-
ፍቅርንቁ!—2018 | ቁጥር 1
-
-
ኢየሱስ ክርስቶስ ትዳርን ስኬታማ ለማድረግ የሚረዱ ጠቃሚ መመሪያዎችን ሰጥቷል። ለምሳሌ እንዲህ በማለት ተናግሯል፦ “‘ሰው ከአባቱና ከእናቱ ይለያል፤ ከሚስቱም ጋር ይጣበቃል፤ ሁለቱም አንድ ሥጋ ይሆናሉ’ . . . ስለዚህ አምላክ ያጣመረውን ማንም ሰው አይለያየው።” (ማቴዎስ 19:5, 6) ከዚህ ጥቅስ ላይ ቢያንስ ሁለት ጠቃሚ መመሪያዎችን ማግኘት እንችላለን።
-
-
ፍቅርንቁ!—2018 | ቁጥር 1
-
-
“አምላክ ያጣመረው።” ጋብቻ ቅዱስ ጥምረት ነው። ይህን ሐቅ የሚገነዘቡ ባልና ሚስት ትዳራቸውን ለማጠናከር ጥረት ያደርጋሉ። በትዳራቸው ውስጥ ችግር ሲያጋጥማቸው ትዳሩን የሚያፈርሱበት ሰበብ አይፈላልጉም። በመካከላቸው ያለው ፍቅር ጠንካራና ችግሮችን ተቋቁሞ ማለፍ የሚችል ነው። እንዲህ ዓይነቱ ፍቅር “ሁሉን ችሎ [ስለሚያልፍ]” ባለትዳሮች የሚያጋጥማቸውን ችግር በመፍታት ሰላምና አንድነታቸውን ጠብቀው እንዲቀጥሉ ይረዳቸዋል።
-