-
ይሖዋ ቤተሰቡን ይሰበስባልመጠበቂያ ግንብ—2012 | ሐምሌ 15
-
-
7. ‘የመንፈስን አንድነት መጠበቅ’ ሲባል ምን ማለት ነው?
7 ይሖዋ፣ በክርስቶስ ቤዛዊ መሥዋዕት አማካኝነት ቅቡዓንን እንደ ልጆቹ፣ ሌሎች በጎችን ደግሞ እንደ ወዳጆቹ በመቁጠር ጻድቃን ብሎ ጠርቷቸዋል፤ ያም ቢሆን በዚህ ሥርዓት ውስጥ እስካለን ድረስ በመካከላችን አለመግባባት መከሰቱ አይቀርም። (ሮም 5:9፤ ያዕ. 2:23) እንዲህ ባይሆን ኖሮ “እርስ በርሳችሁ . . . በመቻቻል ኑሩ” የሚለው መለኮታዊ ምክር መሰጠት አያስፈልገውም ነበር። ታዲያ ከእምነት ባልንጀሮቻችን ጋር አንድነት ሊኖረን የሚችለው እንዴት ነው? “ፍጹም ትሕትናና ገርነት” ማዳበር ይኖርብናል። ከዚህም ሌላ ጳውሎስ “አንድ ላይ በሚያስተሳስረው የሰላም ማሰሪያ የመንፈስን አንድነት ለመጠበቅ” ልባዊ ጥረት እንድናደርግ አበረታቶናል። (ኤፌሶን 4:1-3ን አንብብ።) ይህን ምክር በሥራ ላይ ማዋል የአምላክ መንፈስ እንዲመራንና ይህ መንፈስ በውስጣችን ግሩም የሆኑ ባሕርያትን እንዲያፈራ መፍቀድ ይጠይቃል። የመንፈስ ፍሬ ደግሞ ከፋፋይ ከሆኑት የሥጋ ሥራዎች በተቃራኒ በግለሰቦች መካከል ያለው ልዩነት እንዲጠፋና በመካከላቸው አንድነት እንዲኖር ያደርጋል።
-
-
ይሖዋ ቤተሰቡን ይሰበስባልመጠበቂያ ግንብ—2012 | ሐምሌ 15
-
-
9. “የመንፈስን አንድነት ለመጠበቅ ልባዊ ጥረት” እያደረግን መሆን አለመሆናችንን ማረጋገጥ የምንችለው እንዴት ነው?
9 በመሆኑም እያንዳንዳችን ራሳችንን እንደሚከተለው በማለት መጠየቅ ይኖርብናል፦ ‘“አንድ ላይ በሚያስተሳስረው የሰላም ማሰሪያ የመንፈስን አንድነት ለመጠበቅ ልባዊ ጥረት” እያደረግኩ ነው? ከአንድ የእምነት ባልንጀራዬ ጋር ችግር ቢያጋጥመኝ ምን አደርጋለሁ? ሰዎች ከእኔ ጎን እንዲቆሙ ለማድረግ ስል ብሶቴን አገር እንዲያውቀው አደርጋለሁ? ከወንድሜ ጋር የነበረኝን ሰላማዊ ግንኙነት ለማደስ ጥረት ከማድረግ ይልቅ ሽማግሌዎች ጣልቃ ገብተው እንዲፈቱልኝ እጠብቃለሁ? አንድ ወንድም እንደተቀየመኝ ባውቅ ጉዳዩን አንስቶ ላለመነጋገር ስል በተቻለ መጠን ከእሱ ጋር ላለመገናኘት ጥረት አደርጋለሁ? እንዲህ ማድረጌ ይሖዋ ሁሉንም ነገር በክርስቶስ አማካኝነት በድጋሚ ለመጠቅለል ካለው ዓላማ ጋር ተስማምቼ እንደምኖር ያሳያል?’
10, 11. (ሀ) ከወንድሞቻችን ጋር ያለንን ሰላም መጠበቃችን አስፈላጊ የሆነው ለምንድን ነው? (ለ) ሰላምና መንፈሳዊ ብልጽግና እንዲኖር አስተዋጽኦ የሚያደርጉት ነገሮች ምንድን ናቸው?
10 ኢየሱስ እንዲህ ብሏል፦ “እንግዲያው መባህን ወደ መሠዊያው ባመጣህ ጊዜ ወንድምህ በአንተ ቅር የተሰኘበት ነገር እንዳለ ትዝ ካለህ መባህን በመሠዊያው ፊት ትተህ ሂድ። በመጀመሪያ ከወንድምህ ጋር እርቅ ፍጠር፤ ከዚያም ተመልሰህ መባህን አቅርብ። . . . ፈጥነህ እርቅ ፍጠር።” (ማቴ. 5:23-25) ያዕቆብም ቢሆን “ሰላም ፈጣሪ የሆኑ ሰዎች የጽድቅን ዘር ሰላማዊ በሆኑ ሁኔታዎች ሥር ይዘሩና የጽድቅ ፍሬ ያጭዳሉ” በማለት ጽፏል። (ያዕ. 3:17, 18) በመሆኑም በመካከላችን ሰላም ሳይኖር ጽድቅ የሚንጸባረቅበት ምግባር እናሳያለን ማለት አይቻልም።
11 እስቲ ነገሩን በምሳሌ ለማየት እንሞክር፦ ጦርነት ባጠቃቸው አንዳንድ አገሮች ውስጥ በተቀበሩ ፈንጂዎች ምክንያት ገበሬዎች 35 በመቶ የሚሆነውን አካባቢ ማልማት አልቻሉም። የተቀበሩት ቦንቦች ሲፈነዱ ገበሬዎቹ የሚያርሱትን መሬትና መተዳደሪያቸውን የሚያጡ ሲሆን በከተማ ያሉ ሰዎች ደግሞ የሚበላ ነገር አያገኙም። በተመሳሳይም ከወንድሞቻችን ጋር ያለንን ሰላም የሚያደፈርሱ ባሕርያት ካሉን መንፈሳዊ እድገታችን ይገታል። በሌላ በኩል ደግሞ ይቅር ለማለት ፈጣኖች ከሆንንና ለሌሎች መልካም ነገር የምናደርግ ከሆነ መንፈሳዊ ብልጽግና እናገኛለን።
-