-
“ማንም ሰው እንደዚህ ተናግሮ አያውቅም”“ተከታዬ ሁን”
-
-
9 በአንድ ወቅት ግብር ሰብሳቢዎች ጴጥሮስን፣ ኢየሱስ የቤተ መቅደሱን ግብር ይከፍል እንደሆነ ጠየቁት።c ጴጥሮስም “ይከፍላል” ሲል ወዲያውኑ መለሰላቸው። በኋላ ላይ ኢየሱስ፣ ጴጥሮስ በጉዳዩ ላይ እንዲያስብበት እንዲህ ሲል ጠየቀው፦ “ስምዖን ምን ይመስልሃል? የምድር ነገሥታት ቀረጥ ወይም ግብር የሚቀበሉት ከማን ነው? ከልጆቻቸው ወይስ ከሌሎች?” ጴጥሮስም “ከሌሎች” ብሎ መለሰ። በዚህ ጊዜ ኢየሱስ “እንግዲያው ልጆቹ ግብር ከመክፈል ነፃ ናቸው” አለው። (ማቴዎስ 17:24-27) የነገሥታት ቤተሰቦች ከግብር ነፃ መሆናቸው ይታወቅ ስለነበር ጴጥሮስ ጥያቄዎቹ የያዙትን ቁም ነገር እንደተገነዘበ ጥርጥር የለውም። ኢየሱስ በቤተ መቅደሱ ውስጥ የሚመለከው ሰማያዊ ንጉሥ አንድያ ልጅ እንደመሆኑ መጠን ግብር የመክፈል ግዴታ አልነበረበትም። ኢየሱስ ጥያቄዎችን እንዴት በዘዴ እንደተጠቀመ ልብ አልክ? ለጴጥሮስ መልሱን በቀጥታ ከመንገር ይልቅ ጴጥሮስ ትክክለኛው መደምደሚያ ላይ እንዲደርስ ረድቶታል፤ ምናልባትም ለወደፊቱ መልስ ከመስጠቱ በፊት ቆም ብሎ ማሰብ እንዳለበትም አስገንዝቦታል።
-
-
“ማንም ሰው እንደዚህ ተናግሮ አያውቅም”“ተከታዬ ሁን”
-
-
c አይሁዳውያን በየዓመቱ ሁለት ድራክማ (የሁለት ቀን ደሞዝ ይሆናል) ለቤተ መቅደስ ግብር እንዲከፍሉ ይጠበቅባቸው ነበር። አንድ የማመሣከሪያ ጽሑፍ እንዲህ ብሏል፦ “ይህ ግብር በዋነኝነት የሚውለው በየዕለቱ የሚቀርበውን የሚቃጠል መሥዋዕትና በሕዝቡ ስም የሚቀርቡትን የሁሉንም መሥዋዕቶች ወጪ ለመሸፈን ነው።”
-