-
በኢየሱስ ምክንያት ትሰናከላለህ?መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)—2021 | ግንቦት
-
-
(3) ኢየሱስ ብዙ የአይሁዳውያን ልማዶችን አልተከተለም
13. ብዙዎች ኢየሱስን እንዳይቀበሉት ያደረጋቸው ምንድን ነው?
13 የኢየሱስ ደቀ መዛሙርት አለመጾማቸው የመጥምቁ ዮሐንስን ደቀ መዛሙርት አስገርሟቸው ነበር። ኢየሱስም እሱ በሕይወት እስካለ ድረስ ደቀ መዛሙርቱ የሚጾሙበት ምክንያት እንደሌለ ገልጿል። (ማቴ. 9:14-17) ያም ቢሆን ፈሪሳውያንና ሌሎች ተቃዋሚዎቹ ኢየሱስ የእነሱን ልማዶችና ወጎች ባለመከተሉ አውግዘውታል። የታመሙ ሰዎችን በሰንበት በመፈወሱ በጣም ተቆጥተው ነበር። (ማር. 3:1-6፤ ዮሐ. 9:16) እነዚህ ሰዎች በአንድ በኩል ሰንበትን እንደሚያከብሩ በኩራት ይናገራሉ፤ በሌላ በኩል ግን ያለአንዳች እፍረት በቤተ መቅደሱ ውስጥ የንግድ እንቅስቃሴ ያካሂዳሉ። ይህን በማድረጋቸው ኢየሱስ ስላወገዛቸው በጣም ተቆጥተው ነበር። (ማቴ. 21:12, 13, 15) ኢየሱስ በናዝሬት በሚገኘው ምኩራብ የሰበከላቸው ሰዎችም፣ ኢየሱስ በእስራኤል ታሪክ ውስጥ የሚገኙ ሰዎችን በመጥቀስ ራስ ወዳድነታቸውንና እምነት የለሽነታቸውን ስላጋለጠባቸው በጣም ተበሳጭተው ነበር። (ሉቃስ 4:16, 25-30) በርካታ አይሁዳውያን ኢየሱስ የጠበቁትን ነገር ባለማድረጉ ተሰናክለውበታል።—ማቴ. 11:16-19
14. ኢየሱስ ከቅዱሳን መጻሕፍት ጋር የሚጋጩ የሰው ወጎችን ያወገዘው ለምንድን ነው?
14 ቅዱሳን መጻሕፍት ምን ይላሉ? ይሖዋ በነቢዩ ኢሳይያስ አማካኝነት እንዲህ ብሏል፦ “ይህ ሕዝብ ወደ እኔ የሚቀርበው በአፉ ብቻ ነው፤ በከንፈሩም ያከብረኛል፤ ልቡ ግን ከእኔ እጅግ የራቀ ነው፤ እኔንም የሚፈራው፣ ሰዎች ያስተማሩትን ትእዛዛት በማክበር ነው።” (ኢሳ. 29:13) ኢየሱስ ከቅዱሳን መጻሕፍት ጋር የሚጋጩ የሰው ወጎችን ማውገዙ ትክክል ነበር። ሰው ሠራሽ ሕጎችንና ወጎችን ከቅዱሳን መጻሕፍት ያስበለጡት ሰዎች ይሖዋንና እሱ የላከውን መሲሕ እንደማይቀበሉ አሳይተዋል።
-
-
በኢየሱስ ምክንያት ትሰናከላለህ?መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)—2021 | ግንቦት
-
-
(4) ኢየሱስ በዘመኑ የነበረውን ፖለቲካዊ ሥርዓት አልለወጠውም
17. በኢየሱስ ዘመን የኖሩ ብዙ ሰዎች የተሰናከሉት መሲሑ ምን እንደሚያደርግ ይጠብቁ ስለነበር ነው?
17 በኢየሱስ ዘመን የኖሩ አንዳንድ ሰዎች ያኔውኑ ፖለቲካዊ ለውጥ እንዲመጣ ይፈልጉ ነበር። መሲሑ ከሮማውያን ጭቆና ነፃ እንደሚያወጣቸው ጠብቀው ነበር። ኢየሱስ ግን ሊያነግሡት ሲሞክሩ ፈቃደኛ አልሆነም። (ዮሐ. 6:14, 15) ካህናቱን ጨምሮ ሌሎች ሰዎች ደግሞ ኢየሱስ ሮማውያንን የሚያስቆጣ ፖለቲካዊ ለውጥ ያመጣል የሚል ስጋት አድሮባቸው ነበር፤ ስጋት ያደረባቸው እንዲህ ያለው ለውጥ ሮማውያን ለካህናቱ የሰጧቸውን ሥልጣን እንዲቀሟቸው ሊያደርግ ስለሚችል ነው። ብዙ አይሁዳውያን በኢየሱስ እንዲሰናከሉ ያደረጓቸው እንዲህ ያሉ ፖለቲካዊ ጉዳዮች ነበሩ።
18. ብዙዎች ስለ መሲሑ የሚገልጹትን የትኞቹን ትንቢቶች ችላ ብለዋቸው ነበር?
18 ቅዱሳን መጻሕፍት ምን ይላሉ? መሲሑ ከጊዜ በኋላ ድል አድራጊ ንጉሥ እንደሚሆን የሚጠቁሙ በርካታ ትንቢቶች ቢኖሩም ሌሎች ትንቢቶች ደግሞ መሲሑ መጀመሪያ ለኃጢአታችን እንደሚሞት ይገልጻሉ። (ኢሳ. 53:9, 12) ታዲያ አይሁዳውያን ስለ መሲሑ የተሳሳተ አመለካከት የነበራቸው ለምንድን ነው? በኢየሱስ ዘመን የኖሩ በርካታ ሰዎች ችግሮቻቸው ወዲያውኑ እንደሚፈቱ የማይገልጹ ትንቢቶችን ችላ ብለዋቸው ስለነበር ነው።—ዮሐ. 6:26, 27
-