-
ከዓለም የተለየን ሆነን መኖር የምንችለው እንዴት ነው?‘ከአምላክ ፍቅር አትውጡ’
-
-
3. (ሀ) ኢየሱስ በዘመኑ ለነበረው የፖለቲካ ሥርዓት ምን አመለካከት ነበረው? (ለ) የኢየሱስ ቅቡዓን ተከታዮች አምባሳደሮች ሆነው ያገለግላሉ ሊባል የሚችለው ለምንድን ነው? (የግርጌ ማስታወሻውን ጨምረህ መልስ።)
3 ኢየሱስ በዘመኑ በነበረው የፖለቲካ ሥርዓት ውስጥ ከመካፈል ይልቅ ሙሉ በሙሉ ያተኮረው ስለ አምላክ መንግሥት፣ ማለትም ወደፊት ንጉሥ ሆኖ ስለሚያስተዳድረው መንግሥት በመስበክ ላይ ነበር። (ዳንኤል 7:13, 14፤ ሉቃስ 4:43፤ 17:20, 21) ጳንጥዮስ ጲላጦስ በተባለው ሮማዊ አገረ ገዥ ፊት በቀረበ ጊዜ “መንግሥቴ የዚህ ዓለም ክፍል አይደለም” ያለው በዚህ ምክንያት ነው። (ዮሐንስ 18:36) ተከታዮቹ ለክርስቶስና ለመንግሥቱ ታማኝ በመሆን እንዲሁም ይህን መንግሥት ለዓለም በማሳወቅ የእሱን አርዓያ ይከተላሉ። (ማቴዎስ 24:14) ሐዋርያው ጳውሎስ “እኛ ክርስቶስን ተክተን የምንሠራ አምባሳደሮች ነን፤ . . . ክርስቶስን ተክተን የምንሠራ እንደመሆናችን መጠን ‘ከአምላክ ጋር ታረቁ’ ብለን እንለምናለን” ሲል ጽፏል።a—2 ቆሮንቶስ 5:20
4. እውነተኛ ክርስቲያኖች በሙሉ ለአምላክ መንግሥት ታማኝ መሆናቸውን ያሳዩት እንዴት ነው? (“የጥንቶቹ ክርስቲያኖች ገለልተኛ ነበሩ” የሚለውን ሣጥን ተመልከት።)
4 አምባሳደሮች አንድን የውጭ አገር መንግሥት የሚወክሉ በመሆናቸው በሚሠሩባቸው አገሮች የውስጥ ጉዳይ እጃቸውን ጣልቃ አያስገቡም፤ ገለልተኛ ሆነው ይኖራሉ። ይሁን እንጂ አምባሳደሮች የሚወክሉትን አገር ጥቅምና ፍላጎት ያራምዳሉ። “የሰማይ ዜጎች” የሆኑት የክርስቶስ ቅቡዓን ተከታዮች ሁኔታም ከዚህ የተለየ አይደለም። (ፊልጵስዩስ 3:20) እንዲያውም መንግሥቱን በቅንዓት በመስበካቸው ምክንያት በሚሊዮን የሚቆጠሩ የክርስቶስ “ሌሎች በጎች” ‘ከአምላክ ጋር እንዲታረቁ’ ረድተዋል። (ዮሐንስ 10:16፤ ማቴዎስ 25:31-40) እነዚህ ሌሎች በጎች ለኢየሱስ ቅቡዓን ወንድሞች ድጋፍ በመስጠት የክርስቶስ ልዑካን ሆነው ያገለግላሉ። ሁለቱም ቡድኖች አንድ መንጋ በመሆን የመሲሐዊውን መንግሥት ጉዳዮች ስለሚያራምዱ ከዚህ ዓለም የፖለቲካ ጉዳዮች ፍጹም ገለልተኞች ናቸው።—ኢሳይያስ 2:2-4
-
-
ከዓለም የተለየን ሆነን መኖር የምንችለው እንዴት ነው?‘ከአምላክ ፍቅር አትውጡ’
-
-
a በ33 ከክርስቶስ ልደት በኋላ ከተከበረው የጴንጤቆስጤ በዓል ጀምሮ ክርስቶስ በምድር ባለው የቅቡዓን ተከታዮቹ ጉባኤ ላይ ንጉሥ ሆኗል። (ቆላስይስ 1:13) በ1914 ደግሞ ‘በዓለም መንግሥት’ ላይ ንጉሥ ሆኖ ተሹሟል። በመሆኑም በአሁኑ ጊዜ ቅቡዓን ክርስቲያኖች የመሲሐዊው መንግሥት አምባሳደሮች ሆነው ያገለግላሉ።—ራእይ 11:15
-