-
‘ቢሞትም እንኳ አሁንም ይናገራል’በእምነታቸው ምሰሏቸው
-
-
5. ኢየሱስ አቤልን “ዓለም ከተመሠረተበት ጊዜ” ጋር አያይዞ መጥቀሱ ምን ትርጉም አለው? (የግርጌ ማስታወሻውንም ተመልከት።)
5 አቤል የተወለደው በሰው ልጆች ታሪክ መባቻ ላይ ነው። ከጊዜ በኋላ ኢየሱስ፣ አቤልን “ዓለም ከተመሠረተበት ጊዜ” ጋር አያይዞ ጠቅሶታል። (ሉቃስ 11:50, 51ን አንብብ።) ኢየሱስ እዚህ ላይ የጠቀሰው ዓለም፣ በቤዛው አማካኝነት ከኃጢአት ነፃ የመውጣት ተስፋ ያላቸውን የሰው ልጆች የሚያመለክት መሆን አለበት። አቤል ወደ ሕልውና ከመጡት ሰዎች አራተኛው ቢሆንም ይሖዋ ከኃጢአት ነፃ መውጣት እንደሚችል አድርጎ የተመለከተው የመጀመሪያው ሰው እሱ ይመስላል።a አቤል ያደገው በጎ ተጽዕኖ ሊያሳድሩበት በሚችሉ ሰዎች መካከል እንዳልነበረ ግልጽ ነው።
-
-
‘ቢሞትም እንኳ አሁንም ይናገራል’በእምነታቸው ምሰሏቸው
-
-
a ‘ዓለም ሲመሠረት’ የሚለው አገላለጽ ዘር መዝራትን ይኸውም መዋለድን ያመለክታል፤ በመሆኑም ይህ አገላለጽ መጀመሪያ ከተወለደው የሰው ልጅ ጋር የተያያዘ መሆን አለበት። ታዲያ ኢየሱስ የአዳምና የሔዋን የመጀመሪያ ልጅ የሆነውን ቃየንን ሳይሆን አቤልን ‘ከዓለም መመሥረት’ ጋር አያይዞ የጠቀሰው ለምንድን ነው? ከሁኔታዎች መመልከት እንደሚቻለው ቃየን ያደረገው ውሳኔና የፈጸመው ድርጊት በይሖዋ አምላክ ላይ ሆን ብሎ ከማመፅ አይተናነስም። በመሆኑም እንደ ወላጆቹ ሁሉ ቃየንም የኃጢአት ይቅርታም ሆነ ትንሣኤ የሚያገኝ አይመስልም።
-