-
የእርዳታ አገልግሎትየአምላክ መንግሥት እየገዛ ነው!
-
-
6. (ሀ) ጳውሎስ እንደተናገረው የእርዳታ ሥራ የአምልኳችን ክፍል የሆነው ለምንድን ነው? (ለ) በዛሬው ጊዜ በዓለም ዙሪያ የእርዳታ ሥራ የምናከናውነው እንዴት እንደሆነ ግለጽ። (“አደጋ ሲከሰት!” የሚለውን በገጽ 214 ላይ የሚገኝ ሣጥን ተመልከት።)
6 ጳውሎስ የእርዳታ ሥራ፣ ክርስቲያኖች የሚያከናውኑት አገልግሎትና ለይሖዋ የሚያቀርቡት አምልኮ ክፍል የሆነበትን ምክንያት እንዲገነዘቡ የቆሮንቶስ ክርስቲያኖችን ረድቷቸዋል። ያቀረበውን ማስረጃ እንመልከት፦ እርዳታ የሚሰጡ ክርስቲያኖች ይህን የሚያደርጉት “ስለ ክርስቶስ ለሚገልጸው ምሥራች ተገዢዎች [ስለሆኑ]” እንደሆነ ተናግሯል። (2 ቆሮ. 9:13) ክርስቲያኖች የክርስቶስን ትምህርት በሥራ ማዋል ስለሚፈልጉ የእምነት ባልንጀሮቻቸውን ይረዳሉ። ጳውሎስ፣ ክርስቲያኖች ለወንድሞቻቸው ሲሉ የሚያከናውኑት የደግነት ተግባር “አምላክ [የሰጣቸው] የላቀ ጸጋ” መገለጫ እንደሆነ ተናግሯል። (2 ቆሮ. 9:14፤ 1 ጴጥ. 4:10) ከዚህ አንጻር፣ የታኅሣሥ 1, 1975 መጠበቂያ ግንብ (እንግሊዝኛ) የተቸገሩ ወንድሞቻችንን ስለማገልገል (የእርዳታ ሥራን ይጨምራል) የሚከተለውን ሐሳብ መስጠቱ የተገባ ነው፦ “ይሖዋ አምላክና ልጁ ኢየሱስ ክርስቶስ ለዚህ ዓይነቱ አገልግሎት ከፍ ያለ ቦታ እንደሚሰጡ ፈጽሞ ልንጠራጠር አይገባም።” በእርግጥም የእርዳታ ሥራ ትልቅ ቦታ የሚሰጠው ‘የቅዱስ አገልግሎት’ ክፍል ነው።—ሮም 12:1, 7፤ 2 ቆሮ. 8:7፤ ዕብ. 13:16
-
-
የእርዳታ አገልግሎትየአምላክ መንግሥት እየገዛ ነው!
-
-
7, 8. የምናከናውነው የእርዳታ አገልግሎት የመጀመሪያ ዓላማ ምንድን ነው? አብራራ።
7 የእርዳታ አገልግሎት የምንሰጥበት ዓላማ ምንድን ነው? ጳውሎስ ለቆሮንቶስ ሰዎች በጻፈው ሁለተኛ ደብዳቤ ላይ ለዚህ ጥያቄ መልስ ሰጥቷል። (2 ቆሮንቶስ 9:11-15ን አንብብ።) ጳውሎስ “ሕዝባዊ አገልግሎት” ይኸውም የእርዳታ ሥራ የምናከናውንባቸውን ሦስት ዋና ዋና ዓላማዎች በዚህ ጥቅስ ላይ ጎላ አድርጎ ገልጿል። እስቲ እነዚህን ዓላማዎች አንድ በአንድ እንመልከታቸው።
8 አንደኛ፣ የእርዳታ አገልግሎት መስጠታችን ለይሖዋ ክብር ያመጣል። ጳውሎስ ከላይ በተጠቀሱት አምስት ቁጥሮች ላይ ለወንድሞቹ ስለ ይሖዋ አምላክ ምን ያህል ደጋግሞ እንደተናገረ ልብ በል። ሐዋርያው ‘ለአምላክ ስለሚቀርብ ምስጋና’ እንዲሁም ‘ለአምላክ ስለሚቀርብ ብዙ ምስጋና’ ለወንድሞቹ ገልጾላቸዋል። (ቁጥር 11, 12) የእርዳታ ሥራ፣ ክርስቲያኖች “አምላክን እንዲያከብሩ” እንዲሁም ‘አምላክ የሰጣቸውን የላቀ ጸጋ’ እንዲያደንቁ እንደሚያደርግ ተናግሯል። (ቁጥር 13, 14) ጳውሎስ ስለ እርዳታ አገልግሎት የሰጠውን ሐሳብ የደመደመው “አምላክ የተመሰገነ ይሁን” በማለት ነው።—ቁጥር 15፤ 1 ጴጥ. 4:11
9. የእርዳታ ሥራ በሰዎች አመለካከት ላይ ምን ለውጥ ሊያመጣ ይችላል? ምሳሌ ስጥ።
9 እንደ ጳውሎስ ሁሉ በዛሬው ጊዜ ያሉ የአምላክ አገልጋዮችም የእርዳታ ሥራዎችን የሚመለከቷቸው ለይሖዋ ክብር ለማምጣት እንዲሁም ትምህርቶቹ ውበት እንዲጎናጸፉ ለማድረግ እንደሚያስችሉ አጋጣሚዎች አድርገው ነው። (1 ቆሮ. 10:31፤ ቲቶ 2:10) ደግሞም የእርዳታ ሥራ አንዳንዶች ስለ ይሖዋና ስለ ምሥክሮቹ ያላቸውን አሉታዊ አመለካከት ለመቀየር ብዙውን ጊዜ ትልቅ አስተዋጽኦ ያበረክታል። አንድ ምሳሌ እንመልከት፦ በአውሎ ነፋስ ከባድ ጉዳት በደረሰበት አካባቢ የምትኖር አንዲት ሴት በሯ ላይ “የይሖዋ ምሥክሮች፣ በሬን እንዳታንኳኩ” የሚል ምልክት ለጥፋ ነበር። ከዚያም አንድ ቀን ፈቃደኛ ሠራተኞች ከቤቷ ፊት ለፊት የሚገኘውን በአውሎ ነፋስ ጉዳት የደረሰበት ቤት ሲጠግኑ ተመለከተች። በሠራተኞቹ መካከል ወዳጃዊ መንፈስ እንዳለ በየዕለቱ ታስተውል ስለነበር እነዚህ ሰዎች እነማን እንደሆኑ ለማወቅ ወደ ቦታው ሄደች። እነዚህ ፈቃደኛ ሠራተኞች የይሖዋ ምሥክሮች እንደሆኑ ስትገነዘብ በጣም ተገረመች። “አሁን እንዳስተዋልኩት ስለ እናንተ የነበረኝ አመለካከት የተሳሳተ ነው” በማለት ተናገረች። ይህች ሴት ምን አድርጋ ይሆን? በሯ ላይ የለጠፈችውን ምልክት አንስታለች።
-