-
ለጉባኤው አንድነት የበኩልህን አስተዋጽኦ አበርክትለዘላለም በደስታ ኑር!—አሳታፊ የመጽሐፍ ቅዱስ መማሪያ
-
-
3. ከአንድ ወንድም ወይም ከአንዲት እህት ጋር አለመግባባት ቢያጋጥምህ ምን ማድረግ ይኖርብሃል?
በመካከላችን አንድነት ቢኖርም ሁላችንም ፍጹም አይደለንም። አንዳችን ሌላውን ቅር የምናሰኝበት አልፎ ተርፎም የምንጎዳበት ጊዜ አለ። የአምላክ ቃል “በነፃ ይቅር መባባላችሁን ቀጥሉ” የሚል ምክር የሚሰጠን ለዚህ ነው። ጥቅሱ አክሎም “ይሖዋ በነፃ ይቅር እንዳላችሁ ሁሉ እናንተም እንዲሁ አድርጉ” ይላል። (ቆላስይስ 3:13ን አንብብ።) ይሖዋ በተደጋጋሚ ብናሳዝነውም ይቅር ይለናል። በመሆኑም እኛም ወንድሞቻችንን ይቅር እንድንል ይጠብቅብናል። አንድን ሰው ቅር እንዳሰኘህ ከተገነዘብክ ቅድሚያ ወስደህ ሰላም ለመፍጠር ጥረት አድርግ።—ማቴዎስ 5:23, 24ን አንብብ።b
-
-
ለጉባኤው አንድነት የበኩልህን አስተዋጽኦ አበርክትለዘላለም በደስታ ኑር!—አሳታፊ የመጽሐፍ ቅዱስ መማሪያ
-
-
አንዳንድ ጊዜ እኛ ራሳችን ሌሎችን ቅር ልናሰኝ እንችላለን። እንዲህ ያለ ሁኔታ ሲፈጠር ምን ማድረግ ይኖርብናል? ቪዲዮውን ተመልከቱ፤ ከዚያም በሚከተለው ጥያቄ ላይ ተወያዩ፦
በቪዲዮው ላይ የታየችው እህት ሰላም ለመፍጠር ስትል ምን አድርጋለች?
-