-
“ሕያው ትሆናላችሁ”የይሖዋ ንጹሕ አምልኮ መልሶ ተቋቋመ!
-
-
“አጥንቶቹም እርስ በርስ መገጣጠም ጀመሩ”
10. (ሀ) ሕዝቅኤል 37:7, 8 የአምላክ ሕዝቦች ምን እንደሚሆኑ ይናገራል? (ለ) ፈሪሃ አምላክ የነበራቸው ግዞተኞች እምነታቸው ቀስ በቀስ እንዲያንሰራራ የረዳቸው ምን ሊሆን ይችላል?
10 በጥንት ጊዜ ይሖዋ ሕዝቦቹ ደረጃ በደረጃ ተመልሰው ሕያው እንደሚሆኑ ተንብዮ ነበር። (ሕዝ. 37:7, 8) ታዲያ ፈሪሃ አምላክ የነበራቸው ግዞተኞች፣ ወደ እስራኤል እንደሚመለሱ የተሰጣቸው ተስፋ እንደሚፈጸም ያላቸው እምነት ቀስ በቀስ እንዲያንሰራራ ያደረጉት ነገሮች የትኞቹ ናቸው? ተስፋቸው እንዲያንሰራራ ካደረጉት ነገሮች መካከል አንዱ ቀደም ሲል የነበሩ ነቢያት የተናገሩት ትንቢት መሆን አለበት። ለምሳሌ ኢሳይያስ “የተቀደሰ ዘር” ማለትም አይሁዳውያን ቀሪዎችን ያቀፈ ቡድን ወደ ምድሪቱ እንደሚመለስ ተንብዮ ነበር። (ኢሳ. 6:13፤ ኢዮብ 14:7-9) በተጨማሪም ሕዝቅኤል የጻፋቸው ስለ መልሶ መቋቋም የሚገልጹ በርካታ ትንቢቶች ተስፋቸውን አለምልመውላቸው እንደሚሆን አያጠራጥርም። ከዚህም ሌላ እንደ ነቢዩ ዳንኤል ያሉ ታማኝ ሰዎች በባቢሎን መኖራቸውና የባቢሎን ከተማ በ539 ዓ.ዓ. በአስደናቂ ሁኔታ መውደቋ ግዞተኞቹ ወደ አገራቸው እንደሚመለሱ የነበራቸውን ተስፋ አጠናክሮት መሆን አለበት።
11, 12. (ሀ) ‘የአምላክ እስራኤል’ ቀስ በቀስ መልሶ ሕያው የሆነው እንዴት ነበር? (“ንጹሕ አምልኮ ቀስ በቀስ መልሶ ተቋቋመ” የሚለውን ሣጥን ተመልከት።) (ለ) በሕዝቅኤል 37:10 ላይ ከሚገኘው መግለጫ ጋር በተያያዘ ምን ጥያቄ ይነሳል?
11 ‘የአምላክ እስራኤል’ ማለትም የቅቡዓን ክርስቲያኖች ጉባኤስ ቀስ በቀስ መልሶ ሕያው የሆነው እንዴት ነው? በሞት የተመሰለው የግዞት ዘመን ከጀመረ ከበርካታ መቶ ዓመታት በኋላ ፈሪሃ አምላክ ያላቸው ግለሰቦች ለእውነተኛው አምልኮ ጥብቅና መቆም ሲጀምሩ “የሚንኮሻኮሽ ድምፅ” የተሰማ ያህል ነበር። ለምሳሌ ያህል በ16ኛው መቶ ዘመን ዊልያም ቲንደል መጽሐፍ ቅዱስን ወደ እንግሊዝኛ ተረጎመ። በዚህ ጊዜ ተራው ሕዝብ መጽሐፍ ቅዱስን ማንበብ የሚችልበት አጋጣሚ በማግኘቱ የሮም ካቶሊክ ቀሳውስት ተበሳጩ። በመሆኑም ቲንደል ተገደለ። ያም ሆኖ ሌሎች ደፋር ግለሰቦች መጽሐፍ ቅዱስን ወደ ሌሎች ቋንቋዎች መተርጎማቸውን ቀጠሉ፤ በዚህ መንገድ በጨለማው ዓለም ውስጥ ቀስ በቀስ መንፈሳዊ ብርሃን መፈንጠቅ ጀመረ።
-
-
ንጹሕ አምልኮ ቀስ በቀስ መልሶ ተቋቋመየይሖዋ ንጹሕ አምልኮ መልሶ ተቋቋመ!
-
-
“የሚንኮሻኮሽ ድምፅ”
ዊልያም ቲንደል እና ሌሎች ሰዎች መጽሐፍ ቅዱስን ወደ እንግሊዝኛና ወደ ሌሎች ቋንቋዎች ተረጎሙ
-