ ይጠብቃቸዋል። ይሖዋ ጥበቃውንና ሞገሱን በማንሳቱ ምክንያት ‘ከሚረግፉት’ ሰዎች መካከል የመጀመሪያዎቹ ‘ታላላቆች’ ማለትም ከፍ ያለ ቦታ ያላቸው ናቸው። በዚህ ትንቢት ፍጻሜ መሠረት የኢየሩሳሌም ጥፋት እየተቃረበ ሲመጣ በመጀመሪያ ግብጻውያን ከዚያም ባቢሎናውያን የይሁዳን ነገሥታት ገባር ንጉሥ አድርገው ይገዟቸዋል። በዚህ መሠረት ወደ ባቢሎን በምርኮ ከተወሰዱት የመጀመሪያዎቹ ሰዎች መካከል ንጉሥ ኢዮአቄምና ሌሎች የንጉሣዊው ቤተሰብ አባላት ይገኙበታል።—2 ዜና መዋዕል 36:4, 9, 10
-