ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት | ሕዝቅኤል 1-5 ሕዝቅኤል የአምላክን መልእክት ማወጅ ያስደስተው ነበር ሕዝቅኤል፣ ይሖዋ አንድ ጥቅልል ሲሰጠው በራእይ ተመልክቷል፤ ከዚያም ጥቅልሉን እንዲበላው ይሖዋ ነግሮታል። የዚህ ራእይ ትርጉም ምንድን ነው? 2:9–3:2 ሕዝቅኤል የአምላክ መልእክት ወደ ውስጡ ጠልቆ እንዲገባ ማድረግ ነበረበት። በጥቅልሉ ላይ በተጻፈው መልእክት ላይ ማሰላሰሉ ስሜቱ በጥልቅ እንዲነካ የሚያደርግ ሲሆን ይህም መልእክቱን እንዲናገር ያነሳሳዋል 3:3 ሕዝቅኤል ጥቅልሉ የጣፈጠው ለተሰጠው የሥራ ምድብ አዎንታዊ አመለካከት ስለነበረው ነው መጸለይ፣ መጽሐፍ ቅዱስን በጥልቀት ማጥናትና ማሰላሰል የሚጠቅመኝ እንዴት ነው? ለስብከቱ ሥራ አዎንታዊ አመለካከት ማዳበር የምችለው እንዴት ነው?