-
“የራስ ጠጒራችሁ እንኳ አንድ ሳይቀር” በይሖዋ ተቆጥሯልመጠበቂያ ግንብ—2005 | ነሐሴ 1
-
-
6 ኢየሱስ ሐዋርያቱ ለምን መፍራት እንደሌለባቸው ለማስረዳት ሁለት ምሳሌዎችን ተጠቀመ። እንዲህ አላቸው:- “በአንድ ሳንቲም ከሚሸጡት ሁለት ድንቢጦች አንዲቷ እንኳ ያለ አባታችሁ ፈቃድ ምድር ላይ አትወድቅም። የራስ ጠጒራችሁ እንኳ አንድ ሳይቀር የተቈጠረ ነው። ስለዚህ አትፍሩ፤ ከብዙ ድንቢጦች ይልቅ ዋጋችሁ የከበረ ነው።” (ማቴዎስ 10:29-31) ኢየሱስ እዚህ ላይ መከራ በሚያጋጥመን ጊዜ አለመፍራትን፣ በግለሰብ ደረጃ ይሖዋ ያስብልኛል ብሎ ከመተማመን ጋር አያይዞ እንደገለጸው አስተውል። ሐዋርያው ጳውሎስ እንዲህ ያለ እምነት እንደነበረው ከሁኔታው መረዳት ይቻላል። እንዲህ ብሎ ጽፏል:- “እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ከሆነ፣ ማን ሊቃወመን ይችላል? ለገዛ ልጁ ያልሳሳለት፣ ነገር ግን ለሁላችንም አሳልፎ የሰጠው እርሱ፣ ሁሉንስ ነገር ከእርሱ ጋር እንደ ምን በልግስና አይሰጠን?” (ሮሜ 8:31, 32) አንተም ለይሖዋ ታማኝ እስከሆንክ ድረስ ምንም ዓይነት ችግር ቢያጋጥምህ እርሱ በግለሰብ ደረጃ እንደሚያስብልህ እርግጠኛ መሆን ትችላለህ። ኢየሱስ ለሐዋርያቱ የሰጣቸውን ማሳሰቢያ በጥልቅ እየመረመርን ስንሄድ ይሖዋ በግለሰብ ደረጃ እንደሚያስብልህ በግልጽ መረዳት ትችላለህ።
-
-
“የራስ ጠጒራችሁ እንኳ አንድ ሳይቀር” በይሖዋ ተቆጥሯልመጠበቂያ ግንብ—2005 | ነሐሴ 1
-
-
10. “የራስ ጠጒራችሁ እንኳ አንድ ሳይቀር የተቈጠረ ነው” የሚለው አነጋገር ምን ቁም ነገር ይዟል?
10 ኢየሱስ ስለ ድንቢጦቹ ከተናገረው ምሳሌ በተጨማሪ “የራስ ጠጒራችሁ እንኳ አንድ ሳይቀር የተቈጠረ ነው” ሲል ገልጾ ነበር። (ማቴዎስ 10:30) ይህ አጭር ሆኖም ትልቅ ቁም ነገር ያዘለ ዓረፍተ ነገር ኢየሱስ ስለ ድንቢጦቹ የተናገረውን ምሳሌ ነጥብ በጥልቅ ለመረዳት ያስችላል። እስቲ አስበው፤ በአንድ ሰው ራስ ላይ በአማካይ 100,000 የሚያህሉ ፀጉሮች ይገኛሉ። በአብዛኛው አንዷ ነጠላ ፀጉር ከሌላው ጋር በጣም ስለምትመሳሰል አንዷ ፀጉራችን ልዩ ትኩረት ሊደረግላት ይገባል ብለን አናስብም። ይሁን እንጂ ይሖዋ አምላክ ለእያንዳንዱ ፀጉራችን ትኩረት ከመስጠቱም በተጨማሪ በራሳችን ላይ ያሉትን ፀጉሮች አንድም ሳይቀር ቆጥሯቸዋል። ከዚህ አንጻር ሲታይ ይሖዋ ስለ ሕይወታችን የማያውቀው ነገር ይኖራል? ይሖዋ የእያንዳንዱን አገልጋዩን ባሕርይ ጠንቅቆ እንደሚያውቅ ምንም አያጠራጥርም። አልፎ ተርፎም “ልብን ያያል።”—1 ሳሙኤል 16:7
11. ዳዊት በግለሰብ ደረጃ ይሖዋ እንደሚያስብለት ያለውን እምነት የገለጸው እንዴት ነው?
11 በርካታ ችግሮች ይፈራረቁበት የነበረው ዳዊት ይሖዋ ትኩረት እንደሚሰጠው እምነት ነበረው። “እግዚአብሔር ሆይ፤ መረመርኸኝ፤ ደግሞም ዐወቅኸኝ። አንተ መቀመጤንና መነሣቴን ታውቃለህ፤ የልቤንም ሐሳብ ገና ከሩቁ ታስተውላለህ” በማለት ጽፏል። (መዝሙር 139:1, 2) አንተም ይሖዋ በግለሰብ ደረጃ እንደሚያውቅህ እርግጠኛ መሆን ትችላለህ። (ኤርምያስ 17:10) ‘ሁሉን የሚመለከተው ይሖዋ ትኩረት ሰጥቶ እንዲያየኝ የሚያስችል ብቃት ፈጽሞ የለኝም’ ብለህ ለመደምደም አትቸኩል!
-