-
ይሖዋን በመተማመን ተጠባበቁየኢሳይያስ ትንቢት—ለመላው የሰው ዘር የፈነጠቀ ብርሃን ጥራዝ 1
-
-
13. የይሁዳ መሪዎች ትምክህታቸውን የጣሉት በምን ነገር ላይ ነበር? እንዲህ ያለውስ ትምክህት ተገቢ ነውን?
13 ከዚያም ኢሳይያስ እንዲህ በማለት ያብራራል:- “ነገር ግን:- በፈረስ ላይ ተቀምጠን እንሸሻለን እንጂ እንዲህ አይሆንም አላችሁ፣ ስለዚህም ትሸሻላችሁ፤ ደግሞም:- በፈጣን ፈረስ ላይ እንቀመጣለን አላችሁ፣ ስለዚህም የሚያሳድዱአችሁ ፈጣኖች ይሆናሉ።” (ኢሳይያስ 30:16) የይሁዳ ሰዎች መዳናቸው በይሖዋ ላይ ሳይሆን በፈጣን ፈረሶች የተመካ እንደሆነ አድርገው አስበዋል። (ዘዳግም 17:16፤ ምሳሌ 21:31) ይሁን እንጂ ነቢዩ ጠላቶቻቸው ስለሚያገኟቸው ይህ ትምክህታቸው ሕልም ብቻ እንደሆነ በመናገር መልስ ሰጥቷል። ቁጥራቸው የቱንም ያህል ትልቅ ቢሆን የሚያመጣው ለውጥ የለም። “ከአንድ ሰው ዛቻ የተነሣ ሺህ ሰዎች ይሸሻሉ፤ . . . ከአምስት ሰዎች ዛቻ የተነሣ ትሸሻላችሁ።” (ኢሳይያስ 30:17) የይሁዳ ሠራዊት ሽብር ላይ ስለሚወድቅ እፍኝ በማይሞሉ ጠላቶቻቸው ጩኸት ይሸሻል።a በመጨረሻ “በተራራ ራስ ላይ እንዳለ ምሰሶ፣ በኮረብታም ላይ እንዳለ ምልክት” ሆነው የሚተርፉት ጥቂት ቀሪዎች ብቻ ይሆናሉ። (ኢሳይያስ 30:17) ኢየሩሳሌም በ607 ከዘአበ ስትጠፋ ልክ በትንቢቱ መሠረት የተረፉት ጥቂት ቀሪዎች ብቻ ናቸው።—ኤርምያስ 25:8-11
-
-
ይሖዋን በመተማመን ተጠባበቁየኢሳይያስ ትንቢት—ለመላው የሰው ዘር የፈነጠቀ ብርሃን ጥራዝ 1
-
-
a ይሁዳ የታመነች ሆና ብትገኝ ኖሮ ነገሩ የተገላቢጦሽ ይሆን እንደነበር አትዘንጋ።—ዘሌዋውያን 26:7, 8
-