-
‘የሰሜኑ ንጉሥ’ በፍጻሜው ዘመንመጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)—2020 | ግንቦት
-
-
13. በ1930ዎቹ ዓመታትና በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ወቅት የሰሜኑ ንጉሥ ምን አድርጓል?
13 ከዚያም በ1930ዎቹ ዓመታት፣ በተለይም በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ወቅት የሰሜኑ ንጉሥ የአምላክን ሕዝቦች ያለምንም ርኅራኄ አሳድዷል። የናዚ ፓርቲ ጀርመንን ከተቆጣጠረ በኋላ ሂትለርና ተከታዮቹ በአምላክ ሕዝቦች ሥራ ላይ እገዳ ጥለዋል። ተቃዋሚዎች፣ በመቶዎች የሚቆጠሩ የይሖዋ አገልጋዮችን ገድለዋል፤ እንዲሁም በሺዎች የሚቆጠሩትን ወደ ማጎሪያ ካምፖች ልከዋል። ዳንኤል ይህ እንደሚሆን አስቀድሞ ተናግሮ ነበር። የሰሜኑ ንጉሥ፣ የአምላክ አገልጋዮች ይሖዋን በሕዝብ ፊት ለማወደስ በሚያከናውኑት ሥራ ላይ ከፍተኛ ገደብ በመጣሉ ‘መቅደሱን አርክሷል’ እንዲሁም ‘የዘወትሩን መሥዋዕት አስቀርቷል።’ (ዳን. 11:30ለ, 31ሀ) እንዲያውም የጀርመን መሪ የነበረው ሂትለር የአምላክ ሕዝቦችን ከአገሪቱ ጠራርጎ እንደሚያጠፋ ዝቶ ነበር።
-
-
‘የሰሜኑ ንጉሥ’ በፍጻሜው ዘመንመጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)—2020 | ግንቦት
-
-
ያልተለመደ ትብብር
17. ‘ጥፋት የሚያመጣው ርኩስ ነገር’ ምንድን ነው?
17 የሰሜኑ ንጉሥና የደቡቡ ንጉሥ የተባበሩበት አንድ ቁልፍ ጉዳይ አለ፤ ይህም ‘ጥፋት የሚያመጣውን ርኩስ ነገር’ ማቋቋም ነው። (ዳን. 11:31) “ርኩስ ነገር” የተባለው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ነው።
18. የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት “ርኩስ ነገር” ተብሎ የተገለጸው ለምንድን ነው?
18 የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት “ርኩስ ነገር” ተብሎ የተገለጸው የአምላክ መንግሥት ብቻ ሊያከናውን የሚችለውን ነገር እንደሚያደርግ ይኸውም ዓለም አቀፍ ሰላም እንደሚያመጣ ስለሚናገር ነው። ይህ ርኩስ ነገር ‘ጥፋት እንደሚያመጣ’ ትንቢቱ አክሎ ተናግሯል፤ እንዲህ የተባለው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት፣ ሁሉንም የሐሰት ሃይማኖቶች በማጥፋት ረገድ ቁልፍ ሚና ስለሚጫወት ነው።—“በፍጻሜው ዘመን የተነሱ ተቀናቃኝ ነገሥታት” የሚለውን ሰንጠረዥ ተመልከት።
-