-
ወንድሞቻችንና እህቶቻችን እነማን ናቸው?ከታላቁ አስተማሪ ተማር
-
-
የኢየሱስ ወንድሞች ደቀ መዛሙርቱም ጭምር ነበሩ?— መጽሐፍ ቅዱስ መጀመሪያ ላይ “አላመኑበትም ነበር” ይላል። (ዮሐንስ 7:5) በኋላ ግን ያዕቆብና ይሁዳ ደቀ መዛሙርቱ የሆኑ ሲሆን እንዲያውም በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የሚገኙ መጽሐፎችን ጽፈዋል። እነሱ የጻፏቸው መጽሐፎች የትኞቹ እንደሆኑ ታውቃለህ?— አዎ፣ የያዕቆብና የይሁዳ ደብዳቤዎች ናቸው።
ምንም እንኳን የኢየሱስ እህቶች በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ስማቸው ባይጠቀስም ቢያንስ ሁለት እህቶች እንደነበሩት እናውቃለን። ይሁን እንጂ ቁጥራቸው ከዚህም ሊበልጥ ይችላል። እህቶቹስ ተከታዮቹ ሆነዋል?— መጽሐፍ ቅዱስ ይህን ስለማይነግረን ማወቅ አንችልም። ይሁን እንጂ ኢየሱስ “እናቴ ማን ናት? ወንድሞቼስ እነማን ናቸው?” የሚለውን ጥያቄ ያቀረበው ለምን እንደሆነ ታውቃለህ?— እስቲ እንዲህ ያለበትን ምክንያት ለማወቅ እንሞክር።
-
-
ወንድሞቻችንና እህቶቻችን እነማን ናቸው?ከታላቁ አስተማሪ ተማር
-
-
በዚያን ጊዜ የገዛ ራሱ ወንድሞች የነበሩት ያዕቆብ፣ ዮሴፍ፣ ስምዖንና ይሁዳ ኢየሱስ የአምላክ ልጅ እንደሆነ አላመኑም ነበር። መልአኩ ገብርኤል ለእናታቸው ለማርያም የነገራትን ነገር አላመኑም ነበር ማለት ነው። (ሉቃስ 1:30-33) ስለዚህ ለኢየሱስ ክፉ ሆነውበት ሊሆን ይችላል። እንዲህ ዓይነት ጠባይ የሚያሳይ ሰው እውነተኛ ወንድም ወይም እህት አይደለም። ለወንድሙ ወይም ለእህቱ ክፉ የሆነ ሌላ ሰው ታውቃለህ?—
-