-
ሕሊናህን ማሰልጠን የምትችልበት መንገድመጠበቂያ ግንብ—1997 | ነሐሴ 1
-
-
ለምሳሌ ያህል በ2 ቆሮንቶስ 7:1 ላይ በሚገኙት በሚከተሉት የጳውሎስ ቃላት ላይ ለማሰላሰል ሞክር:- “እንግዲህ፣ ወዳጆች ሆይ፣ የዚህ ተስፋ ቃል ካለን፣ በእግዚአብሔር ፍርሃት ቅድስናን ፍጹም እያደረግን ሥጋንና መንፈስን ከሚያረክስ ሁሉ ራሳችንን እናንጻ።” የእነዚህን ቃላት ትርጉም ለመረዳት ሞክር። ‘ጳውሎስ “የዚህ ተስፋ ቃል” ብሎ የገለጸው ነገር ምንድን ነው?’ ብለህ ራስህን ጠይቅ። በጥቅሱ ዙሪያ ያለውን ሐሳብ ስታነብ ከላይ ከፍ ብለው ያሉት ቁጥሮች የሚከተለውን ሐሳብ እንደያዙ ትገነዘባለህ:- “ጌታ:- ከመካከላቸው ውጡና የተለያችሁ ሁኑ ርኵስንም አትንኩ ይላል፤ ሁሉንም የሚገዛ ጌታ:- እኔም እቀበላችኋለሁ፣ ለእናንተም አባት እሆናለሁ እናንተም ለእኔ ወንድ ልጆችና ሴት ልጆች ትሆናላችሁ ይላል።”—2 ቆሮንቶስ 6:17, 18
ጳውሎስ ‘ራሳችንን ከሚያረክስ ነገር እንድናነጻ’ የሰጠው ትእዛዝ አሁን የበለጠ ኃይል ያገኛል! አምላክ ‘እንደሚቀበለን’ ማለትም በእርሱ ጥበቃ ሥር እንድንሆን እንደሚያደርገን ቃል የገባልን መሆኑ ይህን ትእዛዝ እንድንፈጽም ይበልጥ ያነሳሳናል። ‘ከአምላክ ጋር ያለኝ ዝምድና በአባትና በልጅ መካከል ያለውን ዝምድና ያህል የተቀራረበ ነውን?’ ብለህ ራስህን ልትጠይቅ ትችላለህ። ጥበበኛና አፍቃሪ በሆነ አምላክ ‘ተቀባይነት ማግኘት’ ወይም መወደድ በጣም የሚያስደስት ነገር አይደለምን? በአባትና በልጅ መካከል ያለው ዝምድና ከአንተ ሁኔታ ጋር የሚያያዝ መስሎ ካልታየህ አፍቃሪ አባቶች ለልጆቻቸው ያላቸውን ፍቅርና የመውደድ ስሜት የሚገልጹበትን መንገድ ተመልከት። ከዚያ በኋላ በአንተና በይሖዋ መካከል እንዲህ ዓይነት ግንኙነት እንዳለ አድርገህ አስብ! ይበልጥ በጉዳዩ ላይ ባሰላሰልክ መጠን ለእንዲህ ዓይነቱ ዝምድና ያለህ ፍላጎት እያደገ ይሄዳል።
ሆኖም የሚከተለውን ልብ በል:- ከአምላክ ጋር መቀራረብ የምትችለው ‘ርኩስ የሆነውን ነገር የማትነካ’ እስከሆነ ድረስ ብቻ ነው። የሚከተሉትን ጥያቄዎች ራስህን ጠይቅ:- ‘የትምባሆ ሱስ አምላክ ከሚያወግዛቸው “ርኩስ ነገሮች” መካከል አይደለምን? ትምባሆ ሳጨስ ራሴን ለብዙ ዓይነት የጤና ችግሮች በማጋለጥ ‘ሥጋዬን ማርከሴ’ አይደለምን? ይሖዋ ንጹሕ ወይም “ቅዱስ” አምላክ እንደመሆኑ መጠን እያወቅኩ ይህን በማድረግ ራሴን ማርከሴ በእሱ ዘንድ ተቀባይነት ሊኖረው ይችላልን?’ (1 ጴጥሮስ 1:15, 16) በተጨማሪም ጳውሎስ “መንፈስን” ወይም የአእምሮ ዝንባሌን ከሚያረክስ ነገር እንድንጠበቅ ማሳሰቡን ልብ በል። እንዲህ እያልክ ራስህን ጠይቅ:- ‘ይህ ሱስ በአስተሳሰቤ ላይ ተጽእኖ ያደርጋልን? ፍላጎቴን ለማርካት ስል ትልቅ መሥዋዕትነት እስከ መክፈል ምናልባትም ጤናዬን፣ ቤተሰቤን አልፎ ተርፎም በአምላክ ዘንድ ያለኝን አቋም አደጋ ላይ እስከ መጣል እደርሳለሁን? ለትምባሆ ያለኝ ሱስ ሕይወቴን ምን ያህል እንዲጎዳው ፈቅጄለታለሁ?’ እነዚህን ሕሊና የሚረብሹ ጥያቄዎች ራስህን መጠየቅህ ልማዱን ለመተው የሚያስችል ቆራጥነት እንደሚሰጥህ የታመነ ነው!
-
-
“ዋጋዋ እጅግ የበዛ አንዲት ዕንቁ” አገኘመጠበቂያ ግንብ—1997 | ነሐሴ 1
-
-
የሊን ቤተሰብ እውነትን ከማጥናታቸው በፊት በማሳቸው ውስጥ ያለሟቸው 1,300 የቢተል ነት ተክሎች ነበሯቸው። ምንም እንኳ ተክሎቹ አድገው ትርፍ እስኪያስገኙ ድረስ አምስት ዓመት የሚፈጅ ቢሆንም አንድ ጊዜ ሙሉ ምርታቸውን መስጠት ከጀመሩ በኋላ ግን የሊን ቤተሰብ በዓመት 77,000 ዶላር ለማግኘት ይችል ነበር። መጀመሪያ የደረሰው ቢተል ነት የሚሰበሰብበት ወቅት ሲቃረብ የሊን ቤተሰብ አንድ አስፈላጊ እርምጃ መውሰድ ነበረበት። ክርስቲያኖች እንደ ሲጋራ ማጨስ፣ በዕፅ አለአግባብ መጠቀም እና ቢተል ነት ማኘክ በመሳሰሉ ርኩስ ልማዶች ከመጠቀምም ሆነ ከማስፋፋት በመራቅ “ሥጋንና መንፈስን ከሚያረክስ ሁሉ” ራሳቸውን ማንጻት እንዳለባቸው ከመጽሐፍ ቅዱስ ጥናታቸው ተምረው ነበር። (2 ቆሮንቶስ 7:1) ምን አድርገው ይሆን?
አቶ ሊን ሕሊናው እረፍት ስለነሳው ጥናቱን ለማቆም ወሰነ። ይህ በእንዲህ እንዳለ የአቶ ሊን ባለቤት ቀደም ሲል ተክለዋቸው ከነበሩ ዛፎች ጥቂት ቢተል ነቶችን በመሸጥ ከ3,000 ዶላር በላይ ትርፍ አገኘች። ይህ ደግሞ ተክሎቹ እንዲያድጉ ከተተዉ በቅርብ ጊዜ ውስጥ የሚያስገኙትን ትርፍ የሚያመላክት ነበረ። ሆኖም አቶ ሊን ሕሊናው እረፍት ሊሰጠው አልቻለም።
በጉዳዩ ላይ ካወጣና ካወረደ በኋላ አንድ ቀን በከተማው የሚገኙትን ምሥክሮች የቢተል ተክሎቹን እንዲቆርጡለት ጠየቃቸው። ምሥክሮቹ ይህን ለማድረግ የወሰነው እሱ ስለሆነ ተክሎቹን ራሱ በመቁረጥ ‘የገዛ ራሱን ሸክም መሸከም’ እንዳለበት ገለጹለት። (ገላትያ 6:4, 5) ምሥክሮቹ በ1 ቆሮንቶስ 10:13 ላይ የሚገኙትን “ለሰው ሁሉ ከሚሆነው በቀር ምንም ፈተና አልደረሰባችሁም፤ ነገር ግን ከሚቻላችሁ መጠን ይልቅ ትፈተኑ ዘንድ የማይፈቅድ እግዚአብሔር የታመነ ነው፣ ትታገሡም ዘንድ እንድትችሉ ከፈተናው ጋር መውጫውን ደግሞ ያደርግላችኋል” የሚሉትን ተስፋ ያዘሉ ቃላት እንዲያስታውስ አበረታቱት። በተጨማሪም ምሥክሮቹ “እኛ ዛፎቹን ቆርጠን ብናጠፋቸው ምናልባት ይጸጽትህና ለዛፎቹ መጥፋት እኛን ተወቃሽ ታደርገን ይሆናል” በማለት በምክንያት አስረዱት። ከጥቂት ጊዜያት በኋላ የመጋዝ ድምፅ የአቶ ሊንን ባለቤት ከጠዋት እንቅልፏ ይቀሰቅሳታል። ባለቤቷና ልጆቿ የቢተል ዛፎቹን እየቆረጧቸው ነበር!
አቶ ሊን ይሖዋ የገባውን ቃል የሚፈጽም መሆኑን ተገንዝቧል። ንጹህ ሕሊና እንዲኖረው የሚያስችለውን ሥራ ስላገኘ የይሖዋ አወዳሽ ለመሆን ችሏል። በሚያዝያ 1996 በተደረገ አንድ የይሖዋ ምሥክሮች የወረዳ ስብሰባ ላይ ተጠምቋል።
-