-
ክርስቶስ ጉባኤውን ይመራልመጠበቂያ ግንብ—2002 | መጋቢት 15
-
-
7. (ሀ) ኢየሱስ በመላው ምድር የሚገኙ ጉባኤዎችን ለመምራት የአስተዳደር አካሉን የሚጠቀመው እንዴት ነው? (ለ) ክርስቲያን የበላይ ተመልካቾች በመንፈስ ቅዱስ የተሾሙ ናቸው ሊባል የሚችለው ለምንድን ነው?
7 እንደ መጀመሪያው መቶ ዘመን ሁሉ በአሁኑም ጊዜ ከቅቡዓን የበላይ ተመልካቾች መካከል የተውጣጣ መላውን ታማኝና ልባም ባሪያ የሚወክል ብቃት ያላቸውን ወንዶች ያቀፈ አንድ አነስተኛ ቡድን የአስተዳደር አካል ሆኖ ያገለግላል። መሪያችን ይህን የአስተዳደር አካል በመጠቀም በመንፈስ ከተቀቡትም ሆነ ካልተቀቡት መካከል በጉባኤ ውስጥ ሽማግሌ ሆነው እንዲያገለግሉ ብቃት ያላቸው ወንዶችን ይሾማል። በዚህ ረገድ ኢየሱስ እንዲጠቀምበት ይሖዋ የሰጠው መንፈስ ቅዱስ ወሳኝ ሚና ይጫወታል። (ሥራ 2:32, 33) በመጀመሪያ ደረጃ እነዚህ የበላይ ተመልካቾች በመንፈስ ቅዱስ አነሣሽነት በተጻፈው በአምላክ ቃል ውስጥ የሰፈሩትን ብቃቶች ማሟላት ይገባቸዋል። (1 ጢሞቴዎስ 3:1-7፤ ቲቶ 1:5-9፤ 2 ጴጥሮስ 1:20, 21) የድጋፍ ሐሳብ የሚቀርበው እንዲሁም ሹመቱ የሚጸድቀው ጸሎት ከተደረገ በኋላ በመንፈስ ቅዱስ መሪነት ነው። በተጨማሪም የሚሾሙት ግለሰቦች የዚህን መንፈስ ፍሬ እንዳፈሩ በግልጽ ያሳያሉ። (ገላትያ 5:22, 23) እንግዲያው ጳውሎስ “ለራሳችሁና እግዚአብሔር ጠባቂ አድርጎ በላዩ ለሾማችሁ መንጋ ሁሉ ተጠንቀቁ” በማለት የሰጠው ምክር ለሁሉም ሽማግሌዎች፣ ለተቀቡትም ሆነ ላልተቀቡት በእኩል ደረጃ ይሠራል። (ሥራ 20:28 አ.መ.ት ) እነዚህ የተሾሙ ወንዶች ከአስተዳደር አካሉ መመሪያ ይቀበላሉ እንዲሁም በፈቃደኝነት ጉባኤውን ይጠብቃሉ። በዚህ መንገድ ክርስቶስ ከእኛ ጋር በመሆን ጉባኤውን በሚገባ ይመራል።
-
-
ክርስቶስ ጉባኤውን ይመራልመጠበቂያ ግንብ—2002 | መጋቢት 15
-
-
11. ሽማግሌዎች እንዲኖሩ ለተደረገው ዝግጅት አክብሮት ማሳየት ስንጠመቅ ከገባነው ቃል ጋር ተስማምቶ የመኖር ጉዳይ የሆነው ለምንድን ነው?
11 መሪያችን ፍጹም ነው። ስጦታ አድርጎ የሰጠን ሰዎች ግን ፍጹማን አይደሉም። ስለዚህ አልፎ አልፎ ስህተት ሊሠሩ ይችላሉ። ሆኖም ክርስቶስ ላደረገው ዝግጅት ምንጊዜም ታማኝ ሆነን መገኘታችን አስፈላጊ ነው። እንዲያውም ራሳችንን ለአምላክ ወስነን ስንጠመቅ ከገባነው ቃል ጋር ተስማምተን እንኖራለን ስንል በጉባኤ ውስጥ በመንፈስ ቅዱስ ሹመት አማካኝነት የሚገኝ ሥልጣን እንዳለ አምነን እንቀበላለን እንዲሁም ለዚህ ሥልጣን በፈቃደኝነት እንገዛለን ማለታችን ነው። “በመንፈስ ቅዱስ ስም” መጠመቃችን መንፈስ ቅዱስ ምን እንደሆነ እንደተገነዘብንና በይሖዋ ዓላማ ውስጥ የሚጫወተውን ሚና አምነን እንደተቀበልን በሕዝብ ፊት ማሳወቃችን ነው። (ማቴዎስ 28:19) ይህ ዓይነቱ ጥምቀት ከመንፈሱ ጋር እንደምንተባበርና በክርስቶስ ተከታዮች ላይ እንዳይሠራ የሚያግድ ምንም ነገር እንደማናደርግ ያሳያል። ሽማግሌዎች የድጋፍ ሐሳብ ሲቀርብላቸውም ሆነ ሲሾሙ መንፈስ ቅዱስ ወሳኝ ሚና የሚጫወት እንደመሆኑ በጉባኤ ውስጥ ካለው የሽማግሌዎች ዝግጅት ጋር ሳንተባበር ብንቀር ራሳችንን ለአምላክ ስንወስን የገባነውን ቃል በታማኝነት እየጠበቅን ነው ብለን ልንናገር እንችላለን?
-