-
ትኩረታችሁ ሳይከፋፈል ይሖዋን አገልግሉመጠበቂያ ግንብ—2015 | ጥቅምት 15
-
-
“ማርያም . . . [ኢየሱስ] የሚናገረውን ታዳምጥ ነበር። ማርታ ግን በብዙ ሥራ ተጠምዳ ትባክን ነበር።”—ሉቃስ 10:39, 40
-
-
ትኩረታችሁ ሳይከፋፈል ይሖዋን አገልግሉመጠበቂያ ግንብ—2015 | ጥቅምት 15
-
-
2 ኢየሱስ ማርታን ይወዳት የነበረው እንግዳ ተቀባይና ታታሪ በመሆኗ ብቻ ሳይሆን በመንፈሳዊነቷም ጭምር እንደሆነ ምንም ጥርጥር የለውም። በኢየሱስ ትምህርቶች ከልብ የምታምን ሴት ነበረች። ማርታ ኢየሱስ ተስፋ የተደረገበት መሲሕ እንደሆነ አምና በመቀበል አስደናቂ እምነት እንዳላት አሳይታለች። (ዮሐ. 11:21-27) ይሁንና እሷም እንደ ሌሎቻችን ሁሉ ፍጽምና ይጎድላታል። በአንድ ወቅት ኢየሱስ በቤቷ እየተስተናገደ ሳለ ማርታ ትክክል አይደለም ብላ ያሰበችውን አንድ ሁኔታ ለማስተካከል ኢየሱስ ምን ማድረግ እንዳለበት ለመናገር ደፍራ ነበር። ማርታ “ጌታ ሆይ፣ እህቴ ሥራውን ሁሉ ለእኔ ጥላ ስትቀመጥ ምንም ግድ አይሰጥህም? መጥታ እንድታግዘኝ ንገራት እንጂ” አለችው። (ሉቃስ 10:38-42ን አንብብ።) ከዚህ ዘገባ ምን ትምህርት እናገኛለን?
-
-
ትኩረታችሁ ሳይከፋፈል ይሖዋን አገልግሉመጠበቂያ ግንብ—2015 | ጥቅምት 15
-
-
4 ይሁን እንጂ ማርታ፣ አቅሟ በሚፈቅደው መጠን ኢየሱስን ለማስደሰት ለየት ያለ ምግብ በማዘጋጀትና ሌሎች ሥራዎችን በማከናወን ተጠምዳ ነበር። ይህ ሁሉ ሥራ ግን አላስፈላጊ ጭንቀት ስለፈጠረባት የማርያም ሁኔታ አበሳጫት። ኢየሱስ፣ ማርታ ብዙ ነገር ለማከናወን እየጣረች እንደሆነ ስላስተዋለ በደግነት “ማርታ፣ ማርታ፣ ስለ ብዙ ነገር ትጨነቂያለሽ፤ ደግሞም ትጠበቢያለሽ” አላት። አንድ ዓይነት ምግብ ብቻ በቂ እንደሆነ ሐሳብ ሰጣት። ከዚያም ኢየሱስ ትኩረቱን ወደ ማርያም ዞር በማድረግ “ማርያም በበኩሏ ጥሩ የሆነውን ድርሻ መርጣለች፤ ይህም ከእሷ አይወሰድም” በማለት ድርጊቷ እንደ ቸልተኝነት ሊታይ እንደማይገባ ተናገረ። ማርያም በዚህ ልዩ ወቅት የተመገበችውን ምግብ ብዙም ሳይቆይ ትረሳው ይሆናል፤ ይሁንና ትኩረቷ ሳይከፋፈል ኢየሱስን በማዳመጧ የተቸራትን ምስጋናም ሆነ ያገኘችውን ግሩም መንፈሳዊ ምግብ መቼም አትረሳውም። ሐዋርያው ዮሐንስ ከ60 ከሚበልጡ ዓመታት በኋላ “ኢየሱስ ማርታንና እህቷን . . . ይወዳቸው” እንደነበር ጽፏል። (ዮሐ. 11:5) በመንፈስ መሪነት የተጻፈው ይህ ሐሳብ ማርታ፣ ኢየሱስ የሰጣትን ፍቅራዊ እርማት እንደተቀበለችና በቀሪው ሕይወቷ ይሖዋን በታማኝነት ለማገልገል ጥረት እንዳደረገች በግልጽ ያሳያል።
-