-
ለዘመናችን የሚሆን መልእክት የያዘ የጥበብ መጽሐፍመጠበቂያ ግንብ—1999 | ሚያዝያ 1
-
-
ሚሆኮ ባሏ ያደረገውን ለውጥ በመመልከቷ እርሷም የምትማረውን ትምህርት በሥራ ላይ ማዋል ጀመረች። ሌላው በተለይ በጣም የረዳቸው “እንዳይፈረድባችሁ አትፍረዱ፤ በምትፈርዱበት ፍርድ ይፈረድባችኋልና፣ በምትሰፍሩበትም መስፈሪያ ይሰፈርባችኋል” የሚለው መሠረታዊ ሥርዓት ነው።e ስለዚህ ሚሆኮ እና ባለቤቷ ስለ መልካም ጎኖቻቸው ለማውራትና አንዳቸው የሌላውን ስህተት ከመለቃቀም ይልቅ እንዴት ማሻሻል እንደሚችሉ ለመነጋገር ወሰኑ። ታዲያ ውጤቱ ምን ሆነ? ሚሆኮ እንዲህ በማለት ታስታውሳለች:- “በእርግጥም ደስተኛ እንድሆን አድርጎኛል። ሁልጊዜ ማታ ማታ እራት እየበላን መወያየት ከጀመርን ሰነባብተናል። የሦስት ዓመት ወንድ ልጃችንም ሳይቀር በውይይታችን ውስጥ ይካፈላል። በእርግጥም ማነቃቂያ ሰጥቶናል!”
-