-
ጥምቀት—ትልቅ ቦታ የሚሰጠው ግብ!ለዘላለም በደስታ ኑር!—አሳታፊ የመጽሐፍ ቅዱስ መማሪያ
-
-
3. አንድ ሰው ለጥምቀት ብቁ እንዲሆን ምን ማድረግ ይኖርበታል?
ከመጠመቅህ በፊት ስለ ይሖዋ መማርና በእሱ ላይ ጠንካራ እምነት መገንባት ይኖርብሃል። (ዕብራውያን 11:6ን አንብብ።) እውቀትህና እምነትህ እያደገ ሲሄድ ለይሖዋ ያለህ ፍቅርም ይጨምራል። ይህ ደግሞ ስለ እሱ ለመስበክና እሱ ባወጣቸው መሥፈርቶች ለመመራት እንድትነሳሳ ያደርግሃል። (2 ጢሞቴዎስ 4:2፤ 1 ዮሐንስ 5:3) አንድ ሰው ‘ለይሖዋ በሚገባ ሁኔታ መመላለስና እሱን ሙሉ በሙሉ ማስደሰት’ ሲችል ሕይወቱን ለአምላክ ለመስጠትና ለመጠመቅ መወሰኑ አይቀርም።—ቆላስይስ 1:9, 10a
-
-
ጥምቀት—ትልቅ ቦታ የሚሰጠው ግብ!ለዘላለም በደስታ ኑር!—አሳታፊ የመጽሐፍ ቅዱስ መማሪያ
-
-
a አንድ ሰው ከዚህ በፊት በሌላ ሃይማኖት ውስጥ ተጠምቆ የነበረ ቢሆንም እንኳ እንደገና መጠመቅ ያስፈልገዋል። ለምን? ምክንያቱም ቀደም ሲል የተጠመቀበት ሃይማኖት የመጽሐፍ ቅዱስን እውነት አያስተምርም።—የሐዋርያት ሥራ 19:1-5ን እና ምዕራፍ 13ን ተመልከት።
-
-
ለመጠመቅ ዝግጁ ነህ?ለዘላለም በደስታ ኑር!—አሳታፊ የመጽሐፍ ቅዱስ መማሪያ
-
-
1. ከመጠመቅህ በፊት ምን ያህል እውቀት ሊኖርህ ይገባል?
ለመጠመቅ “የእውነትን ትክክለኛ እውቀት” ማግኘት ያስፈልግሃል። (1 ጢሞቴዎስ 2:4) እንዲህ ሲባል ግን ከመጠመቅህ በፊት፣ ሰዎች ለሚያነሷቸው የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎች በሙሉ ምን መልስ መስጠት እንዳለብህ ልታውቅ ይገባል ማለት አይደለም። ከተጠመቁ ብዙ ዓመት የሆናቸው ክርስቲያኖችም እንኳ መማራቸውን መቀጠል ይኖርባቸዋል። (ቆላስይስ 1:9, 10) ይሁንና መሠረታዊ የሆኑትን የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርቶች ማወቅህ አስፈላጊ ነው። የጉባኤ ሽማግሌዎች በቂ እውቀት ይኖርህ እንደሆነና እንዳልሆነ ማወቅ እንድትችል ይረዱሃል።
-