-
ከዳንኤል ምሳሌ ተማሩመጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)—2023 | ነሐሴ
-
-
6. ዳንኤል ደፋር እንዲሆን የረዳው ምን ሊሆን ይችላል?
6 ዳንኤል በመላ ሕይወቱ ደፋር እንዲሆን የረዳው ምን ሊሆን ይችላል? በልጅነቱ ከእናቱና ከአባቱ ምሳሌ እንደተማረ ምንም ጥያቄ የለውም። እናቱና አባቱ፣ ይሖዋ ለእስራኤላውያን ወላጆች የሰጠውን መመሪያ በመከተል ለልጃቸው የአምላክን ሕግ አስተምረውት መሆን አለበት። (ዘዳ. 6:6-9) ዳንኤል እንደ አሥርቱ ትእዛዛት ያሉትን የሕጉን መሠረታዊ ክፍሎች ብቻ ሳይሆን ዝርዝር ነገሮችንም ያውቅ ነበር፤ ለምሳሌ እስራኤላውያን መብላት የሚፈቀድላቸውንና የማይፈቀድላቸውን ምግብ ለይቶ ያውቃል።b (ዘሌ. 11:4-8፤ ዳን. 1:8, 11-13) በተጨማሪም ዳንኤል የአምላክን ሕዝቦች ታሪክ ተምሯል፤ እስራኤላውያን የይሖዋን መሥፈርቶች ሳይከተሉ በቀሩበት ወቅት ምን እንደደረሰባቸው ያውቃል። (ዳን. 9:10, 11) ከዚህም ሌላ በሕይወት ዘመኑ ያጋጠሙት ተሞክሮዎች ይሖዋና ኃያላን መላእክቱ እንደሚደግፉት እርግጠኛ እንዲሆን አድርገውታል።—ዳን. 2:19-24፤ 10:12, 18, 19
-
-
ከዳንኤል ምሳሌ ተማሩመጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)—2023 | ነሐሴ
-
-
b ዳንኤል የባቢሎናውያንን ምግብ ለመብላት ፈቃደኛ ያልሆነው በሚከተሉት ሦስት ምክንያቶች የተነሳ ሊሆን ይችላል፦ (1) የሚበሉት በሕጉ የተከለከሉትን እንስሳት ሥጋ ሊሆን ይችላል። (ዘዳ. 14:7, 8) (2) ሥጋው በተገቢው መንገድ ደሙ ያልፈሰሰ ሊሆን ይችላል። (ዘሌ. 17:10-12) (3) ምግቡን መብላቱ የጣዖት አምልኮ ተካፋይ እንደሆነ ሊያስቆጥረው ይችላል።—ከዘሌዋውያን 7:15፤ 1 ቆሮንቶስ 10:18, 21, 22 ጋር አወዳድር።
-