-
“ሕያው ትሆናላችሁ”የይሖዋ ንጹሕ አምልኮ መልሶ ተቋቋመ!
-
-
9. በጥንቶቹ እስራኤላውያን ላይ በደረሰውና “በአምላክ እስራኤል” ላይ በደረሰው ነገር መካከል ምን ተመሳሳይነት አለ?
9 የሕዝቅኤልን ትንቢቶች ጨምሮ ስለ እስራኤል መልሶ መቋቋም የሚናገሩት ትንቢቶች በወቅቱ ከነበራቸው ፍጻሜ በተጨማሪ ሌላም የላቀ ፍጻሜ አላቸው። (ሥራ 3:21) በጥንት ጊዜ የእስራኤል ብሔር ‘እንደተገደለና’ በምሳሌያዊ ሁኔታ ለበርካታ ዓመታት በድን ሆኖ እንደቆየ ሁሉ ‘የአምላክ እስራኤል’ የተባለው የቅቡዓን ክርስቲያኖች ጉባኤም በምሳሌያዊ ሁኔታ ተገድሎ ለረጅም ዓመታት ከሞት በማይተናነስ ግዞት ሥር ኖሯል። (ገላ. 6:16) የቅቡዓን ክርስቲያኖች ጉባኤ በምርኮ የቆየበት ጊዜ በጣም ረጅም ከመሆኑ የተነሳ የነበሩበት መንፈሳዊ ሁኔታ ‘በጣም ከደረቁ’ አጥንቶች ጋር የሚመሳሰል ሆኖ ነበር። (ሕዝ. 37:2) ከዚህ በፊት በነበረው ምዕራፍ ላይ እንደተብራራው የቅቡዓን ክርስቲያኖች ጉባኤ በምርኮ የተያዘው በሁለተኛው መቶ ዘመን ዓ.ም. ሲሆን ኢየሱስ ስለ ስንዴውና ስለ እንክርዳዱ የተናገረው ምሳሌ እንደሚያመለክተው ይህ ሁኔታ ለብዙ መቶ ዓመታት ዘልቋል።—ማቴ. 13:24-30
-