-
ዝሙት አዳሪዎቹ እህትማማቾችየይሖዋ ንጹሕ አምልኮ መልሶ ተቋቋመ!
-
-
ዝሙት አዳሪዎቹ እህትማማቾች
ሕዝቅኤል ምዕራፍ 23 የአምላክ ሕዝቦች በፈጸሙት ክህደት ምክንያት የተሰነዘረባቸውን ከባድ የውግዘት ቃል ይዟል። ይህ ምዕራፍ፣ ከምዕራፍ 16 ጋር በብዙ መንገዶች ይመሳሰላል። እንደ ምዕራፍ 16 ሁሉ ምዕራፍ 23ም ዝሙት አዳሪነትን እንደ ምሳሌ ይጠቀማል። ኢየሩሳሌምና ሰማርያ እንደ እህትማማቾች ተደርገው የተገለጹ ሲሆን ኢየሩሳሌም ታናሽ፣ ሰማርያ ደግሞ ታላቅ እንደሆነች ተገልጿል። ሁለቱም ምዕራፎች ታናሽየዋ ታላቅ እህቷን ተከትላ እንዴት ዝሙት አዳሪ እንደሆነች፣ በኋላ ግን ታላቋን በክፋትም ሆነ በብልግና እንዴት እንደበለጠቻት ይናገራሉ። በምዕራፍ 23 ላይ ይሖዋ ለሁለቱም እህትማማቾች ስም አውጥቶላቸዋል። ታላቅየዋ ኦሆላ ተብላ የተጠራች ሲሆን የአሥሩ ነገድ የእስራኤል መንግሥት ዋና ከተማ የነበረችውን ሰማርያን ታመለክታለች። ታናሽየዋ ደግሞ ኦሆሊባ የምትባል ሲሆን የይሁዳ ዋና ከተማ የሆነችውን ኢየሩሳሌምን ታመለክታለች።a—ሕዝ. 23:1-4
-
-
ዝሙት አዳሪዎቹ እህትማማቾችየይሖዋ ንጹሕ አምልኮ መልሶ ተቋቋመ!
-
-
a ስማቸው በራሱ የሚያስተላልፈው ትርጉም አለ። ኦሆላ የሚለው ስም “የእሷ [የአምልኮ] ድንኳን” የሚል ትርጉም አለው፤ ይህም እስራኤል በኢየሩሳሌም በሚገኘው የይሖዋ ቤተ መቅደስ ከመጠቀም ይልቅ የራሷን የአምልኮ ማዕከሎች ማቋቋሟን የሚያመለክት ስያሜ ሳይሆን አይቀርም። ኦሆሊባ ማለት ደግሞ “[የአምልኮ] ድንኳኔ በእሷ ውስጥ ነው” ማለት ነው። ኢየሩሳሌም የይሖዋ የአምልኮ ቤት የሚገኝባት ከተማ ነበረች።
-