-
በይሖዋ መንገድ መመላለሳችሁን ቀጥሉመጠበቂያ ግንብ—1999 | ግንቦት 15
-
-
6, 7. እስራኤላውያን የይሖዋ አምላኪዎች የነበሩ ቢሆኑም እንኳ በየትኞቹ ወቅቶች ላይ ተሳስተው ነበር? ለምንስ?
6 እንዲህ ያለው ሁኔታ በጥንቱ እስራኤል ላይ ደርሶ እንደነበር ሐዋርያው ጳውሎስ አመልክቷል። እንዲህ ሲል ጻፈ:- “እነዚህም ክፉ ነገር እንደ ተመኙ እኛ ደግሞ እንዳንመኝ ይህ ምሳሌ ሆነልን። ሕዝብም ሊበሉ ሊጠጡም ተቀመጡ ሊዘፍኑም ተነሡ ተብሎ እንደ ተጻፈ ከእነርሱ አንዳንዶቹ እንዳደረጉት ጣዖትን የምታመልኩ አትሁኑ። ከእነርሱም አንዳንዶቹ እንደ ሴሰኑ በአንድ ቀንም ሁለት እልፍ ከሦስት ሺህ እንደ ወደቁ አንሴስን።”—1 ቆሮንቶስ 10:6-8
7 በመጀመሪያ ጳውሎስ እስራኤላውያን በሲና ተራራ ግርጌ የወርቅ ጥጃ ሠርተው ያመለኩበትን ወቅት ጠቀሰ። (ዘጸአት 32:5, 6) ይህ ድርጊታቸው ከጥቂት ሳምንታት ቀደም ብሎ እንደሚታዘዙ ቃል የገቡትን አንድ መለኮታዊ ትእዛዝ በቀጥታ የሚጻረር ነበር። (ዘጸአት 20:4-6፤ 24:3) ከዚያም ጳውሎስ እስራኤላውያን ከሞአብ ሴቶች ጋር ለበኣል የሰገዱበትን ጊዜ ጠቀሰ። (ዘኁልቁ 25:1-9) የጥጃ አምልኮ ፈንጠዝያ በሞላበት ‘ዘፈን’ የሚታጀብ ነው።a በበኣል አምልኮ ወቅት ደግሞ አስጸያፊ የፆታ ብልግና ይፈጸም ነበር። (ራእይ 2:14) እስራኤላውያን እነዚህን ኃጢአቶች የፈጸሙት ለምን ነበር? ልባቸው ‘ክፉውን ነገር’ ማለትም የጣዖት አምልኮውንም ሆነ በጣዖት አምልኮው ወቅት የሚፈጸመውን ልቅ የብልግና ድርጊት ‘እንዲመኝ’ ስለፈቀዱለት ነው።
8. እስራኤላውያን ከገጠሟቸው ሁኔታዎች ምን ልንማር እንችላለን?
8 ጳውሎስ ከእነዚህ ታሪኮች ትምህርት መቅሰም እንዳለብን ጠቁሟል። የምንማረው ግን ምንድን ነው? አንድ ክርስቲያን ለአንድ የወርቅ ጥጃ ወይም ለጥንቱ የሞዓባውያን አምላክ እንደማይሰግድ የታወቀ ነው። ይሁን እንጂ ስለ ፆታ ብልግና ወይም ከልክ በላይ ለራስ ፍላጎት ተገዢ ስለመሆን ምን ለማለት ይቻላል? እነዚህ ነገሮች በአሁኑ ጊዜ የተለመዱ ሆነዋል። ልባችን እነዚህን ነገሮች እንዲመኝ ከፈቀድንለት ከይሖዋ ጋር ያራርቁናል። ውጤቱ ተመሳሳይ ነው። የጣዖት አምልኮ እንደፈጸምን ያህል ከአምላክ እንድንርቅ ያደርጉናል። (ከቆላስይስ 3:5 እና ከፊልጵስዩስ 3:19 ጋር አወዳድሩ።) ጳውሎስ በዚያን ወቅት ተከስተው ስለነበሩ ጉዳዮች የሰጠውን ማብራሪያ የደመደመው ለእምነት ባልደረቦቹ “ጣዖትን ከማምለክ ሽሹ” የሚል ማሳሰቢያ በመስጠት ነው።—1 ቆሮንቶስ 10:14
-
-
በይሖዋ መንገድ መመላለሳችሁን ቀጥሉመጠበቂያ ግንብ—1999 | ግንቦት 15
-
-
a አንድ ተንታኝ እዚህ ላይ “ሊዘፍኑም ተነሱ” ተብሎ የተተረጎመው የግሪክኛ ቃል በአረማውያን በዓላት ወቅት የነበረውን ጭፈራ የሚያመለክት እንደሆነ ገልጸው “በሰፊው እንደሚታወቀው አብዛኞቹ ጭፈራዎች ልቅ የጾታ ስሜት ለማነሳሳት የታለሙ ናቸው” በማለት አክለው ተናግረዋል።
-