-
የሞቱ ሰዎች በምን ዓይነት ሁኔታ ላይ ይገኛሉ?ለዘላለም በደስታ ኑር!—አሳታፊ የመጽሐፍ ቅዱስ መማሪያ
-
-
3. የሞቱ ሰዎች የሚገኙበትን ሁኔታ በተመለከተ እውነታው ምንድን ነው?
የሞቱ ሰዎች የሚገኙበትን ሁኔታ በተመለከተ በዓለም ዙሪያ የተለያየ አመለካከት አለ። መቼም እነዚህ ሁሉ አመለካከቶች እውነት ሊሆኑ እንደማይችሉ የታወቀ ነው።
የሞቱ ሰዎች የሚገኙበትን ሁኔታ በተመለከተ በአካባቢህ ያለው አመለካከት ምንድን ነው?
መጽሐፍ ቅዱስ ምን እንደሚያስተምር ለማወቅ ቪዲዮውን ተመልከቱ።
መክብብ 3:20ን አንብቡ፤ ከዚያም በሚከተሉት ጥያቄዎች ላይ ተወያዩ፦
በዚህ ጥቅስ መሠረት ሰው ከሞተ በኋላ ምን ይሆናል?
ሰው ሲሞት በሕይወት መኖሯን የምትቀጥል ነገር አለች?
መጽሐፍ ቅዱስ የኢየሱስ የቅርብ ወዳጅ ስለነበረው ስለ አልዓዛር ሞት ይናገራል። ዮሐንስ 11:11-14ን አንብቡ፤ ጥቅሱ ሲነበብ ኢየሱስ አልዓዛር የሚገኝበትን ሁኔታ የገለጸው እንዴት እንደሆነ ለማስተዋል ሞክር። ከዚያም በሚከተሉት ጥያቄዎች ላይ ተወያዩ፦
ኢየሱስ ሞትን ከምን ጋር አመሳስሎታል?
ይህ ንጽጽር የሞቱ ሰዎች ስለሚገኙበት ሁኔታ ምን ያስተምረናል?
መጽሐፍ ቅዱስ ሞትን በተመለከተ ስለሚያስተምረው ትምህርት ምን ይሰማሃል?
-
-
በሞት የተለዩህ የምትወዳቸው ሰዎች ዳግመኛ በሕይወት ይኖራሉ!ለዘላለም በደስታ ኑር!—አሳታፊ የመጽሐፍ ቅዱስ መማሪያ
-
-
4. ኢየሱስ የሞቱ ሰዎችን ማስነሳት እንደሚችል አሳይቷል
ኢየሱስ ለወዳጁ ለአልዓዛር ያደረገውን ነገር በስፋት እንመልከት። ዮሐንስ 11:14, 38-44ን አንብቡ፤ ከዚያም በሚከተሉት ጥያቄዎች ላይ ተወያዩ፦
አልዓዛር በእርግጥ ሞቶ እንደነበር እንዴት እናውቃለን?—ቁጥር 39ን ተመልከት።
አልዓዛር ወደ ሰማይ ሄዶ ቢሆን ኖሮ ኢየሱስ መልሶ ወደ ምድር እንዲመጣ የሚያደርገው ይመስልሃል?
-