-
‘ታማኙ ባሪያ’ ፈተናውን አለፈ!መጠበቂያ ግንብ—2004 | መጋቢት 1
-
-
2, 3. ‘የክፉው ባሪያ’ አባላት አስቀድሞ የየትኛው ቡድን አባላት ነበሩ? ክፉ ባሪያ የሆኑትስ እንዴት ነው?
2 ኢየሱስ ስለ “ታማኝና ልባም ባሪያ” ከተናገረ በኋላ ስለ አንድ ክፉ ባሪያም ተናግሮ ነበር። እንዲህ አለ፦ “ያ ክፉ ባሪያ ግን፦ ጌታዬ እስኪመጣ ይዘገያል ብሎ በልቡ ቢያስብ፣ ባልንጀሮቹን ባሮች ሊመታ ቢጀምር ከሰካሮችም ጋር ቢበላና ቢጠጣ፣ የዚያ ባሪያ ጌታ ባልጠበቃት ቀን ባላወቃትም ሰዓት ይመጣል፣ ከሁለትም ይሰነጥቀዋል፣ እድሉንም ከግብዞች ጋር ያደርግበታል፤ በዚያ ልቅሶና ጥርስ ማፋጨት ይሆናል።” (ማቴዎስ 24:48-51 የ1954 ትርጉም) “ያ ክፉ ባሪያ” የሚለው አገላለጽ ኢየሱስ ቀደም ሲል ስለ ታማኝና ልባም ባሪያ የተናገረውን ሐሳብ ያስታውሰናል። አዎን፣ የዚህ “ክፉ ባሪያ” አባላት በአንድ ወቅት የታማኙ ባሪያ ክፍል ነበሩ።a ታዲያ “ክፉ ባሪያ” የሆኑት እንዴት ነው?
-
-
‘ታማኙ ባሪያ’ ፈተናውን አለፈ!መጠበቂያ ግንብ—2004 | መጋቢት 1
-
-
4. ኢየሱስ ‘ክፉውን ባሪያና’ የእርሱን ዓይነት መንፈስ ያሳዩትን ምን ያደርጋቸዋል?
4 እነዚህ ቀድሞ ክርስቲያን የነበሩ ሰዎች የኋላ ኋላ ‘የክፉው ባሪያ’ አባላት የሆኑ ሲሆን በዚህም ምክንያት ኢየሱስ ‘ከሁለት ሰንጥቋቸዋል።’ እንዴት? በእርሱ ዘንድ የነበራቸውን ተቀባይነትና ወደ ሰማይ የመሄድ መብታቸውን አጥተዋል። ወዲያውኑ ግን አላጠፋቸውም። ከዚያ በፊት ከክርስቲያን ጉባኤ ‘ውጭ ወዳለው ጨለማ’ ተጥለው ‘እያለቀሱና ጥርሳቸውን እያፋጩ’ ለተወሰነ ጊዜ ይቆያሉ። (ማቴዎስ 8:12) ከዚያ ጊዜ ወዲህ ሌሎች ጥቂት የተቀቡ ክርስቲያኖችም ተመሳሳይ መጥፎ መንፈስ በማንጸባረቅ ‘የክፉው ባሪያ’ ክፍል መሆናቸውን አሳይተዋል። ‘ከሌሎች በጎች’ መካከልም አንዳንዶቹ የእነርሱን የክህደት ጎዳና ተከትለዋል። (ዮሐንስ 10:16) እንደነዚህ ያሉት የክርስቶስ ጠላቶች በሙሉ ‘በውጭ ወዳለው መንፈሳዊ ጨለማ ይጣላሉ።’
-