-
የይሖዋ የፍርድ ቀን ቀርቧል!መጠበቂያ ግንብ—2001 | የካቲት 15
-
-
11. የሶፎንያስ 1:8-11 መሠረታዊ ትርጉም ምንድን ነው?
11 የይሖዋን ቀን በማስመልከት ሶፎንያስ 1:8-11 የሚከተለውን ይጨምራል:- “በእግዚአብሔርም መሥዋዕት ቀን አለቆችንና የንጉሥን ልጆች እንግዳ ልብስ የሚለብሱትንም ሁሉ እቀጣለሁ። በዚያም ቀን በመድረኩ ላይ የሚዘልሉትን፣ የጌታቸውን ቤት ዓመፃንና ሽንገላን የሚሞሉትን እቀጣለሁ። በዚያ ቀን፣ ይላል እግዚአብሔር፣ ከዓሣው በር የጩኸት ድምፅ፣ ከከተማውም በሁለተኛው ክፍል ውካታ፣ ከኮረብቶቹም ታላቅ ሽብር ይሆናል። እናንተ በመክቴሽ የምትኖሩ ሆይ፣ የከነዓን ሕዝብ ሁሉ ጠፍተዋልና፣ ብርም የተሸከሙ ሁሉ ተቈርጠዋልና አልቅሱ።”
-
-
የይሖዋ የፍርድ ቀን ቀርቧል!መጠበቂያ ግንብ—2001 | የካቲት 15
-
-
13. ከሶፎንያስ ትንቢት ጋር በሚስማማ መንገድ ባቢሎናውያን ኢየሩሳሌምን ሲያጠቁ ምን መፈጸም ነበረበት?
13 ይሁዳ ለፍርድ የምትቀርብበት ‘ያ ቀን’ ይሖዋ ክፋትን ለማስወገድና የበላይነቱን ለማረጋገጥ በጠላቶቹ ላይ የቅጣት እርምጃ ከሚወስድበት የይሖዋ ቀን ጋር ተመሳሳይ ይሆናል። ባቢሎናውያን ኢየሩሳሌምን በሚያጠቁበት ጊዜ ከዓሣ በር ጩኸት ይመጣል። ይህ በር እንዲህ ያለ ስያሜ የተሰጠው ዓሣ ከሚሸጥበት ገበያ አጠገብ ይገኝ ስለነበር ሳይሆን አይቀርም። (ነህምያ 13:16) የባቢሎን ጭፍሮች ሁለተኛው ክፍል ተብሎ ይጠራ ወደነበረው አካባቢ ይገባሉ። “ከኮረብቶችም ታላቅ ሽብር” የተባለውም ባቢሎናውያኑ እየገሰገሱ ሲመጡ የሚሰማውን ድምፅ የሚያመለክት ሊሆን ይችላል። የመክቴሽ ምናልባትም የላይኛው ታይሮፕያን ሸለቆ ነዋሪዎች ‘ያለቅሳሉ።’ የሚያለቅሱት ለምንድን ነው? ‘ብር የሚሸከሙትን’ ጨምሮ ማንኛውም የንግድ እንቅስቃሴ ስለሚቆም ነው።
-