-
“በመንፈስ የጋላችሁ ሁኑ”መጠበቂያ ግንብ—2009 | ጥቅምት 15
-
-
9. ጳውሎስ በመንፈስ የተቀቡ ክርስቲያኖችን ከአካል ክፍሎች ጋር ያመሳሰላቸው ለምንድን ነው?
9 ሮም 12:4, 5, 9, 10ን አንብብ። ጳውሎስ ቅቡዓን ክርስቲያኖችን ከአካል ክፍሎች ጋር ያመሳሰላቸው ሲሆን ራሳቸው በሆነው በክርስቶስ ሥር በአንድነት እንደሚያገለግሉ ገልጿል። (ቆላ. 1:18) ጳውሎስ፣ በአንድ አካል ላይ የተለያዩ ሥራዎች ያሏቸው ብዙ የአካል ክፍሎች እንዳሉና እነዚህ የአካል ክፍሎች ‘ብዙ ቢሆኑም እንኳ ከክርስቶስ ጋር ባላቸው አንድነት አንድ አካል እንደሆኑ’ በመንፈስ ለተቀቡት ክርስቲያኖች አስታውሷቸዋል። ከዚህ ጋር በሚመሳሰል መንገድ ጳውሎስ በኤፌሶን የሚገኙትን ክርስቲያኖች እንዲህ ሲል አሳስቧቸዋል፦ “በሁሉም ነገር ወደ እሱ ይኸውም ራስ ወደሆነው ወደ ክርስቶስ በፍቅር እንደግ። እሱን መሠረት በማድረግ፣ የአካል ክፍሎች ሁሉ አስፈላጊ የሆነውን ነገር በሚያሟላው በእያንዳንዱ መገጣጠሚያ አማካኝነት እርስ በርስ ተስማምተው እየተገጣጠሙና እያንዳንዱ የአካል ክፍል እንደ አቅሙ በሚያከናውነው የሥራ ድርሻ መሠረት እርስ በርስ ተደጋግፈው እየሠሩ፣ አካሉ እንዲያድግና በፍቅር ራሱን እንዲያንጽ ያደርጉታል።”—ኤፌ. 4:15, 16
-
-
“በመንፈስ የጋላችሁ ሁኑ”መጠበቂያ ግንብ—2009 | ጥቅምት 15
-
-
11. አንድነታችን በምን ላይ የተመሠረተ ነው? ጳውሎስ ምን ተጨማሪ ምክር ሰጥቷል?
11 እንዲህ ያለው አንድነት “ፍጹም የሆነ የአንድነት ማሰሪያ” በሆነው በፍቅር ላይ የተመሠረተ ነው። (ቆላ. 3:14) ጳውሎስ በሮም ምዕራፍ 12 ላይ ይህን ሲያጎላ ፍቅራችን “ግብዝነት የሌለበት” መሆን እንደሚገባውና “በወንድማማች ፍቅር” ‘እርስ በርሳችን ከልብ መዋደድ’ እንዳለብን ተናግሯል። እንዲህ ያለው ፍቅር እርስ በርስ እንድንከባበር ያደርገናል። ሐዋርያው “አንዳችሁ ሌላውን ለማክበር ቀዳሚ ሁኑ” በማለት ተናግሯል። እርግጥ ነው፣ ፍቅራችንን ስንገልጽ ተገቢ ያልሆነ ታማኝነት እናሳያለን ማለት አይደለም። የጉባኤውን ንጽሕና ለመጠበቅ የተቻለንን ሁሉ ማድረግ ይኖርብናል። ጳውሎስ ስለ ፍቅር በሰጠው ምክር ላይ አክሎ “ክፉ የሆነውን ነገር ተጸየፉ፤ ጥሩ የሆነውን ነገር አጥብቃችሁ ያዙ” በማለት ተናግሯል።
-