-
የወደፊት ዕጣህን መወሰን ትችላለህ?መጠበቂያ ግንብ—2005 | ጥር 15
-
-
ሐዋርያው ጳውሎስ እንዲህ ብሎ ጽፏል:- “በሰማያዊ ስፍራ በመንፈሳዊ በረከት ሁሉ በክርስቶስ የባረከን [አምላክ] . . . ዓለም ከመፈጠሩ አስቀድሞ በእርሱ መርጦናልና። . . . በኢየሱስ ክርስቶስ ልጆቹ እንሆን ዘንድ . . . አስቀድሞ ወሰነን።” (ኤፌሶን 1:3-5) አምላክ አስቀድሞ የወሰነው ምንድን ነው? ጳውሎስ ‘ዓለም ከመፈጠሩ አስቀድሞ መርጦናል’ ሲል ምን ማለቱ ነበር?
-
-
የወደፊት ዕጣህን መወሰን ትችላለህ?መጠበቂያ ግንብ—2005 | ጥር 15
-
-
ሐዋርያው ጳውሎስ “ዓለም ከመፈጠሩ አስቀድሞ በእርሱ መርጦናልና” ብሎ በጻፈበት ጊዜ በአእምሮው ይዞ የነበረው የትኛውን ዓለም ነው? እዚህ ላይ የጠቀሰው አምላክ አዳምና ሔዋንን በፈጠረበት ጊዜ የተገኘውን ዓለም አይደለም። ያ ዓለም ከኃጢአትና ከመጥፎ ሥነ ምግባር ነፃ የሆነ “እጅግ መልካም” ዓለም ነበር። (ዘፍጥረት 1:31) ስለዚህ የኃጢአት “ይቅርታ” ማግኘት አያስፈልገውም ነበር።—ኤፌሶን 1:7
ጳውሎስ የጠቀሰው፣ አዳምና ሔዋን በኤድን ገነት ውስጥ ካመጹ በኋላ የተፈጠረውንና አምላክ አስቦት ከነበረው በጣም የተለየ የሆነውን ዓለም ነው። ይህ ዓለም የተፈጠረው አዳምና ሔዋን ልጅ በወለዱ ጊዜ ሲሆን ከአምላክ የራቁ እንዲሁም የኃጢአትና የመጥፎ ሥነ ምግባር ባሪያ የሆኑ የሰው ልጆችን አቅፎ ይዟል። በተጨማሪም ዓለም የሚለው ቃል እንደ አዳምና ሔዋን በራሱ ፈቃድ ሳይሆን ሳይወድ በግዱ የኃጢአት ባሪያ በመሆኑ ምክንያት ቤዛ ሊከፈልለት የሚገባውን የሰው ዘር ያመለክታል።—ሮሜ 5:12፤ 8:18-21
ይሖዋ አምላክ በኤድን የተነሳው ዓመጽ ያስከተለውን ችግር ወዲያውኑ የመፍታት ችሎታ ነበረው። ይህን ማድረግ ባስፈለገው ጊዜ አንድ ልዩ ድርጅት ለማቋቋም ወዲያውኑ ወሰነ፤ ይህ ድርጅት በኢየሱስ ክርስቶስ የሚመራው መሲሐዊ መንግሥት ሲሆን ይሖዋ በዚህ መንግሥት አማካኝነት የሰው ዘሮችን ከአዳማዊ ኃጢአት ነፃ ከማውጣት ጋር የተያያዙ ነገሮችን ያከናውናል። (ማቴዎስ 6:10) አምላክ ይህን ያቀደው ቤዛ ሊከፈልለት የሚገባው የሰው ዘር “ዓለም ከመፈጠሩ አስቀድሞ” ማለትም ዓመጸኞቹ አዳምና ሔዋን ልጆች ከመውለዳቸው በፊት ነው።
-