-
የመጨረሻው ጠላት የሆነው ሞት ይደመሰሳልመጠበቂያ ግንብ—2014 | መስከረም 15
-
-
10. (ሀ) ይሖዋ፣ በአዳም ምክንያት የመጣውን ኃጢአት እንደሚደመስስ የሚያሳዩ አንዳንድ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች የትኞቹ ናቸው? (ለ) እነዚህ ጥቅሶች ስለ ይሖዋ እና ስለ ልጁ ምን ያስተምሩናል?
10 ይሖዋ፣ ጳውሎስን ሊታደገው ይችላል። ኢሳይያስ ስለ ‘መጋረጃው’ ከተናገረ በኋላ “ሞትንም ለዘላለም ይውጣል። ጌታ እግዚአብሔር ከፊት ሁሉ እንባን ያብሳል” ሲል ጽፏል። (ኢሳ. 25:8) ለልጆቹ ሥቃይ መንስኤ የሆነውን ነገር በማስወገድ እንባቸውን እንደሚያብስ አባት ሁሉ ይሖዋም በአዳም ምክንያት የመጣውን ሞት ለማስወገድ ይጓጓል! ይህንንም ሲያደርግ የሚተባበረው አካል አለ። 1 ቆሮንቶስ 15:22 “ሁሉም በአዳም እንደሚሞቱ ልክ እንደዚሁም ሁሉም በክርስቶስ ሕያው ይሆናሉ” ይላል። በተመሳሳይም ጳውሎስ “ማን ይታደገኛል?” ብሎ ከጠየቀ በኋላ “በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል የሚታደገኝ አምላክ የተመሰገነ ይሁን!” ብሏል። (ሮም 7:25) በግልጽ ለማየት እንደሚቻለው ይሖዋ የሰው ልጆችን እንዲፈጥር ያነሳሳው ፍቅር፣ አዳምና ሔዋን ካመፁ በኋላም አልቀዘቀዘም። ይሖዋ የመጀመሪያዎቹን ባልና ሚስት ሲፈጥር በሥራው የተባበረው ኢየሱስም ለሰው ልጆች ያለው ልዩ ፍቅር አልቀነሰም። (ምሳሌ 8:30, 31) ይሁንና የሰው ልጆችን መታደግ የሚቻለው እንዴት ነው?
-
-
የመጨረሻው ጠላት የሆነው ሞት ይደመሰሳልመጠበቂያ ግንብ—2014 | መስከረም 15
-
-
15, 16. (ሀ) “የመጨረሻው ጠላት የሆነው ሞት” የሚለው አገላለጽ ምንን ያመለክታል? ይህ ጠላት የሚደመሰሰውስ መቼ ነው? (ለ) 1 ቆሮንቶስ 15:28 እንደሚገልጸው ከጊዜ በኋላ ኢየሱስ ምን ያደርጋል?
15 የመንግሥቱ የሺህ ዓመት ግዛት ሲያበቃ ታዛዥ የሆኑ የሰው ልጆች፣ በአዳም አለመታዘዝ ምክንያት ከመጡት ጠላቶች በሙሉ ነፃ ይወጣሉ። መጽሐፍ ቅዱስ እንዲህ ይላል፦ “ሁሉም በአዳም እንደሚሞቱ ልክ እንደዚሁም ሁሉም በክርስቶስ ሕያው ይሆናሉ። ሆኖም እያንዳንዱ በራሱ ተራ ይሆናል፦ ክርስቶስ በኩራት ነው፤ በመቀጠል ደግሞ ክርስቶስ በሚገኝበት ጊዜ የእሱ የሆኑት [ተባባሪ ገዢዎቹ] ሕያዋን ይሆናሉ። ከዚያም መንግሥትን ሁሉ እንዲሁም ሥልጣንን ሁሉና ኃይልን አጥፍቶ መንግሥቱን ለአምላኩና ለአባቱ በሚያስረክብበት ጊዜ ፍጻሜ ይሆናል። አምላክ ጠላቶችን ሁሉ ከእግሩ በታች እስኪያደርግለት ድረስ ንጉሥ ሆኖ ሊገዛ ይገባዋልና። የመጨረሻው ጠላት የሆነው ሞት ይደመሰሳል።” (1 ቆሮ. 15:22-26) አዎን፣ ከአዳም የተወረሰው ሞት በመጨረሻ ይወገዳል። መላውን የሰው ዘር የሸፈነው “መጋረጃ” ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ይጠፋል።—ኢሳ. 25:7, 8
-