-
“ሁልጊዜ ከእናንተ ጋር ነኝ”መጠበቂያ ግንብ—2013 | ሐምሌ 15
-
-
16, 17. (ሀ) ኢየሱስ በምሳሌው ላይ የጠቀሰው የመጨረሻ ክንውን ምንድን ነው? (ለ) ይህ ክንውን የሚፈጸመው ወደፊት ነው የምንለው ለምንድን ነው?
16 አምስተኛው ደግሞ ደምቆ ማብራት ነው። ኢየሱስ ምሳሌውን የደመደመው እንደሚከተለው በማለት ነው፦ “በዚያ ጊዜ ጻድቃን በአባታቸው መንግሥት እንደ ፀሐይ ደምቀው ያበራሉ።” (ማቴ. 13:43) ይህ የሚሆነው መቼና የት ነው? ይህ ትንቢት የሚፈጸመው ገና ወደፊት ነው። ኢየሱስ እዚህ ላይ የገለጸው በአሁኑ ጊዜ በምድር ላይ እየተከናወነ ያለን ነገር ሳይሆን ወደፊት በሰማይ ላይ የሚፈጸምን ነገር ነው።f እዚህ መደምደሚያ ላይ እንድንደርስ ያደረጉንን ሁለት ምክንያቶች እስቲ እንመልከት።
17 በመጀመሪያ “መቼ” ለሚለው ጥያቄ መልስ ለማግኘት እንሞክር። ኢየሱስ “በዚያ ጊዜ ጻድቃን . . . ደምቀው ያበራሉ” ብሏል። “በዚያ ጊዜ” የሚለው ሐረግ የሚያመለክተው ከዚህ ጥቅስ በፊት የተናገረውን ይኸውም ‘እንክርዳዱ ወደ እቶን እሳት የሚጣልበትን’ ጊዜ እንደሆነ የተረጋገጠ ነው። ይህ የሚሆነው ደግሞ በታላቁ መከራ የመጨረሻ ምዕራፍ ላይ ነው። እንግዲያው ቅቡዓኑ ‘ደምቀው የሚያበሩትም’ ከላይ በተጠቀሰው ጊዜ ላይ መሆን ይኖርበታል። ሁለተኛው ጥያቄ “የት” የሚለው ነው። ኢየሱስ ጻድቃን በአምላክ “መንግሥት እንደ ፀሐይ ደምቀው ያበራሉ” ብሏል። ይህ ምን ማለት ነው? የታላቁ መከራ የመጀመሪያ ምዕራፍ ካለፈ በኋላ በምድር ላይ የሚገኙት ሁሉም ታማኝ ቅቡዓን ወዲያውኑ የመጨረሻው ማኅተም ይደረግባቸዋል። ከዚያም ኢየሱስ ስለ ታላቁ መከራ በተናገረው ትንቢት ላይ እንደገለጸው ቅቡዓኑ ወደ ሰማይ ይሰበሰባሉ። (ማቴ. 24:31) በዚያም “በአባታቸው መንግሥት” ደምቀው ያበራሉ፤ ከአርማጌዶን ጦርነት ብዙም ሳይቆይ ‘በበጉ ሠርግ’ ላይ ደስተኛ የኢየሱስ ሙሽራ ሆነው ይቀርባሉ።—ራእይ 19:6-9
-
-
“ሁልጊዜ ከእናንተ ጋር ነኝ”መጠበቂያ ግንብ—2013 | ሐምሌ 15
-
-
f አንቀጽ 16፦ ዳንኤል 12:3 “ጥበበኞች [ቅቡዓን ክርስቲያኖች] እንደ ሰማይ ጸዳል፣ . . . ለዘላለም ይደምቃሉ” ይላል። ቅቡዓኑ በምድር ላይ እያሉ ይህን የሚያደርጉት በስብከቱ ሥራ በመካፈል ነው። ይሁንና ማቴዎስ 13:43 የሚገልጸው በአምላክ መንግሥት ውስጥ በሰማይ ደምቀው ስለሚያበሩበት ጊዜ ነው። ከዚህ ቀደም ሁለቱም ጥቅሶች ስለ አንድ ነገር ይኸውም ስለ ስብከቱ ሥራ እንደሚያመለክቱ አድርገን እናስብ ነበር።
-