-
በፍርድ ዙፋኑ ፊት የምትቀርበው እንዴት ነው?መጠበቂያ ግንብ—1995 | ጥቅምት 15
-
-
20, 21. የኢየሱስ ሐዋርያት የጠየቁት ዘመናችንን የሚመለከት ጥያቄ የትኛው ነው? ይህስ ወደ የትኛው ጥያቄ ይመራል?
20 ኢየሱስ ከመሞቱ ከጥቂት ጊዜ በፊት ሐዋርያቱ “‘እነዚህ ነገሮች መቼ ይሆናሉ? የመገኘትህና የነገሮች ሥርዓት መደምደሚያ ምልክት ምን ይሆናል?’ ብለው ጠየቁት።” (ማቴዎስ 24:3 አዓት) ኢየሱስ ‘መጨረሻው ከመምጣቱ’ በፊት በምድር ላይ የሚፈጸሙትን በጣም አስፈላጊ የሆኑ ሁኔታዎች አስቀድሞ ተናገረ። ይህ መጨረሻ ከመምጣቱ ጥቂት ቀደም ብሎ ብሔራት “የሰው ልጅን በኃይልና በብዙ ክብር በሰማይ ደመና ሲመጣ ያዩታል።”—ማቴዎስ 24:14, 29, 30
21 የሰው ልጅ በክብሩ በሚመጣበት ጊዜ በእነዚህ ብሔራት ውስጥ የሚገኙ ሰዎች ምን ዋጋ ይቀበላሉ? “የሰው ልጅ በከብሩ በሚመጣበት ጊዜ ከእርሱም ጋር ቅዱሳን መላእክቱ ሁሉ፣ በዚያን ጊዜ በክብሩ ዙፋን ይቀመጣል” በማለት ከሚጀምረው ስለ በጎችና ፍየሎች ከሚናገረው ምሳሌ መልሱን ለማግኘት እንሞክር።—ማቴዎስ 25:31, 32
22, 23. የበጎቹና የፍየሎቹ ምሳሌ በ1914 መፈጸም አለመጀመሩን የሚያመለክቱት የትኞቹ ነጥቦች ናቸው?
22 ኢየሱስ በ1914 በንጉሣዊ ሥልጣኑ ላይ እንደ ተቀመጠ ከብዙ ጊዜ በፊት ተረድተን ነበር፤ ታዲያ ይህ ምሳሌ ከዚያን ጊዜ ጀምሮ በመፈጸም ላይ ነውን? ማቴዎስ 25:34 ኢየሱስን እንደ ንጉሥ አድርጎ ስለሚገልጸው ይህ ምሳሌ ከ1914 ጀምሮ መፈጸም ጀምሯል ብሎ ማሰብ ምክንያታዊ ነው። ይሁን እንጂ ከዚያ ጊዜ በኋላ ወዲያውኑ የተሰጠው ፍርድ ምን ነበር? “በአሕዛብ ሁሉ” ላይ ፍርድ አልተሰጠም። ከዚህ ይልቅ ‘የእግዚአብሔር ቤት’ ነን በሚሉት ላይ ትኩረቱን አድርጓል። (1 ጴጥሮስ 4:17) ከሚልክያስ 3:1–3 ጋር በሚስማማ መንገድ ኢየሱስ እንደ የይሖዋ መልእክተኛ በመሆን በምድር ላይ በቀሩት ቅቡዓን ክርስቲያኖች ላይ ፍርድ በመስጠት ምርመራ አካሂዷል። በተጨማሪም በሐሰት “የእግዚአብሔር ቤት” ነኝ በምትለዋ በሕዝበ ክርስትና ላይ ፍርድ የሚሰጥበት ጊዜ ነበር።c (ራእይ 17:1, 2፤ 18:4–8) ይሁን እንጂ በዚያን ጊዜ ወይም ከዚያ ጊዜ ጀምሮ ኢየሱስ አሕዛብን ሁሉ በጎችና ፍየሎች ናችሁ በማለት የመጨረሻ ፍርድ ለመስጠት እንደተቀመጠ የሚያሳይ ምንም ማስረጃ የለም።
23 ኢየሱስ በምሳሌው ውስጥ የሚያከናውነውን ተግባር ከመረመርን በመጨረሻ በአሕዛብ ሁሉ ላይ ሲፈርድ እንመለከተዋለን። ምሳሌው ባለፉት አሥርተ ዓመታት የሞቱት ሰዎች ሁሉ ዘላለማዊ ሞት ወይም ሕይወት እየተፈረደባቸው ወይም እየተፈረደላቸው ይህ ፍርድ ለብዙ ዓመታት እንደሚቀጥል አያመለክትም። በቅርብ ዓመታት የሞቱ አብዛኞቹ ሰዎች ወደ ሰው ልጆች ተራ መቃብር የሄዱ ይመስላል። (ራእይ 6:8፤ 20:13) ሆኖም ምሳሌው ኢየሱስ በሕይወት የሚኖሩትንና የፍርድ ውሳኔውን የሚቀበሉትን “አሕዛብን ሁሉ” የሚዳኝበትን ጊዜ ይገልጻል።
24. የበጎቹና የፍየሎቹ ምሳሌ ፍጻሜውን የሚያገኘው መቼ ነው?
24 በሌላ አባባል ይህ ምሳሌ የሰው ልጅ በክብሩ የሚመጣበትን የወደፊት ጊዜ ያመለክታል። በዚያን ጊዜ በሕይወት በሚኖሩ ሰዎች ላይ ለመፍረድ ይቀመጣል። የሚሰጠው ፍርድ ባሳዩት ባሕርይ ላይ የተመሠረተ ይሆናል። በዚያን ጊዜ ‘በጻድቁና በኃጢአተኛው መካከል ያለው ልዩነት’ በግልጽ ይታያል። (ሚልክያስ 3:18) ፍርዱ የሚሰጠውም ሆነ የሚፈጸመው በአንድ በተወሰነ ጊዜ ውስጥ ይሆናል። በዚያን ጊዜ ኢየሱስ በግለሰቦች ላይ በሚታየው ነገር መሠረት ትክክለኛ የፍርድ ውሳኔዎችን ያስተላልፋል።—በተጨማሪም 2 ቆሮንቶስ 5:10ን ተመልከት።
25. የሰው ልጅ በክብራማ ዙፋን መቀመጡን በተመለከተ ማቴዎስ 25:31 የሚገልጸው ምንድን ነው?
25 ይህም ማለት በማቴዎስ 25:31 ላይ እንደ ተገለጸው ኢየሱስ ‘በክብሩ ዙፋን ላይ ተቀምጦ’ የሚሰጠው ፍርድ ይህ ኃያል ንጉሥ ወደፊት በአሕዛብ ላይ ፍርድ ለመስጠትና ያን ፍርድ ለማስፈጸም የሚቀመጥበትን ጊዜ ያመለክታል። አዎን፣ በማቴዎስ 25:31–33, 46 ላይ ኢየሱስን በተመለከተ የተገለጸው የፍርድ ትዕይንት በመግዛት ላይ ያለው በዘመናት የሸመገለው ንጉሥ የዳኝነት ተግባሩን ለማከናወን መቀመጡን ከሚናገረው በዳንኤል ምዕራፍ 7 ላይ ካለው ትዕይንት ጋር የሚመሳሰል ነው።
26. ይህን ምሳሌ በተመለከተ ምን አዲስ ግንዛቤ ተገኝቷል?
26 የበጎቹንና የፍየሎቹን ምሳሌ በዚህ መንገድ መረዳት በበጎቹና በፍየሎቹ ላይ ፍርድ የሚሰጠው ወደፊት እንደሆነ ያሳያል። በማቴዎስ 24:29, 30 ላይ የተጠቀሰው “መከራ” ከፈነዳና የሰው ልጅ ‘በክብሩ ከመጣ’ በኋላ የሚፈጸም ነገር ነው። (ከማርቆስ 13:24–26 ጋር አወዳድር።) ከዚያ በኋላ በጠቅላላው የነገሮች ሥርዓት መጨረሻ ወቅት ኢየሱስ ችሎት ላይ ተቀምጦ ለአንዳንዶቹ ሲፈርድላቸው በሌሎች ላይ ደግሞ የጥፋት ፍርድ ይበይንባቸዋል።—ዮሐንስ 5:30፤ 2 ተሰሎንቄ 1:7–10
-
-
የበጎቹና የፍየሎቹ የወደፊት ዕጣ ምንድን ነው?መጠበቂያ ግንብ—1995 | ጥቅምት 15
-
-
3. ኢየሱስ ቀደም ሲል ባቀረበው ንግግሩ ላይ ታላቁ መከራ ከጀመረ በኋላ ወዲያውኑ ምን ይሆናል ብሎ ነበር?
3 ኢየሱስ ታላቁ መከራ ከፈነዳ “በኋላ ወዲያው” እንደሚከሰቱ የምንጠብቃቸውን አስደንጋጭ ሁኔታዎች አስቀድሞ ተናግሯል። በዚያን ጊዜ “የሰው ልጅ ምልክት” ይታያል ብሏል። ይህ ሁኔታ “የሰው ልጅ በኃይልና በብዙ ክብር በሰማይ ደመና ሲመጣ” የሚያዩትን “የምድር ወገኖች” በከፍተኛ ደረጃ ይነካል። የሰው ልጅ “ከመላእክቱ” ጋር ይመጣል። (ማቴዎስ 24:21, 29–31)a የበጎቹና የፍየሎቹ ምሳሌ የሚፈጸመው እንዴት ነው? ዘመናዊ መጽሐፍ ቅዱሶች በምዕራፍ 25 ውስጥ ያስቀምጡት እንጂ ይህ ምሳሌ ኢየሱስ ለቀረበለት ጥያቄ የሰጠው መልስ ክፍል ሲሆን በክብሩ ስለሚመጣበት ጊዜ ተጨማሪ ማብራሪያ የሚገኝበትና “በአሕዛብ ላይ” በመፍረድ ሥራው ላይ የሚያተኩር ነው።—ማቴዎስ 25:32
በምሳሌው ውስጥ የተገለጹት
4. በበጎቹና በፍየሎቹ ምሳሌ መጀመሪያ ላይ ስለ ኢየሱስ የተጠቀሰው ምንድን ነው? ሌሎችስ እነማን ተጠቅሰዋል?
4 ኢየሱስ ምሳሌውን የጀመረው ‘የሰው ልጅ በሚመጣበት ጊዜ’ በማለት ነው። “የሰው ልጅ” ማን እንደሆነ ሳታውቅ አትቀርም። የወንጌል ጸሐፊዎች ብዙውን ጊዜ የሰው ልጅ የሚለውን አጠራር ኢየሱስን ለመግለጽ ይጠቀሙበታል። ኢየሱስ ራሱ እንኳ ራሱን የሰው ልጅ ብሎ የጠራው “የሰው ልጅ የሚመስል” “ግዛትና ክብር መንግሥትም” ለመቀበል በዘመናት ወደ ሸመገለው እንደ ቀረበ የሚገልጸውን የዳንኤል ራእይ በአእምሮው ይዞ እንደ ነበረ አያጠራጥርም። (ዳንኤል 7:13, 14፤ ማቴዎስ 26:63, 64፤ ማርቆስ 14:61, 62) በዚህ ምሳሌ ውስጥ በዋነኛነት የተጠቀሰው ኢየሱስ ቢሆንም ሌሎችም አሉ። በማቴዎስ 24:30, 31 ላይ እንደ ተገለጸው ቀደም ሲል በዚህ ንግግሩ ውስጥ የሰው ልጅ ‘በኃይልና በብዙ ክብር ሲመጣ’ መላእክት ከፍተኛ ሚና እንደሚጫወቱ ተናግሮ ነበር። በተመሳሳይም የበጎቹና የፍየሎቹ ምሳሌ ኢየሱስ ‘በክብሩ ዙፋን ላይ’ ለፍርድ ‘ሲቀመጥ’ መላእክት ከእሱ ጋር እንደሚኖሩ ያሳያል። (ከማቴዎስ 16:27 ጋር አወዳድር።) ይሁን እንጂ ዳኛውና መላእክቱ በሰማይ ስለሆኑ በምሳሌው ውስጥ የተጠቀሱት ሰዎች በሰማይ ናቸውን?
-
-
የበጎቹና የፍየሎቹ የወደፊት ዕጣ ምንድን ነው?መጠበቂያ ግንብ—1995 | ጥቅምት 15
-
-
ተመሳሳይነታቸውን አስተውሉ
ታላቁ መከራ ከጀመረ በኋላ የሰው ልጅ ይመጣል የሰው ልጅ ይመጣል
በታላቅ ክብር ይመጣል በክብር ከመጣ በኋላ
በክብራማ ዙፋኑ ላይ ይቀመጣል
-
-
የበጎቹና የፍየሎቹ የወደፊት ዕጣ ምንድን ነው?መጠበቂያ ግንብ—1995 | ጥቅምት 15
-
-
የምድር ወገኖች ሁሉ ያዩታል አሕዛብ ሁሉ በፊቱ ይሰበሰባሉ፤ በመጨረሻም
ፍየሎች ይፈረድባቸዋል (ታላቁ
መከራ ያበቃል)
-