-
‘የአምላክ ታላቅ ሥራ’ ለተግባር ያነሳሳልመጠበቂያ ግንብ—2002 | ነሐሴ 1
-
-
ለተግባር ተንቀሳቀሱ!
4. በ33 እዘአ በዋለው የጰንጠቆስጤ ዕለት ፍጻሜውን ያገኘው የትኛው የኢዩኤል ትንቢት ነው?
4 በኢየሩሳሌም ተገኝተው መንፈስ ቅዱስ የተቀበሉት ደቀ መዛሙርት በዚያን ዕለት ጠዋት በዓሉን ለማክበር ከተሰበሰቡት ሰዎች አንስተው የመዳንን ምሥራች ለሌሎች ለማካፈል ጊዜ አላጠፉም ነበር። የስብከት እንቅስቃሴያቸው የባቱኤል ልጅ ኢዩኤል ከስምንት መቶ ዘመናት በፊት የመዘገበው አስደናቂ ትንቢት ፍጻሜውን እንዲያገኝ አስችሏል:- “መንፈሴን በሥጋ ለባሽ ሁሉ ላይ አፈስሳለሁ፤ ወንዶችና ሴቶች ልጆቻችሁም ትንቢት ይናገራሉ፣ ሽማግሌዎቻችሁም ሕልምን ያልማሉ፣ ጐበዞቻችሁም ራእይ ያያሉ፤ ደግሞም በዚያ ወራት በወንዶችና በሴቶች ባሪያዎች ላይ መንፈሴን አፈስሳለሁ። ታላቁና የሚያስፈራው የእግዚአብሔር ቀን ሳይመጣ።”—ኢዩኤል 1:1፤ 2:28, 29, 31፤ ሥራ 2:17, 18, 20
5. በመጀመሪያው መቶ ዘመን የነበሩ ክርስቲያኖች ትንቢት የተናገሩት በምን መንገድ ነው? (የግርጌ ማስታወሻውን ተመልከት።)
5 እንዲህ ሲባል ታዲያ አምላክ እንደ ዳዊት፣ ኢዩኤልና ዲቦራ የመሳሰሉ ወንዶችና ሴቶች ነቢያትን አስነስቶ ወደፊት የሚከናወኑ ነገሮችን እንዲተነብዩ ያደርጋል ማለት ነው? አይደለም። ክርስቲያን ‘ወንዶችና ሴቶች ልጆች እንዲሁም ባሪያዎች’ ትንቢት ይናገራሉ ሲባል ይሖዋ እስካሁን ድረስ ያደረጋቸውንና ወደፊትም የሚያደርጋቸውን ‘ታላላቅ ሥራዎች’ እንዲያውጁ በእሱ መንፈስ ይንቀሳቀሳሉ ማለት ነው። በዚህም መንገድ የልዑል ቃል አቀባይ ሆነው ያገለግላሉ።a ሆኖም የሕዝቡ ምላሽ ምን ነበር?—ዕብራውያን 1:1, 2
-