-
በእምነታቸው የተጠሉ ሰዎችመጠበቂያ ግንብ—1998 | ታኅሣሥ 1
-
-
17. የመጀመሪያው መቶ ዘመን ክርስቲያኖች የስብከት ሥራ ውጤታማ እንደነበረ የሚያሳየው ምንድን ነው?
17 የመጀመሪያው መቶ ዘመን ክርስቲያኖች የአምላክን መንግሥት ምሥራች በማይቀዘቅዝ ቅንዓት ሰብከዋል። (ማቴዎስ 24:14) በ60 እዘአ ገደማ ጳውሎስ ምሥራቹ “ከሰማይ በታች ባለው ፍጥረት ሁሉ ዘንድ [ተሰብኳል]” ለማለት ችሎ ነበር። (ቆላስይስ 1:23) በመጀመሪያው መቶ ዘመን ማብቂያ ላይ የኢየሱስ ተከታዮች በመላው የሮማ ግዛት ማለትም በእስያ፣ በአውሮፓና በአፍሪካ ደቀ መዛሙርትን አፍርተው ነበር! ሌላው ቀርቶ ‘ከቄሣር ቤተሰብ’ አባላት መካከል አንዳንዶች ክርስቲያኖች ሆነው ነበር።a (ፊልጵስዩስ 4:22) ይህ ቅንዓት የተሞላበት ስብከት ጥላቻን አስነስቷል። ኔአንደር እንዲህ ሲሉ ተናግረዋል:- “ክርስትና በሁሉም የኑሮ መስኮች በሚገኙ ሰዎች ዘንድ ያለማቋረጥ ተቀባይነት እያገኘ በመምጣቱ መንግሥታዊውን ሃይማኖት ስጋት ላይ ጥሎት ነበር።”
-
-
በእምነታቸው የተጠሉ ሰዎችመጠበቂያ ግንብ—1998 | ታኅሣሥ 1
-
-
a ‘ከቄሣር ቤተ ሰዎች’ የሚለው አገላለጽ በወቅቱ ነግሦ የነበረው የኔሮ የቅርብ ዘመድ የሆኑ የቤተሰብ አባላትን ብቻ የሚያመለክት ላይሆን ይችላል። ከዚህ ይልቅ ለንጉሣዊው ቤተሰብና ለአባላቱ ምግብ የሚያዘጋጁና ጽዳትን የመሳሰሉ የቤት ውስጥ ሥራዎች የሚያከናውኑ የቤት ሠራተኞችንና ዝቅተኛ ሹማምንቶችን የሚያመለክት ሊሆን ይችላል።
-