-
“በልቧ ይዛ ታሰላስል ነበር”መጠበቂያ ግንብ—2008 | ጥቅምት 1
-
-
ዮሴፍና ማርያም ራቅ ብላ ወደምትገኘው ወደ ቤተ ልሔም በመጓዝ ላይ ናቸው። ማርያም በአህያ ላይ ተቀምጣ ለሰዓታት ስትጓዝ የቆየች ሲሆን የተመቻት አትመስልም። ዮሴፍ ደግሞ በቀስታ ፊት ፊቷ ይሄዳል። ማርያም በማሕፀኗ ውስጥ ያለው ጽንስ ሲንቀሳቀስ ተሰማት።
በዚህ ወቅት ማርያም ‘የመውለጃ ጊዜዋ ተቃርቦ’ እንደነበር መጽሐፍ ቅዱስ ይናገራል። (ሉቃስ 2:5) ምናልባት ባልና ሚስቱ ማሳዎችን እያቆራረጡ ሲሄዱ የሚያርሱ ወይም የሚዘሩ ገበሬዎች ማርያምን በማየት በእንዲህ ያለ ሁኔታ ላይ ያለች ሴት ለምን እንደምትጓዝ ሳይገርማቸው አይቀርም። ማርያም ከምትኖርበት ከናዝሬት ተነስታ ራቅ ብሎ ወደሚገኘው ወደ ቤተ ልሔም እንድትጓዝ ያነሳሳት ምን ነበር?
-
-
“በልቧ ይዛ ታሰላስል ነበር”መጠበቂያ ግንብ—2008 | ጥቅምት 1
-
-
ሉቃስ፣ ዮሴፍ ‘ለመመዝገብ የተጓዘው ከማርያም ጋር እንደነበር’ ተናግሯል። ከዚህም በተጨማሪ ‘በታጨችለት መሠረት [ዮሴፍ] ማርያምን እንዳገባት’ ገልጿል። (ሉቃስ 2:4, 5 NW) ማርያም ያገባች መሆኗ በምታደርጋቸው ውሳኔዎች ላይ ትልቅ ለውጥ ያመጣል። ዮሴፍን በመንፈሳዊ ጉዳዮች ረገድ የቤተሰቡ ራስ አድርጋ በመመልከት አምላክ የሰጣትን ረዳት የመሆን ኃላፊነቷን ትወጣና ባሏ የሚያደርገውን ውሳኔ ትደግፍ ነበር።a እምነቷን ሊፈትን ይችል የነበረውን ይህን ሁኔታ ታዛዥነት በማሳየት በቀላሉ ልትወጣው ችላለች።
-