-
ሰውነታችን ቢዝልም መንፈሳችን አይደክምምመጠበቂያ ግንብ—2004 | ነሐሴ 15
-
-
1, 2. (ሀ) ንጹሑን አምልኮ መከተል ለሚፈልጉ ሁሉ ምን ማራኪ ግብዣ ቀርቦላቸዋል? (ለ) መንፈሳዊ አቋማችንን ከባድ አደጋ ላይ ሊጥልብን የሚችለው ምንድን ነው?
የኢየሱስ ደቀ መዛሙርት እንደመሆናችን መጠን “እናንት ሸክም የከበዳችሁና የደከማችሁ ሁሉ ወደ እኔ ኑ፤ እኔም ዕረፍት እሰጣችኋለሁ። . . . ቀንበሬ ልዝብ ሸክሜም ቀላል ነውና” የሚለውን አስደሳች ግብዣ በደንብ እናውቀዋለን። (ማቴዎስ 11:28-30) ከዚህ በተጨማሪ ክርስቲያኖች ‘[ከይሖዋ] ዘንድ የመታደስ ዘመን’ እንደሚመጣላቸው ቃል ተገብቶላቸዋል። (የሐዋርያት ሥራ 3:19) የመጽሐፍ ቅዱስን እውነት መማር፣ ስለ ወደፊቱ ጊዜ ብሩህ ተስፋ ማግኘትና የይሖዋን መሠረታዊ ሥርዓቶች በሥራ ማዋል ከፍተኛ እረፍት የሚያስገኝ መሆኑን እንደቀመሳችሁ ግልጽ ነው።
2 ሆኖም አንዳንድ የይሖዋ አምላኪዎች አልፎ አልፎ ኃይላቸው እንደተሟጠጠ ይሰማቸዋል። አንዳንድ ጊዜ እንዲህ ዓይነቱ የተስፋ መቁረጥ ስሜት ለአጭር ጊዜ የሚቆይ ሲሆን በሌላ ወቅት ደግሞ ረዘም ላለ ጊዜ ሊዘልቅ ይችላል። ጊዜ እያለፈ ሲሄድ አንዳንዶች ክርስቲያናዊ ግዴታዎቻቸው ኢየሱስ ተስፋ እንደሰጠው እረፍት የሚያስገኝ ቀላል ሸክም ከመሆን ይልቅ አድካሚ ሆነውባቸዋል። እንዲህ ያለው አፍራሽ ስሜት አንድ ክርስቲያን ከይሖዋ ጋር የመሠረተውን ዝምድና ከባድ አደጋ ላይ ሊጥልበት ይችላል።
-
-
ሰውነታችን ቢዝልም መንፈሳችን አይደክምምመጠበቂያ ግንብ—2004 | ነሐሴ 15
-
-
የክርስትና ሕይወት ጨቋኝ አይደለም
5. የክርስቶስ ደቀ መዝሙር መሆንን በተመለከተ እርስ በርሱ የሚጋጭ የሚመስለው ሐሳብ የትኛው ነው?
5 የክርስትና ሕይወት ተጋድሎ እንደሚጠይቅ የታወቀ ነው። (ሉቃስ 13:24) እንዲያውም ኢየሱስ “የራሱንም መስቀል ተሸክሞ የማይከተለኝ ደቀ መዝሙሬ ሊሆን አይችልም” ሲል ተናግሯል። (ሉቃስ 14:27) ይህን አባባል በጥሞና ካላጤንነው በስተቀር ኢየሱስ ሸክሙ ቀላልና እረፍት የሚያስገኝ እንደሆነ ከተናገረው ሐሳብ ጋር የሚቃረን ሊመስል ይችላል። እንደ እውነቱ ከሆነ ግን ሁለቱ ሐሳቦች እርስ በርስ አይጋጩም።
6, 7. አምልኮታችን አታካች አይደለም ሊባል የሚችለው ለምንድን ነው?
6 ጉልበት ሳይቆጥቡ በትጋት መሥራት አድካሚ ቢሆንም ለጥሩ ዓላማ እስከሆነ ድረስ አርኪና መንፈስ የሚያድስ ሊሆን ይችላል። (መክብብ 3:13, 22) ታዲያ አስደሳች የሆነውን የመጽሐፍ ቅዱስ እውነት ለሰዎች ከማካፈል የተሻለ ምን ሥራ አለ? ከዚህ በተጨማሪ አምላክ ያወጣቸውን ከፍተኛ የሥነ ምግባር ደንቦች ለመጠበቅ የምናደርገውን ትግል ከምናገኘው ጥቅም ጋር ስናወዳድረው እዚህ ግባ የሚባል አይደለም። (ምሳሌ 2:10-20) ስደት በሚደርስብን ጊዜም እንኳ ለአምላክ መንግሥት ብለን መከራ መቀበሉን እንደ ክብር እንቆጥረዋለን።—1 ጴጥሮስ 4:14
7 በሐሰት ሃይማኖት ቀንበር ሥር ያሉ ሰዎች ከሚገኙበት መንፈሳዊ ጨለማ ጋር ካስተያየነው ደግሞ የኢየሱስ ሸክም እረፍት የሚያስገኝ ለመሆኑ ምንም ጥያቄ የለውም። አምላክ በጣም ስለሚወደን ከአቅማችን በላይ የሆነ ትእዛዝ አይሰጠንም። የይሖዋ ‘ትእዛዛት ከባዶች አይደሉም።’ (1 ዮሐንስ 5:3) በቅዱሳን ጽሑፎች ላይ በተገለጸው መሠረት እውነተኛ ክርስትና ጨቋኝ አይደለም። አዎን፣ አምልኮታችን እንድንዝልና ተስፋ እንድንቆርጥ የሚያደርግ አይደለም።
-