-
“ኢየሱስ . . . እስከ መጨረሻው ወደዳቸው”“ተከታዬ ሁን”
-
-
9 ኢየሱስ በሞተበት ዕለት እንኳ ለሚወዳቸው ሰዎች መንፈሳዊ ደህንነት እንደሚጨነቅ አሳይቷል። እስቲ ሁኔታውን በዓይነ ሕሊናህ ለመሳል ሞክር። ኢየሱስ በእንጨት ላይ ተሰቅሎ በጣም እየተሠቃየ ነው። አየር ለመሳብ ሲሞክር በእግሩ ተጠቅሞ ሰውነቱን ወደ ላይ መግፋት ይኖርበታል። ይህን ሲያደርግ፣ የሰውነቱ ክብደት እግሩ በምስማር የተበሳበት ቦታ ላይ ስለሚያርፍ ምስማሩ እግሩን ይበልጥ እየቀደደው ይገባል፤ በግርፋት የተተለተለው ጀርባው ደግሞ ከተሰቀለበት እንጨት ጋር ይፋተጋል፤ ይህ ለከባድ ሥቃይ እንደሚዳርገው ጥርጥር የለውም። መናገር ትንፋሽን መቆጣጠር ይጠይቃል፤ በመሆኑም በዚህ ሁኔታ ውስጥ ሆኖ መናገር ምን ያህል እንደሚከብድና እንደሚያሠቃይ መገመት ያዳግታል። ያም ሆኖ ኢየሱስ ሊሞት በማጣጣር ላይ ሳለ እናቱን ማርያምን ከልብ እንደሚወዳት የሚያሳይ ነገር ተናግሯል። ማርያምንና ሐዋርያው ዮሐንስን በአቅራቢያው ቆመው ሲያያቸው እንደምንም ኃይሉን አሰባስቦ ድምፁን በማሰማት እናቱን “አንቺ ሴት፣ ልጅሽ ይኸውልሽ!” አላት። ከዚያም ዮሐንስን “እናትህ ይህችውልህ!” አለው። (ዮሐንስ 19:26, 27) ኢየሱስ፣ ይህ ታማኝ ሐዋርያ የማርያምን አካላዊና ቁሳዊ ብቻ ሳይሆን መንፈሳዊ ፍላጎቷንም እንደሚያሟላላት ያውቅ ነበር።b
-