-
ይሖዋ የሚሰጠውን ማጽናኛ ማካፈልመጠበቂያ ግንብ—1996 | ኅዳር 1
-
-
ጳውሎስ በእስያ የደረሰበት መከራ
13, 14. (ሀ) ጳውሎስ በእስያ ውስጥ ያጋጠመውን ከባድ የመከራ ጊዜ የገለጸው እንዴት ነው? (ለ) ጳውሎስ የትኛውን ድርጊት በአእምሮው ይዞ ሊሆን ይችላል?
13 የቆሮንቶስ ጉባኤ እስከዚህ ደረጃ ድረስ የደረሰበት መከራ ጳውሎስ ከደረሰበት ብዙ መከራ ጋር ፈጽሞ አይወዳደርም። በመሆኑም እንዲህ ሲል ሊያሳስባቸው ችሏል፦ “በእስያ ስለ ደረሰብን መከራችን፣ ወንድሞች ሆይ፣ ታውቁ ዘንድ እንወዳለንና፤ ስለ ሕይወታችን እንኳ ተስፋ እስክንቆርጥ ድረስ ከዓቅማችን በላይ ያለ ልክ ከብዶብን ነበር፤ አዎን፣ ሙታንን በሚያነሣ በእግዚአብሔር እንጂ በራሳችን እንዳንታመን፣ እኛ ራሳችን የሞትን ፍርድ በውስጣችን ሰምተን ነበር። እርሱም ይህን ከሚያህል ሞት አዳነን፣ ያድነንማል፤ . . . ወደ ፊት ደግሞ እንዲያድን በእርሱ ተስፋ አድርገናል።”—2 ቆሮንቶስ 1:8-11
14 አንዳንድ የመጽሐፍ ቅዱስ ምሁራን ጳውሎስ የእሱንም ሆነ ከእሱ ጋር አብረው ተጉዘው የነበሩትን የመቄዶንያ ተወላጆች የጋይዮስንና የአርስጥሮኮስን ሕይወት ሊያሳጣ ይችል የነበረውን የኤፌሶን ከተማ ረብሻ መጥቀሱ ነበር ብለው ያምናሉ። እነዚህ ሁለት ክርስቲያኖች “የኤፌሶን [የሴት አምላክ] አርጤምስ ታላቅ ናት” እያሉ ለሁለት ሰዓት ይጮኹ በነበሩ ሰዎች ወደተሞላ ቲያትር ቤት በኃይል ተወሰዱ። በመጨረሻ የከተማው ባለ ሥልጣን ሕዝቡን ዝም ማሰኘት ቻለ። በጋይዮስና በአርስጥሮኮስ ሕይወት ላይ አንዣብቦ የነበረው ይህ አደጋ ጳውሎስን እጅግ ሳያስጨንቀው አልቀረም። እንዲያውም ወደ ውስጥ ገብቶ እነዚያን አክራሪ ረብሸኞች ለማሳመን ፈልጎ ነበር፤ ሆኖም ይህን በማድረግ ሕይወቱን አደጋ ላይ እንዳይጥል ከለከሉት።—ሥራ 19:26-41
15. በ1 ቆሮንቶስ 15:32 ላይ የተገለጸው ምን የከፋ ሁኔታ ሊሆን ይችላል?
15 ይሁን እንጂ ጳውሎስ ከላይ ከተገለጸው ድርጊት እጅግ የከፋ ሁኔታን መግለጹ ሊሆን ይችላል። ጳውሎስ ለቆሮንቶስ ክርስቲያኖች በጻፈው የመጀመሪያ ደብዳቤው “እንደ ሰው በኤፌሶን ከአውሬ ጋር ከታገልሁ . . . ምን ይጠቅመኛል?” ሲል ጠይቋል። (1 ቆሮንቶስ 15:32) ይህ ማለት ምናልባት የጳውሎስ ሕይወት አደጋ ላይ ወድቆ የነበረው የአውሬነት ጠባይ ባላቸው ሰዎች ብቻ ሳይሆን ቃል በቃል በኤፌሶን ስታድየም ከእንስሳት ጋር በሚደረገው ትግል ጭምር ሊሆን ይችላል። አንዳንድ ጊዜ ወንጀለኞች ደም የተጠሙ ሰዎች ቁጭ ብለው እየተመለከቱ ከአውሬዎች ጋር እንዲታገሉ በማድረግ ይቀጡ ነበር። ጳውሎስ ቃል በቃል ከአውሬዎች ጋር እንዲታገል ተደርጎ እንደነበረ መጥቀሱ ከሆነ ልክ ዳንኤል ከአንበሶች አፍ እንደዳነ ሁሉ እሱም መጨረሻ ላይ ከአሠቃቂ ሞት ተአምራዊ በሆነ መንገድ ተርፏል ማለት ነው።—ዳንኤል 6:22
-
-
ይሖዋ የሚሰጠውን ማጽናኛ ማካፈልመጠበቂያ ግንብ—1996 | ኅዳር 1
-
-
16. (ሀ) ብዙ የይሖዋ ምሥክሮች በጳውሎስ ላይ የደረሱትን መከራዎች በሚገባ ሊያውቋቸው የሚችሉት ለምንድን ነው? (ለ) በእምነታቸው ምክንያት የሞቱትን በተመለከተ ስለ ምን ነገር እርግጠኞች መሆን እንችላለን? (ሐ) አንዳንድ ክርስቲያኖች ከሞት የተረፉባቸው በጣም አስገራሚ ሁኔታዎች ምን ጥሩ ውጤት አስገኝተዋል?
16 በዘመናችን ያሉ ብዙ ክርስቲያኖች በጳውሎስ ላይ የደረሱትን ዓይነት መከራዎች እንደተቀበሉ መናገር ይችላሉ። (2 ቆሮንቶስ 11:23-27) በዛሬው ጊዜም ክርስቲያኖች ‘ከዓቅማቸው በላይ የሆኑ ከባድ መከራዎች’ አሳልፈዋል፤ ብዙዎቹም ‘ስለ ሕይወታቸው እንኳ ተስፋ እንዲቆርጡ የሚያደርጉ’ ሁኔታዎች አጋጥመዋቸዋል። (2 ቆሮንቶስ 1:8) አንዳንዶች የጅምላ ጭፍጨፋ ባካሄዱ ሰዎችና ጨካኝ በሆኑ አሳዳጆች እጅ ሕይወታቸው ጠፍቷል። የአምላክ አጽናኝ ኃይል መጽናት እንዲችሉ እንደረዳቸው እርግጠኞች መሆን እንችላለን። ተስፋቸው ሰማያዊም ይሁን ምድራዊ ልባቸውና አእምሮአቸው በተስፋቸው ፍጻሜ ላይ እንዳተኮረ ሞተዋል። (1 ቆሮንቶስ 10:13፤ ፊልጵስዩስ 4:13፤ ራእይ 2:10) በሌሎች ሁኔታዎች ደግሞ ይሖዋ አንዳንድ ጉዳዮች አቅጣጫቸውን እንዲለውጡ በማድረግ ወንድሞቻችን ከሞት እንዲተርፉ አድርጓል። በዚህ መንገድ የተረፉ ወንድሞች ‘ሙታንን በሚያስነሳው አምላክ’ ላይ ያላቸው ትምክህት ይበልጥ እንደጨመረ ጥርጥር የለውም። (2 ቆሮንቶስ 1:9) ከዚህ በኋላ የአምላክን አጽናኝ መልእክት ለሌሎች ሲያካፍሉ ከበፊቱ የበለጠ ሙሉ እምነት አድሮባቸው መናገር ይችላሉ።—ማቴዎስ 24:14
-