-
“ይሖዋ አምላክህን ብቻ አምልክ”የይሖዋ ንጹሕ አምልኮ መልሶ ተቋቋመ!
-
-
3, 4. (ሀ) ሰይጣን የመጀመሪያዎቹን ሁለት ፈተናዎች የጀመረው በየትኞቹ ቃላት ነው? ይህን ያለውስ ኢየሱስ ስለ ምን ነገር ጥርጣሬ እንዲያድርበት ለማድረግ ፈልጎ ሊሆን ይችላል? (ለ) በዛሬው ጊዜ ሰይጣን ተመሳሳይ ዘዴዎችን የሚጠቀመው እንዴት ነው?
3 ማቴዎስ 4:1-7ን አንብብ። ሰይጣን የመጀመሪያዎቹን ሁለት ፈተናዎች ያቀረበው “የአምላክ ልጅ ከሆንክ” የሚሉትን ተንኮል ያዘሉ ቃላት በማስቀደም ነበር። ሰይጣን ይህን ያለው ኢየሱስ የአምላክ ልጅ መሆኑን ተጠራጥሮ ነው? በፍጹም። ከአምላክ ልጆች አንዱ የነበረው ይህ ዓመፀኛ መልአክ ኢየሱስ የአምላክ የበኩር ልጅ መሆኑን ጠንቅቆ ያውቃል። (ቆላ. 1:15) ሰይጣን፣ ኢየሱስ በተጠመቀበት ወቅት ይሖዋ “በጣም የምደሰትበት የምወደው ልጄ ይህ ነው” በማለት ከሰማይ ሲናገር እንደሰማም ምንም ጥርጥር የለውም። (ማቴ. 3:17) ምናልባትም የሰይጣን ዓላማ ኢየሱስ፣ አባቱ እምነት የሚጣልበትና ለእሱ ከልብ የሚያስብ መሆኑን እንዲጠራጠር ማድረግ ሊሆን ይችላል። ዲያብሎስ ለኢየሱስ ባቀረበው የመጀመሪያ ፈተና ላይ “የአምላክ ልጅ ከሆንክ እስቲ እነዚህ ድንጋዮች ዳቦ እንዲሆኑ እዘዝ” ሲል፣ በተዘዋዋሪ መንገድ ‘የአምላክ ልጅ አይደለህ? ታዲያ በዚህ ጠፍ ምድረ በዳ ውስጥ አባትህ የማይመግብህ ለምንድን ነው?’ ማለቱ ነበር። በሁለተኛው ፈተና ላይ ደግሞ ወደ ቤተ መቅደሱ አናት ወስዶ “የአምላክ ልጅ ከሆንክ እስቲ ራስህን ወደ ታች ወርውር” ሲለው ‘እንግዲህ የአምላክ ልጅ ነኝ ብለሃል፤ ታዲያ አባትህ በእርግጥ እንደሚጠብቅህ ትተማመናለህ?’ ያለው ያህል ነበር።
-
-
“ይሖዋ አምላክህን ብቻ አምልክ”የይሖዋ ንጹሕ አምልኮ መልሶ ተቋቋመ!
-
-
5. ኢየሱስ ለመጀመሪያዎቹ ሁለት ፈተናዎች ምላሽ የሰጠው እንዴት ነው?
5 ኢየሱስ ለመጀመሪያዎቹ ሁለት ፈተናዎች ምላሽ የሰጠው እንዴት እንደሆነ እስቲ እንመልከት። አባቱ እንደሚወደው ቅንጣት ታክል እንኳ አልተጠራጠረም፤ እንዲሁም በአባቱ ላይ ሙሉ እምነት ነበረው። ኢየሱስ በመንፈስ መሪነት የተጻፈውን የአባቱን ቃል በመጥቀስ ያለአንዳች ማመንታት ሰይጣንን ተቃውሟል። የጠቀሳቸው ጥቅሶች ይሖዋ የሚለውን መለኮታዊ ስም የያዙ ናቸው፤ ይህም ተገቢ ነው። (ዘዳ. 6:16፤ 8:3) ደግሞስ አምላክ የገባውን ቃል እንደሚፈጽም ዋስትና የሚሰጠውን ይሖዋ የሚለውን ስም ከመጠቀም የተሻለ በአባቱ ላይ እምነት እንዳለው የሚያሳይ ምን ሌላ መንገድ ይኖራል?a
-