-
ክርስቲያን ሴቶችን ደግፏቸውመጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)—2020 | መስከረም
-
-
6. በሉቃስ 10:38-42 ላይ እንደተጠቀሰው ኢየሱስ ማርያምንና ማርታን የረዳቸው እንዴት ነው?
6 ኢየሱስ ከመንፈሳዊ እህቶቹ ጋር ጊዜ ያሳልፍ ነበር፤ እውነተኛ ወዳጅም ሆኖላቸዋል። ከማርያምና ከማርታ ጋር የነበረውን ወዳጅነት እንደ ምሳሌ እንመልከት፤ ሁለቱም ነጠላ የነበሩ ይመስላል። (ሉቃስ 10:38-42ን አንብብ።) ኢየሱስ በንግግሩም ሆነ በድርጊቱ ነፃነት ተሰምቷቸው እንዲቀርቡት አድርጓቸው መሆን አለበት። ማርያም አንድ ደቀ መዝሙር እንደሚያደርገው ሳትፈራ እግሩ ሥር ተቀምጣለች።c ማርታም ብትሆን ማርያም ስላላገዘቻት በተበሳጨችበት ወቅት፣ ስሜቷን ለኢየሱስ በነፃነት ነግራዋለች። በዚህ ግብዣ ላይ ኢየሱስ ሁለቱንም ሴቶች በመንፈሳዊ ለመርዳት አጋጣሚውን ተጠቅሞበታል። በተጨማሪም እነዚህን ሴቶችም ሆነ ወንድማቸውን አልዓዛርን በሌሎች አጋጣሚዎችም ሄዶ በመጠየቅ እንደሚያስብላቸው አሳይቷል። (ዮሐ. 12:1-3) አልዓዛር በጠና በታመመበት ወቅት ማርያምና ማርታ የኢየሱስን እርዳታ ለመጠየቅ ያልተሳቀቁት ለዚህ ነው።—ዮሐ. 11:3, 5
-
-
ክርስቲያን ሴቶችን ደግፏቸውመጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)—2020 | መስከረም
-
-
c አንድ የማመሣከሪያ ጽሑፍ እንዲህ ይላል፦ “ደቀ መዛሙርት በአስተማሪዎቻቸው እግር ሥር ይቀመጡ ነበር። እነዚህ ሰዎች በቁም ነገር ትምህርታቸውን የሚከታተሉት አስተማሪ ለመሆን ነበር፤ ይህ ደግሞ ለሴቶች የሚፈቀድ ነገር አልነበረም። . . . ማርያም በባሕሉ ከሴቶች የሚጠበቀውን ድርሻ . . . ከመወጣት ይልቅ ኢየሱስ እግር ሥር መቀመጧና ከእሱ ለመማር የነበራት ጉጉት አብዛኞቹን አይሁዳውያን ወንዶች የሚያስደነግጥ ነበር።”
-