-
በመንግሥቱ አገዛዝ ሥር ያሳለፍነው መቶ ዓመት!መጠበቂያ ግንብ—2015 | ኅዳር 15
-
-
2. ኢየሱስ በማቴዎስ 28:19, 20 ላይ የሚገኘውን ተልእኮ ሲሰጥ ምን ያህል ደቀ መዛሙርት ተገኝተው ሊሆን ይችላል? እዚህ መደምደሚያ ላይ የደረስነው ለምንድን ነው?
2 ኢየሱስ ከሞት ከተነሳ ብዙም ሳይቆይ የመንግሥቱ አዋጅ ነጋሪዎች ለሚሆኑ ከ500 የሚበልጡ ደቀ መዛሙርት ታይቶ ነበር። (1 ቆሮ. 15:6) የመንግሥቱን መልእክት “ከሁሉም ብሔራት” ለተውጣጡ ሰዎች እንዲያደርሱ ያዘዛቸው በዚያ ወቅት ሳይሆን አይቀርም፤ በወቅቱ ይህን ሥራ ማከናወን ተፈታታኝ ነበር!a ኢየሱስ ይህ ታላቅ ሥራ “እስከ ሥርዓቱ መደምደሚያ ድረስ” እንደሚከናወን የተነበየ ሲሆን ይህም እየተፈጸመ ነው። አንተም ይህ ተልእኮና ትንቢት ፍጻሜውን እንዲያገኝ የበኩልህን አስተዋጽኦ እያደረግክ ሊሆን ይችላል።—ማቴ. 28:19, 20
-
-
በመንግሥቱ አገዛዝ ሥር ያሳለፍነው መቶ ዓመት!መጠበቂያ ግንብ—2015 | ኅዳር 15
-
-
a በዚህ ጊዜ ከተገኙት መካከል አብዛኞቹ፣ በኋላ ላይ ክርስቲያኖች እንደሆኑ ለማመን የሚያበቃ ምክንያት አለን። ጳውሎስ ለቆሮንቶስ ክርስቲያኖች በጻፈው ደብዳቤ ላይ እነሱን አስመልክቶ ሲናገር ‘ከ500 የሚበልጡ ወንድሞች’ ብሏቸዋል። አክሎም “አንዳንዶቹ በሞት ቢያንቀላፉም አብዛኞቹ ግን አሁንም ከእኛ ጋር አሉ” ማለቱ ትኩረት የሚስብ ነው። በመሆኑም ጳውሎስና በመጀመሪያው መቶ ዘመን የነበሩ ሌሎች ክርስቲያኖች፣ ኢየሱስ የሰጠውን ትእዛዝ በቦታው ተገኝተው ከሰሙት ወንድሞች አብዛኞቹን የሚያውቋቸው ይመስላል።
-