-
አምላክ ሀብት በመስጠት ይባርከናል?ንቁ!—2003 | ጥቅምት 8
-
-
አምላክ እኛን የሚባርከን እንዴት ነው?
ኢየሱስ ተከታዮቹ መሠረታዊ ስለሆኑ ነገሮች ‘እንዳይጨነቁ’ በነገራቸው ጊዜ ስለ ገንዘብ ጤናማ አመለካከት እንዲኖራቸው አስተምሯቸዋል። ሰሎሞን እንኳን ያን ያህል ክብር ኖሮት የሜዳ አበቦችን ያህል እንዳልለበሰ አስረዳቸው። ሆኖም ኢየሱስ “እግዚአብሔር ግን . . . የሜዳን ሣር እንዲህ የሚያለብሰው ከሆነ፣ እናንተ እምነት የጎደላችሁ እናንተንማ ይልቁን እንዴት?” ብሏል። ኢየሱስ ተከታዮቹ መንግሥቱንና ጽድቁን ካስቀደሙ የሚያስፈልጋቸውን ምግብ፣ ልብስና መጠለያ እንደሚያገኙ ለክርስቲያኖች ማረጋገጫ ሰጥቷቸዋል። (ማቴዎስ 6:25, 28-33) ኢየሱስ የሰጠው ይህ ተስፋ የሚፈጸመው እንዴት ነው?
የመጽሐፍ ቅዱስን ምክር መከተል በተለይ መንፈሳዊ በረከቶችን ያስገኛል። (ምሳሌ 10:22) ይሁን እንጂ ሌላ ጥቅምም አለው። ለምሳሌ ያህል የአምላክ ቃል ክርስቲያኖችን “የሰረቀ ከእንግዲህ ወዲህ አይስረቅ፣ . . . በገዛ እጆቹ መልካምን እየሠራ ይድከም” በማለት ያዛቸዋል። (ኤፌሶን 4:28) በተጨማሪም “የታካች እጅ ችግረኛ ታደርጋለች፤ የትጉ እጅ ግን ባለጠጋ ታደርጋለች” በማለት ይናገራል። (ምሳሌ 10:4) ይህን ምክር የሚከተሉ ሐቀኞችና ታታሪ ክርስቲያኖች ብዙውን ጊዜ በሥራው መስክ ተፈላጊነት አላቸው። ይህም በረከት ሊሆን ይችላል።
በተጨማሪም መጽሐፍ ቅዱስ ክርስቲያኖች ስግብግብነትን የሚያንጸባርቅ የጊዜ ማሳለፊያ ከሆነው ከቁማር፣ ሰውነትን ከሚያረክሰው ሲጋራ የማጨስ ሱስና በጣም ጎጂ ከሆነው የመጠጥ ሱስ እንዲርቁ ያስተምራል። (1 ቆሮንቶስ 6:9, 10፤ 2 ቆሮንቶስ 7:1፤ ኤፌሶን 5:5) ይህን ምክር ተግባራዊ የሚያደርጉ ሁሉ ወጪያቸው የሚቀንስ ከመሆኑም በላይ ጤንነታቸውም ይሻሻላል።
-
-
አምላክ ሀብት በመስጠት ይባርከናል?ንቁ!—2003 | ጥቅምት 8
-
-
ይሖዋ አምላክ ፈቃዱን ለማድረግ የሚጣጣሩ ሰዎችን ይባርካል። (መዝሙር 1:2, 3) መከራን ለመቋቋም፣ ለቤተሰቦቻቸው የሚያስፈልገውን ለማቅረብና መንግሥቱን ለማስቀደም የሚያስችላቸውን ጥንካሬና የገቢ ምንጭ ይሰጣቸዋል። (መዝሙር 37:25፤ ማቴዎስ 6:31-33፤ ፊልጵስዩስ 4:12, 13) በመሆኑም እውነተኛ ክርስቲያኖች አምላክ በዋነኝነት የሚባርካቸው ቁሳዊ ነገሮችን በመስጠት እንደሆነ አድርገው ከማሰብ ይልቅ “በበጎ ሥራ ባለጠጎች” ለመሆን ይጣጣራሉ። ክርስቲያኖች ከፈጣሪ ጋር የቅርብ ዝምድና በመመሥረት “ለሚመጣውም ዘመን ለራሳቸው መልካም መሠረት የሚሆንላቸውን መዝገብ” ይሰበስባሉ።—1 ጢሞቴዎስ 6:17–19፤ ማርቆስ 12:42-44
-